May 24, 2018
ከጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ
አፄ ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ መንግሥት የሚቆጣጠረውን የብሔራዊ ሜታልና ኢንጂነሪንግ (ሜቴክ) የዳይሬክተሮች ቦርድ የአመራር ለውጥ በማድረግ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የሆኑትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንን 3ኛው የቦርድ ሊቀ መንበር አድርገው ሾመዋል። ዶ/ር አምባቸው ላለፉት 6 ወራት ቦታው ላይ የነበሩትን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ በቦታው በሃላፊነት የቆዩትን የቀድሞው መከላከያ ሚንስትርና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር የሆኑትን ሲራጅ ፈጌሳን ተክተው ይሰራሉ ማለት ነው።
ሜቴክ ከ10 አመት በፊት በ10 ቢሊዮን ካፒታል የተቋቋመ የመከላከያ ተቋም ሲሆን 17 የኢንዱስትሪ ሰብሲደሪዎችና 19 ሺህ ሰራተኞችን ያቀፈ፤ እስካለፈው ወር ድረስ በመከላከያው ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እየተመራ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ፣ የውዝግብና የሙስና መናኸሪያ የሆነ መንግሥታዊ ድርጅት ነው።
ለዚሁ ተቋም ተጨማሪ የቦርድ አመራር ውስጥ የተካተቱት የቀድሞው ጠቅላይ መለስ ዜናዊ ባለቤት የሆኑት በኅብረተሰቡ “የሙስናዋ እናት” በመባል የሚታወቁትና ባለፈው ታህሳስ ወር ከህወሃት ፖሊት ቢሮ አባልነታቸው የተነሱት ወይዘሮ አዜብ መስፍን (ጎላ) እና በፓርላማው የመንግሥት ወኪል የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፋሶ) ናቸው።
ኤርሚያስ ለገሰ አንደጻፈው አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነብሶ) የሚከተሉት በግልፅ የተቀመጡ ስልጣኖች አሉት፣
#1• የህውሓት እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
#2 • የመንግስት ዋና ተጠሪ
#3 • የበጐ አድራጐትና ማህበራት የቦርድ ሰብሳቢ
#4 • የፀረ -ሙስና ብሔራዊ ጥምረት ሊቀመንበር
#5 • የብሮድካስቲንግ የቦርድ ሰብሳቢ
#6 • የፍትህ እና የህግ ኢንስቲትዩት የቦርድ አባል
#7 • የፍትህ ማሻሻያ ፕሮግራም የቦርድ አባል
#8• በፌዴራል የፍትህ እና አስተዳደር ካውንስል የፓርላማ ዋና ተወካይ
#9• የኢትዬጲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚ አባል
#10• የኢትዬ ቻይና ወዳጅነት ሊቀመንበር
#11• የኢትዬጲያ ፓር ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር
#12• የትግራይ አካል ጉዳተኞች (TDVA) ፕሬዝዳንት
የቀድሞ ስልጣናቸውን ልጨምርበት፣
#1• የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ክላስተር ዋና አማካሪ
#2• የአፍሪካ እርስ በርስ መገማገሚያ (African peer Review) የባርድ አባል
#3• የፓርላማ የፍትህና የህግ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
#4• የኢትዬ – እንግሊዝ የፓርላማ ግንኙነት ሊቀመንበር
በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የተሰጣቸው ስልጣን፣
#1• ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን ድርድር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መምራት
#2• በፌዴራል የሚመደቡ ዳኞች ከደህንነት ፅህፈት ቤት ጋር በመሆን ማፅደቅ


