A German airport management company bought 45 percent of Athens International Airport on May 31. Ethiopian International Airport.
ኢትዮጵያዊው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ እንደ ዊል ስሚዝ (Will Smith) ትወናውን ቀጥሎል፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይም ቢሆኑ የውጭውን ጉዞቸውን ቀነስ አድርገው የኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥ ስቃይ ላይ አተኩረው፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››ን ለማስቆም እንኮን አቅም ቢያጡ፣ የምስኪን ዜጎችን የግፍ ፍንቀላና ግድያ ይገጡ ዘንድ ፈጣን መፍትሄ እንዲዘይዱ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የግፍ ፍንቀላና ግድያ ሲፈፀሙም በእዛ በአማላይ ልሳናቸው ቅዋሜ ማሰማት የስልጣናቸው ግዴታ ነው፡፡ ዝምታቸው ግድየለሽ  እንዳያስመስላቸውም መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡› ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ፡፡ 1   አንድ አገር ብሄራዊ ኢኮኖሚዋን ለመገንባት መሠረተ ልማቶን ለማፋጠን የውጭ ምንዛሪ የሚስገኙ የግብርና ምርቶችና የማእድን ዘርፎች የሚወጡበት አካባቢ በቅድሚያ መንገዶች፣ የባቡር መስመሮችና ኤርፖርቶች ማስፋፋት አለባት፡፡ በዚህም መሰረት የኦሮሚያ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች የቡና፣ ሠሊጥ፣ የቦለቄ፣ የአበባ፣ የጫት፣ የወርቅ ወዘተ ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ ሦስት አራተኛውን የሃገሪቱን የውጭ መንዛሪ ስለሚያስገኙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ የምጣኔ ኃብት ጠበብቶች፡፡ የወያኔ መሠረተ ልማት በጠባብ ብሄርተኛነትና በአድሎ ላይ የተመሰረተ ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሪ አስተዋፅዖ በማያደርጉ ከልሎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ለውጭ ዕዳ ሃገሪቱን ዳርጎል፣ በዚህም ምክንያት በክልሎች ያልተመጣጠነ እድገት በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ የሃገሪቱ ብሄራዊ ኢኮኖሚ በክልላዊ ኢኮኖሚ በመተካቱ በመንግስት ውስጥ ስውር መንግስት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የሃገሪቱ ብድርና የዕዳ ጫና የተከሰተው በዚህ ምክንያት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡

ተልባ ቢንጫጫ፣ በአንድ ሙቀጫ!!!፣ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት

{1} የወያኔ መንግሥት ከትንሽ  ጊዜ በኃላ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› አንስተናል ብለው ያውጃሉ!!!  ሆኖም የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት የመከላከያ ሠራዊትና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲና  ኮማንድ ፖስቱ  ከክልሎች አይወጣም አፈናውና ጭቆናው ይቀጥላል ፡፡ በተጨማሪም ወያኔ ሌሎች አጋር ድርጅቶችን በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ ሌሎች የጦር አበጋዞች መንግሥት  ልክ እንደ ሶማሌው ፕሬዜዳንት አብዲ አሊ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ የጦር አበጋዞች መሪዎች በማሰልጠንና በመፈልፈል የህዝብ ግጭትን በማስፋፋት አቅጣጫ ማስቀየር ሴራ ይቀጥላል፡፡

{2} የወያኔ ሌቦችና ሙሰኛች ከእስር ተፈተዋል፣ ብዙ የፖለቲካ እስረኞች አሁንም ወህኒ ቤት ናቸው፡፡ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ በኮንትሮባንድ ድንበር አቆርጦ ለመውጣት ሲሞክር መያዙን ሬዲዬና ቴሌቪዥን ተገልፆል፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ የሌቦችና ሙስናን የመታገል አቆም ከቃላት የዘለለ አይደለም፡፡ ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎችንና ገዳይና ሌቦችን ሊያስታርቁ ይሻሉ! የሃገሪቱ ህገመንግሥትና ህግ ካልተከበረ ሰላም አይመጣም!!!

{3} የህዝብ መፈናቀል ቀጥሎል፣ በሶማሌና ኦሮሞ ግጭት ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተፈናቅለዋል፣ ከቤኒሻንጉል ከብዙ ሽህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎል፣ በጌዲዮና ጉጂ ዞን ከ200 ሽህ ህዝብ በላይ ተሰደዋል፣ አዲስ አበባ ሃና ማርያም ከ20 ሽህ ህዝብ በላይ ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ፈሰዋል፡፡ ሰሚ ያጣው ተፈኛቃይ ህዝብ ዶክተር አብይ አህመድን ‹‹ለቤት ሳማ፣ ለውጭ ቄጤማ!!!›› እያላቸው ይገኛል፡፡

{4} ወያኔ የዲሞክራታይዜሽኑን ምህዳር በማስፋት መንግስት ከሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እውነተኛ ድርድር አደርጋለሁ ብሎ  ለሁሉም በግልፅ ይፋዊ የውሽት ጥሪ ያደርጋል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣  ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣  ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- ለውይይት ይጠራልና በተንዛዛ አጀንዳና ጉንጭ አልፋ ውይይት ግማሽ አመት ይፈጃሉ፡፡ ወያኔ በትረ ሥልጣኑን እያጠናከረ ይገዛል፡፡ የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ መሪነት (private-sector-led) እድገትን፣ በተለያዮ ዘርፎች ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ  ሰላምና ብልፅግናን አጎናፅፋለሁ በማለት  የልማት ዕርዳታና ድጋፍ የሚሠጡ መንግሥታትና ዓለም ዓቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችን ወያኔ ያማልላል፣ ከእነሱም እርዳታ ያገኛል፡፡ በቅርቡ 250 ሚሊዮን ዶላር ከቻይና መንግስት በትግራይ ውኃ አገልግሎት የሚውል ብድር አግኝቶል፡፡ ‹‹ምክር ቤቱ የ702 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አፀደቀ›› ከዓለም ባንክ ብድርና እርዳታ በቅርቡ አግኝቶል፡፡

{5} ሸክ አላሙዲን በማስፈታት በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንዲያደርጉ የኢንቨስትመንት አርዐያ አድርጎ ለድቤ መችዎቹ በሚሊኒየም አዳራሽ አስጨብጭቦል፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ክልል ልጆቻቸው ለተገደሉባቸውና ለተፈናቀሉ ዜጎች መልስ ሳይሠጥና አንዳርጋቸው ፅጌና ሌሎች እስረኞች ሳይፈታ በሳውዲ ዜጋ ለማስፈታት ድራማውን ቀጥሎል፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መንግሥት ከኣለም የልማት ማሕበር ጋር የ702 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አፀደቀ› ከዚህ ውስጥ 327 ሚሊዮን ዶላር ለከተሞችየተቆማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፍያ ፕሮግራም፣ ቀሪው 375 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እንደሚውል ተመልክቶል፡፡ ከብድሩ ስምምነት በተጨማሪ የዓለም ባንክ 273 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ የተለገሰ ሲሆን፣ ይህም ለኤሌክትሪፊኬሽን ማስፈፀሚያ ይውላል፡፡››2

{6} ዶክተር አብይ አህመድ በየአስራምስት ቀናት አምስት አምስት ከ75 እስከ 80 እድሜ ያላቸው ሹማምንቶች ጡረታ ያስወጣሉ ይህም ስድስት ወራት ይፈጅባቸዋል፣ ልክ እየሰፈሩ እስረኞች እንደሚለቁና በምትካቸው አዲስ እስረኞች ዘብጥያ እንዳሚያወርዱ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ዓይነት ነው የትወና ጨዋታው፡፡ በጡረታ ሚኒስቴር እድሜቸው ያለፈ ሹማምንቶች ሚኒስትር፣ ሚኒስቴር ድኤታ፣ ጀነራል መኮንኖች የስም ዝርዝር ስላለ በአንድ ጊዜ እነዚህን ጡረተኞች በአንዴ ቢጠርጎቸው ትወናዎ ያጥርብዎታል፡፡ የተፎካካሪ ፓርቲ ፖለቲከኛዋችም እነ አቶ ሌንጮ ለታ፣ ዲማ ነገዎም ወዘተ ጡረታ ወጥተው በወጣቶች መተካት ግድ ይላቸዋል፡፡ ሁሉም ሰው በህግ ፊት ጡረታ የመውጫው እድሜ በእኩልነትና ያለአድሎ ይከበር!!! ለሁሉም ፖለቲከኞች የእድሜ ገደብ በሥራ ላይ ይዋል፡፡ ደ/ር አአ በጋዜጠኞችና ፋስቡክ ላይ ያላቸው አቆም ኢህአዲጋዊ በረከታዊ ትራንፓዊ ተናዳፊ ምላሳዊነት መለወጣቸው አይቀሬ ነው፡፡ በዲያስፖራና በወልቃይት ጥያቄ ላይ ፍርደ ገምድል የአውቃለሁ ባይነት የሸፍጥ ተናዳፊነት ፍንጭ ከአንደበታቸው ወጥቶልና!!! ነገ ይደግሙታል፡፡ ዊሊ ስሚዝ የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ መምህራንንና ፕሬስ ኮንፍረንስ የጋዜጠኞች ጥያቄንና የምሁራን ለማወያየት ፈርተዋል፡፡  ለጠቃቅንና ለኮብል ስቶን አንድ ለአምስት ወያኔ ያደራጃቸውን ወጣቶች በማስጨብጨብ ትወና ዶክተር አብይ ራሳቸው ገዝፈው ታይተዋል፡፡ በሚቀጥለው ጥቂት ወራቶች ውስጥ የህዝብ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ምክንያት ህዝባዊ እንቢተኝነትና አመጽ ዳግም ይቀጣጠላል እንላለን፡፡

{7} የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ህዝቡን አስመርሮታል፣ የስንዴ፣ ዘይት፣ ስኮር፣ ዱቄት፣ ወዘተ የዳቦ ዋጋ መናር ህዝቡን አሰቃይቶታል፣ የቤት ኪራይ መጨመር፣ የህዝብ ከመኖሪው መፈናቀል መልስ አላገኘም፣ በተለይ የመድኃኒቶች ከገበያ መጥፋት ህዝቡን አስመርሮታል፡፡

ኢትዮጵያ ከሃገረ ግሪክ የዕዳ ጫና ትማር ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት፣ለማዓት!!!  በ2017 እኤአ የግሪክ መንግሥት በተዘፈቀበት 354 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ምክንያት የባህር ወደቦቹን፣ ኤርፖርቶቹንና ሜጋ ፕሮጀክቶቹን በዕዳ ጫና ምክንያት ለውጪ ኢንቨሰተሮች በፕራይቬታይዝ ተሸጠዋል፡፡

የአየር መንገድ አገልግሎት፣ በዓለም አቀፍ የሎጅስቲክስ የአፈፃፀም መለኪያ (Logistics Performance) ከነበረበት 2.59 በ2012 ወደ 3.07 ከፍማድረግ} { ዓለም አቀፍ የበረራ ጣቢያዎችን እና የተያያዙ የአለም አቀፍ መንገዳኞችን ብዛት በቅደም ተከተል በ2007 ከነበረበት 81 ጣቢያዎች እና 4.5 ሚሊዩን መንገደኞች በ2012 ወደ 127 ጣቢያዎች እና 11.3 ሚሊዩን መንገደኖች ማድረስ፣} { የአውሮፕላኖችን ቁጥር በ2012 ወደ 113 ማድረስ እና የአገር ውስጥ መንገደኞች ቁጥርን በ2012 ወደ 2.6 ሚሊዩን ማድረስ፣} { የጭነት(Cargo) አገልግሎትን በ2012 ዓ/ም 503.7 ሽህ ቶን ማድረስ፣ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በ2012 አ/ም 5.1 ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር ማድረስ፣} { የውጪ ንግድ ምርቶችን ለመደገፍ እንዲቻል በክልል ኤርፖርቶች ያሉትን ቀዝቃዛ መጋዘኖች ቁጥር ከ2 ወደ 3 ከፍ እንዲል ማድረግ፣}

የኢትዩጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት፣ የቀድሞው የኢትዩጵያ ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር ሥር የነበረ ኃላም ራሱን ችሎ በ1995 ዓ/ም የኤርፖርቶች መሠረተ ልማት ግንባታዎች እንዲስፋፋና እንዲያስተዳድር በደንብ ቁጥር 82/1995 ዓ/ም የኢትዩጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ተቆቆመ፡፡ አገራችን ለአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ለምታስመዘግበው እድገት የኤርፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ኢትዩጵያ 22 ኤርፖርቶች ያሎት ሲሆን፣ አራቱ ዓለም ዐቀፍ በረራን፣ አሥራ ስምንቱ የሃገር ውስጥ በረራዎችን የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡ በ2008 ዓ/ም በጀት ዓመት ኤርፖርት የሌላቸው 7 አካባቢዎች የሮቤ፣ ጂንካ፣ ሽሬና ሠመራ ኤርፖርቶች አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ግንባታ ሲከናወን ቆይቶል፡፡ በተጨማሪም የባህር ዳር ግንቦት 20 ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ማስፋፊያ ግንባታ በመከናወን ላይ ነበር፡፡

አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ግንባታ በ2008/09 ዓ/ም በጀት ዓመት ውስጥ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያሉበት ሁኔታ፤ {1} የሮቤ ኤርፖርት አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ለግንባታው የተበጀተ ጠቅላላ ገንዘብ 494,846,771 ሚሊዮን ብር {2} የጂንካ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ለግንባታው የተበጀተ ጠቅላላ ገንዘብ 571,711,451 ሚሊዮን ብር {3} የሽሬ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ  ለግንባታው የተበጀተ ጠቅላላ ገንዘብ 417,585,000 ሚሊዮን ብር {4} የሠመራ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ  ለግንባታው የተበጀተ ጠቅላላ ገንዘብ 450,000,000 ሚሊዮን ብር በ2008/09 ዓ/ም በጀት ዓመት ውስጥ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ ግንባታ እየተጠናቀቀ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ {5} የደንቢዶሎ ኤርፖርት አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ፣ ለግንባታው ጠቅላላ ወጪ  ገንዘብ 42,000,000.000 ቢሊዮን ብር በወርሃ ግንቦት በ2010ዓ/ም ሥራ ጀምሮል፡፡ {6} የሃዋሳ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ፣ ለግንባታው ጠቅላላ ወጪ  ገንዘብ 457,350,361 ሚሊዮን ብር {7} የቀብሪ ደሀር አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ፣ ለግንባታው ጠቅላላ ወጪ  ገንዘብ 417,585,000 ሚሊዮን ብር፡፡

የአይሮፕላን ማረፍያ፤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት አራት ደረጃቸውን የጠበቁ የአይሮፕላን ማረፍያዎች በመቐሌ፣አክሱምና፣ሁመራ (የጎንደር መሬት ወደ ትግራይ በጉልበት የተጠቃለለ) እንዲሁም አራተኛው የሽሬ አውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፊያ ሜዳ በጀነራል ኃያሎም አርዓያ ስም ተሠርቶ ተጠናቆል፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እቅድ የአይሮጵላን ማረፍያ፣ ባቡር፣ ኢንዱስትሪያ ዞን፣ ስኮር፣ ሃይድሮፓወር ወዘተ ድርሻ ሄዶ! ሄዶ! ያልተስተካከለ የክልሎች እድገት ማስከተሉን ፍንትው ብሎ አድሎዊነቱ ይስተዋላል፤ እንደ ክልሎች ኃብትና የውጪ ምንዛሪ አስተዋፅኦ ድርሻ ልማቱ መከወን አለበት፣ አንዱ ክልል ምንም የውጭ ምንዛሪ አስተዋፅኦ ያላበረከተ በአድሎና በሌብነት የሚደረግ የሃብት ቅርምትና መስገብገብ ውሎ አድሮ ያስጠይቃል፡፡ አንዱ ክልል በሌላው ክልል ኪሳራ ማደግ የለበትም እንላለን ካለበለዛ፣ አበው እንዳሉት ‹‹ለብዙ ፀሎት ማሠርያው አቡነ ዘበሰማያት!!!››

  • የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ማስፋፊያ ሥራ ግንባታው በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ኩባንያ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ለግንባታው የተበጀተ ጠቅላላ ገንዘብ 345,000,000 ዶላር
  • የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናጃ ህንፃ ማስፋፊያ ሥራ ግንባታው በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ኩባንያ (China Communication corporation Company (CCCC) ያካሂዳል፡፡
  • በአሁኑ ግዜ ኤርፖርቱ በአመት8 ሚሊዩን መንገደኞችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡ የአየር መንገዱ አስተዳደር በአንድ ዘር ላይ የተዋቀረ አድሎዊና ኢ-ፍትሃዊ አሰራር የሚከተል አስተዳደር በመሆኑ የሠራተኞች ብሶት ከፍተኛ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይገልፃሉ፡፡
  • የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ግንባታ ሥራዉ ሲጠናቀቅ በዓመት ከ20 ሚሊዩን በላይ መንገደኞች ማስተናገድ ይችላል፡፡ በቀን በአንድ ጊዜ አምስት ሽህ ተጎዦችን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
  • የኢትዩጵያ አየር መንገድ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል ግንባታ በ65 ሚሊዩን ዶላር ወጭ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሚገኝ 40,000 ካሬ ሜትር ላይ አራት የተለያዩ ምግብ ቤቶች፣ሁለት መጠጥ ቤቶች፣ 370 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት መዋኛ ገንዳዎች፣ ጂምናዚም፣ ስጦታ መሸጫ ሱቆች፣ 2,000 ሰዎች የሚያስተናግድ የመሰብሰቢያ አዳራሰሾች፣ 3 አነስተኛ አዳራሾች ያሉት ሆቴል በማስገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታውን የሚያካሂደው አቪክ የተሰኘ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡
  • በሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ውስጥ መሆናችንና የዲያጎ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅና ኢትዮጵያውያኖች መገደል የውጭ ሃገራት ኢንቨስተሮችን፣ መንገደኞችና አገር ጎብኝዎች የመምታትን ፍላጎት ያጨልማል፡፡ መንግስት ከቱሪዝም ያገኝ የነበረው ትልቅ ገቢ ቀንሶል፡፡ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የመንግሥት የኦክሲጂን እጥረት ሆኖበት የሃገሪቱ ዕድገት በዶላር ደዌ ተይዞ አልጋ ላይ ውሎ አድሮል፡፡ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጎትቶል፡፡ የከተማ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ ተስተጎጉሎል፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ለጥፋት በማለት ህዝቡ ትግሉን ቀጥሎል፡፡

የኢትዬጵያ አየር መንገድ፣ አይሮፕላኖቹን እያስያዙ ከተለያዩ ባንኮች የሚያደርጎቸውን የውጭ ብድሮች ቀጥለን እንመልከት፡፡ በ2008 እኤአ ስምንት ቦንባርዲየር ኪው 400 አይሮፕላኖች 242 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር፣በ2010እኤአ አስር ቦይንግ 737-800 አይሮፕላኖች  767 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ዋጋ ለመግዛት ተስማምተዋል፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ1.6 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለአስር ቦይንግ ድሪም ላይነርስ አበድሮል፡፡ በ2011 እኤአ አራት ቦይንግ 777ኤፍ አይሮፕላኖች በ1.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለመግዛት ስምምነት ተፈፅሞል፡፡ በ2012 እኤአ አምስት ኪው 400 አይሮፕላኖች   160 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለርና ተጨማሪ አንድ ቦይንግ 777-200ኤልአር አይሮፕላን  276 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር  ለመግዛት ስምምነት ተደርጎል፡፡ በተለያየ ግዜትም የተገዙት አይሮፕላኖች ወደ አገር ውስጥ ገብተዋል፡፡በ2013 እኤአ ኤር ሊዝ ኮርፖሬሽንና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ 777-300 ኢአር አይሮፕላኖች ለመከራየት  ተስማምተው፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ130 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ለኢትዬጵያ አየር መንገድ  ብድር አበደረ፡፡ በ2014 እኤአ የኢትዬጵያ አየር መንገድ 20 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላኖች  የ2.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከዩኤስ አቪየሽን ጋር ስምምነት አደርገዋል፡፡ በተጨማሪም አስራአምስት 737 ማክስ 8 ነዳጅ ቆጣቢ አይሮፕላኖች ለመግዛት ስምምነት ፈፅመዋል፡፡በአጠቃላይ ከ 2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር አይሮፕላኖች ለመግዛት የውጭ ብድር ተበድሮል፡፡ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ አይሮፕላኖቹን 1,730,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር በማበደር የአንበሳውን ድርሻ በመያዝ የኢትዬጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች በወለድ አግድ collatoral በመያዝ እንደሚያበድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 56 እስከ 58% እጅ ይይዛል፡፡ በሌላ በኩል መንግሥታዊና የግል ዘርፎች ትስስር የረጅም ጊዜ ስምምነትና ፍቃድ፣ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፕራይቬታይዝ በማድረግ በሚገኝ ገንዘብ መሠረተ ልማት ግንባታ ማካሄድ እንደሚቻል አይ ኤፍ ኤም አሳስቦል፡፡ እንዲሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቴሌኮም ከባህር ማዶ ብድር እንዳይበደሩ ቢያሳስቡም ያለበቸውን እዳ ግን ባለመግለፅ ወያኔን ተባበረዋል፡፡ አይ ኤም ኤፍ፣ የኢትዮጵያ የዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶል ብሎል!!!

የኢትዮጵያ ሃገራችን የህዝብ ሃብትም ዕጣ ፈንታችን  ለቻይና መንግሥት በእዳ ጫና ምክንያት መሸጡ አይቀሬ መሆኑ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ቻይና ቻይና የሸተተ ልማት፣ ለቅኝ ተገዥነት!!!   የአቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ ሄለኒክ ሪፓብሊክ አሴት ዲቨሎፕመንት ፈንድ አቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ለአቪአልያንስ የጀርመን ኤርፖርት ማኔጅመንት ካንፓኒ በ45 በመቶ ድርሻ  በ672 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጦል፡፡ በ2016እኤአ ጀርመን ካንፓኒ ሆነው  ፍራፖርት ስሌንቴል 14 የግሪክ የአይሮፕላኖች ማኮብኮቢያና ማረፍያዎች፣ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር ገዝተዋል፡፡ ስምምነቱ የዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ፍላጎት የመንግሥታዊ ኃብቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ብሎም የ86 ቢሊዩን ፓውንድ እዳ ለመክፈል የተደረሰ የአቴንስ ስምምነት ነበር፡፡ የፍራንክ ፈርት ኤርፖርት ኦፕሬተር ፍራፖርት በ1.23 ቢሊዮን ፓውንድ የ40 ዓመታት ሊዝ ኮንትራት ፈፅመዋል፡፡3 ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሳ!!! የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

 

ምንጭ

{1} (ዘ-ሐበሻ ሜይ 21 ቀን 2018እኤአ)

{2} ግንቦት 8 ቀን ቀን 2010 አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{3} Hellenic Republic Asset Developent Fund (HRADF) website.