አገር ሠሪ፣ አገር አልባ ሕዝብ!
ዐማራው በትግሬ ወያኔ-ኦነግ አገር የለሽ ተደርጓል!!

ዐማራ እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ኢትዮጵያን እንደ አገር ከሠሯት ነገድና ጎሣዎች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን የአገሪቱ የረጅም የመንግሥትነትና አገራዊነት ታሪክ ያስረዳል። ዐማራው ቋንቋን ከፊደል፣ ሃይማኖትን ከሥርዓት፣ ሕግን ከባህል፣
አጣጥሞና አዋሕዶ ለኢትዮጵያውያን የወል መጠቀሚያነት ያበረከተ ሕዝብ ነው። ጀግናና ኩሩም ነው። የዛሬውን አያድርገውና፣ መብቱ ሲነካበት የማይወድ፣ ለማንነቱና ለነፃነቱ ቀናዒ ሕዝብ የነበረ ነው። እነዚህ መገለጫዎቹ መሆናቸውን የድሆኖ፣ የእንትጮ፣ የሣር ውኃ፣
የመተማ፣ የዐድዋ፣ የአምባላጌ፣ የወልወል፣ የቆራሄ፣ የመቀሌ፣ የማይጨው ወዘተ ጦር ሜዳዎችና የተገኙት ድሎች ሕያው ምስክሮች ናቸው።

PDF: የዐኅኢአድ ልሳን – መቅደላ ቅጽ ፩ ቁጥር ፲፫ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲ ዓም