ጲላጦስ አምላኩንና አጋሩን ክርስቶስ ዶሮ ሳትጮህ ሦስት ጊዜ ያስካደው እራሱን ከክርስቶስ በላይ በመውደዱ ነው። ኦዴግ (ODF) የአንድነት ጎራውን የካደው መካድ ባህሉ ባደረገው በለመደ አንጀቱ ነው። ጲላጦስ መካድን የተለማመደው በክርስቶስ፤ ኦዴግም በሃገሩ ኢትዮጵያ ላይ ነው።ስፕሪት ሣይንስ ላይ ” ከሃዲዎች በጠባቡ መተላለፊያቸው ላይ ሲያስቀምጡህ ታውረህ ማየት ስለተሳነህ ለራስህ ይቅርታ ልታደርግለት ይገባል” [“Forgive yourself for the blindness that put you in the path of those who betrayed you” (Sprit Science)] የሚል ሠፍሯል።
እውቁም አሜሪካዊ የትያትር ፀሃፊና ደራሲ ስቴቨን ዲዝ “ከህደት ተስፋን በፈቃደኝነት ማረድ ነው [“Betrayal, though … betrayal is the willful slaughter of hope]” በማለት ይገልፀዋል።
ለመሆኑ ኦዲግ (ODF) ማነው?
ኦዲግ ‘የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር’ ምህፃረ ቃል ነው። ባጭሩ ኦዴግ የ”ኦነግ ወይም ኦህዴድ” ቅፅል ስም ነው (synonym)።
የህወሃትና ኦዴግ ፖለቲካዊ ቁማርና ጥሎሽ-አልባ ፍጥምጥም!
<የምር ተኳሹን እኛ ስናውቀው፣
ድንጉጡን “ኦዴግ” ማን ደባለቀው::>
1. ጥንሥሠ ፅድቅ
ፈጣሪ መጀመሪያ እራሱ ቀጥሎም መሬትንና መንግስተ-ሰማይትን በመቀጠልም ውሐን ሠራ:: ይህ የፅድቅ ፍጥረት ጥንስስም ነበር:: ክርስቶስም ልጁ በጊዜ ተከሠተ:: የክርስቶስ ልጁም ዝና ቀጥሎ ገነነ:: ጠላቶቹም አበሩ:: በፈታኝ ሠዐት ላይ ወዳጁ ጴጥሮስም ካደው::
2. ጥንሥሠ ዲያቢሎስ
መጀመሪያ ሻዕቢያ (EPLF) በ1962 ዓ.ም እራሱን ከጀበሃ (ELF) ነጠለና በራሱ ቆመ:: ሻዕቢያ በ1965 ዓ.ም ኦነግን ገነባ:: ሊገራውና ሊያግደውም ቃል ገባ። በመቀጠልም ህወሃትን በ1967 ዓ.ም ጠፍጥፎ በራሱ ቅርፅ ሠራው:: ይህ ክህደትን መሠረት ያደረገ የዲያቢሎስ ጥምር ፍጥረት ቀንም ነበር:: ወያኔም ስልጣን ያዘ:: ለጥቆም ሻዕቢያና ወያኔም ኦነግን ካዱት:: ክህደት ባህላቸው ነውና ወያኔ እንደገና ሲፈረጥም ሻዕቢያን መልሶ ካደው::
ህወሃትም ለቀጣዩ የህዝብ ግድያና ማፈናቀል ያሰለጠነውን ኦነግንና አራጆቹን ድጋፍና የበደኖ፣ የአርባ ጉጉን ጭፍጨፋ መሃንዲሶች ልምድ ፈለገ:: ካራውንም አዘጋጀ:: በ2010 ዓ.ም ወያኔ እንደ መሪው ሌንጮ (ዮሐንስ) ለታ ስሙን ከኦነግ ወደ ኦዴግ የቀየረውን የኦነግ ሚስጥራዊ ደብዳቤን መልሶ ጠራው:: ሙዳ ስጋ በህወሃት እጅ ያየው ኦዴግም አላንገራገረም:: ላየው አጥንት ለሃጩን እያዝረከረከ ተጠጋው። ኦዴግም ወደ ህወሃት ገሃነም በአጋርነት ለማገልገል በፈቃዱ ተመለሰ:: ዳግምም እጅ ሰጠ::
የህወሃትና ኦዴግ ጨዋታ ገና ይቀጥላል!
ይህን እናስተውል! ከኦዴግና ህወሃት ህብረት ጀርባ ሤራ አለ።
(‘መካድ የለመድ እናቱን ይክዳል!’)
ኦዴግ ከነባሩ ኦነግ ተገነጠልን በሚሉ የኦነግ አንጋፋ መሪዎች የተመሰረተ ድርጅትም ነው። ኦዴግና ኦነግ ከሚያለያያቸው ይልቅ የሚያስተሳስራቸው ጉዳይ የበዛ እንደኔም ግምት አንዱ ለሌላው የእህት ድርጅት (sister or affilated company) ነው።
“ኦነግና ኦዴግ” በሁለት ስም አንድን ተልዕኮ ለማሣካት በሽፋን ወይም በጭንብል ይንቀሣቀሳሉ ( Camoflaged or Concealment by means of disguise)። ኦዴግ በሃሰት ሰንደቅ (false flag) ነባሩን የኦነግ ዓላማ ለማስፈፀም “በህጋዊነትና በሰላማዊ ትግል” ሽፋን በተቃዋሚ ወይም መንግስት ውስጥ ሠርጎ በመግባት ጥንት የደነቆረበትንና ሆያ ሆዬ ሲል የሚኖርበትን የኦሮሞን ሪፑብሊክ ቅዠቱን ለማሳካት የሚፍጨረጨር ነውም።
“ኦነግ፣ ኦዴግና ኦህዴድ” የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፆች ናቸው። አንድም ሦስትም ናቸው።
1. እንደ ሴተኛ አዳሪ የከፈለ ሁሉ እጃቸውን ጠምዝዞ ይዟቸው የሚሄድና ለትርፍራፊ ትላንትም ይሁን ዛሬ እራሳቸውንና የህዝብ ትግልና መስዋዕቶችን እየከዱ የሚሄዱ የቦይ ውሐዎች ናቸው::
2. ብዙዎቹ የ”ኦነግና ኦዴግ” አባላት ‘በቀይ ሽብር’ ጊዜም የአምባገነኖች ጉዋንት (gloves) የመሆን ልምድና ህዝባዊ መነሳሳትን ማጨናገፍና ህዝባዊውን ትግል በመሰላልነት በመጠቀም የፖለቲካ ስልጣን መፈለግ 50+አመታት ያካበቱት ልምድም ነው። በደርግ ዘመንም ከደርግ ጋር በማበር ንፁሃን ወጣቶችን ሲፈጁና ሲያስፈጁ ነበር። ከአምባገነኖች ጋር የመጋባት ባህል አዳብረዋል።
3. በበደኖና በአርባ ጉጉ ላይ በ1993 ዓ.ም ከህወሃት ጋር በጋራ ተሰልፈው ንፁሃንን ገደል የጨመሩና በአሰቃቂ ጭካኔ የገደሉም ናቸው። በንፁሃን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት ያደረጉ እጃቸው ላይ የህዝብ ደም ያለ ነብሰ ገዳዬችም ናቸው።
4. “ኦነግ ወይም ኦዴግና ” የኦሮምኛ ተናጋሪ ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች ጥርቅም እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ማለት አይደሉም። የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና የኢትዮጵያም የጋራ ባለድርሻ ነው። ከኦሮሞ ህዝብ ከ60-65% በላይ የሚሆነው ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ጋር የተደባለቀ ነው። “ኦነግ ወይም ኦዴግ ” የኦሮሞን ህዝብ ከወገኖቹ ኢትዮጵያውያን ለመለየት የኦሮሞን ህዝብ ይሁንታ/mandate/ ያላገኙ በበታችነት ስሜት በተወጠሩ ግለሰቦች የሚመሯቸው ዱዳ ድርጅቶች ናቸው።
በድምሩ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ” ከህወሃት የሚለዩ ሣይሆን “ኦነግ ወይም ኦዴግ ” ህወሃት፤ ህወሃትም “ኦነግ ወይም ኦዴግ ” ነው። ይህም አንድነታቸው በዚህ ይገለፃል።
1. ሁለቱም የሚተኙት በአንድ አልጋ፣ የሚያልሙት አንድ ዓይነት ህልም ነው። ሁለቱ የሚጋጩት ብርድልብስ ሲጋፈፉና ህልሙን በየበኩላቸው ሲፈቱ ነው።
2. ሁለቱም በበታችነት ስሜት (inferiority complex) የሚሰቃዩና አስተሳሰባቸው ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት እንደነበሩም ሰዎች ነው።
3. ህወሃት አዞ ሲሆን፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ” የአዞውን ወያኔ ጥርስ በመፅዳት ተግባር ላይ የተሠማሩ ወፎችና (Egyptian plover bird) አዞው – ህወሃት የማይፈልገውን ትርፍራፊ ለቃሚ ናቸው (symbiotic relationship)። ጎጠኞቹ ለአዞው ህወሃት የኦሮሞ ልጆችን በቀለብነት እየማገዱ በማስበላት፤ ቅሪተ – አካላቸውን መልሰው ከአዞው ወያኔ ጥርስ ይለቅማሉ። ይበላሉ።
4. ህወሃት ስልጣንን የሚፈልገው የኢኮኖሚ የበላይነቱንና ልዕልናውን ማስጠበቂያነት ሲሆን፤ ጎጠኞቹ የህወሃትን ኢኮኖሚና ፓለቲካ በሹመኛነት ማስተዳደር ብቻ ነው።
5. የሁለቱም የጋራ ሃይማኖት “የጎሣ ፌደራሊዝም” ሆኖ የሚፈልጉትም ይህንኑ ሃይማኖት ማስቀጠል ነው። የሃይማኖቱ መሪ “ጳጳስ” ህወሃት ነው። “የጎሣ ፌደራሊዝም” ሰዎችን እንደከብት በጋራ ስም የሚነዳና የሚጠራ፤ የፓለቲካ ስትራቴጂው በቂምና በበቀል ላይ ያደረገና የግለሰቦችን ነፃ የማሠብ መብት የሚገፍ የሠው ለምድ በለበሱ እንሠሦች የሚቀነቀን ጠንቀኛ የፓለቲካ ሥርዐት ነው። በዲሞክራሲ ስም ዲሞክራሲያዊ ባህልን የሚዋጋ በበታችነት ስሜት ለሚንገላቱ ህዳጣን እንደ ፍቱን መድሃኒት ሙጥኝ የሚሉበትና ወደ ስልጣን የሚረምማመዱበት የደካሞች ከዘራ ነው። ሁለቱም ማለትም ህወሃት “የጎሣ ፌደራሊዝም” መሃንዲስ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ግንበኞች ናቸው።
6. ሁለቱም ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አይፈልጉም። ምክንያቱም ህወሃት በሥነ-ህዝብ ቁጥር አናሣ (dominant & demographic minority) ስለሆነና ጎጠኞቹም የቁጥር ብዙሃን (numerical majority) እንጂ ዴሞክራሲያዊ ብዙሃን (democratic majority) ባለመሆናቸውም ጭምር ነው።
7. ሁለቱም በየፊናቸው የሚባክኑት ለጥገና ለውጥ ነው።
8. ሁለቱም በልዩነት ውስጥ ባላቸው አንድነት የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን እንዳይቀናጅ እንቅፋትም ናቸው። ሁለቱም ኢትዮጵያን የማፍረስ የጋራ አጀንዳም አላቸው።
9. ህወሃት እስካለ “ኦነግ ወይም ኦዴግና ኦህዴድ” በፓለቲካው ምህዳር ላይ ውር ውር ይላሉ። አዞውን ወያኔ እስካልተዳፈሩ። “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ኖሩም አልኖሩም ህወሃት ይኖራል። ህወሃት አዞው የጎጠኞቹ የሆድ አምላክ፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” የአዞው ጥርስ በመሣልና በማፅዳት የተሰማሩ ለትርፍራፊ ያደሩ ወፎችም ናቸው። ለዚህም ነው እነኝህ ኦሮሞ የጎሣ ፓለቲከኞች ከፓለቲካዊ ስርዐት ለውጥ ይልቅ በአዞው ህወሃት ስር ለፓለቲካ ስልጣን የሚፈልጉት።
10. “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ ወይም ህወሃት” በንፁሃን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት ያደረጉ እጃቸው ላይ የህዝብ ደም ያለ ነብሰ ገዳዬችም ናቸው።
11. ኢትዮጵያን እንደ አንበጣ መንጋ ወሮ፤ ኢትዮጵያዊያንን በቋንቋ የፌደራሊዝም ክልል ሸንሽኖ አፓርታዲያዊ የፖሊቲካ ስርዓትን መስርቶ ኢትዮጵያን በግፍ የሚገዛ የህወሃት ወራሪ ሃይል ነው። ይህ ስርዓት ከተፈጥሮው ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱም ከጣሊያን ባለሟሎቹ በተቀዳ ስልትና እቅድ የሚመራ ነው። ይህ ሃይል መገርሰስ የሚቻለው በኢትዮጵያዊያን የተቀነባበረና የተቀናጀ ትግል ብቻ ነው። ይህ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ትግል ያጋጠመው እንቅፋት የህወሃት ህዝባዊ ድጋፍ መሠረት ሣይሆን፤ ኦነግ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት መሰለፉና በተዘዋዋሪ ለህወሃት ጥንካሬና የእድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ሆኖ መገኘቱ ነው።
ኦነግና ህወሃት በጋራ የሚያመሳስላቸው ሁለቱም ፀረ-ኢትዮጵያ መሆናቸው ነው።
የአንድነት ጎራው መርዶ!
አሜሪካዊው ፀሃፊ ፊሊፕ ኬ. ዲክ (Flow My Tears, the Policeman Said) በተሰኘው መፅሃፉ ” የተካዱ እውነታዎች ተመልሰው በመምጣት ያጠምዱናል (Reality denied comes back to haunt.)” ይለናል።
በተለይ ተቀማጭነቱን አስመራ ያደረገው ግንቦት 7 ምንም እንኩዋን በኢትዮጵያ አንድነት ስም ቢንቀሣቀስም “አንድነቱን” የፈጠረው ከፀረ-አንድነትና ከፀረ-ኢትዬጵያ ሃይሎች ጋር ነው። ለዚህም ኦዴግ፣ ትህዴንና ሲአን (የሲዳማ ነፃ አውጪ ግንባር) ናቸው። ሲአንም በደርግ ዘመን የደርግ ልዩ ሃይል ሆኖ ወጣቶችን ሲረሽንና ሲያስረሽን የነበረ ነው። ይህም የፓለቲካ ተቀናቃኞችን በማሰባሰብ አፍራሽ ተግባር ለማረቅ በሚል ይመስላል። ትልቅ ፓለቲካዊ ኪሣራውም ከጠላቶቹ ወዳጆች (ኦዴግ) ጋር ጠላት ወያኔን መፋለም ማለሙ ነው። የነርሱንም እኩይ “የጎሣ ፌደራሊዝም” ፀረ-ዴሞክራሲ መሆኑን እያወቀ ማበሩ ነው። በፓለቲካዊ ቁማር ህዝባዊ ስልጣንን እተገብራለሁ ብሎ መንቀሣቀሱም ነው። ይኸው ከአጋሮቹ አንዱ ኦዴግ ጭራሽ የትጥቅ ትግሉን አወገዘለት። ግልፅ የሆነ የአንድነት ፕሮግራም የሚነሣው ያለምንም የፓለቲካ አድርባይነት ጠላትንና ወዳጅን ለይቶ በማውጣት ነው። ይህን ለማረም ድርጅቱ ያለውን ፈቃደኛነት ባላውቅም መንገዱ የገደል መንገድ ነውና ጭራሹን አያዋጣውም።
ለማስታወስ ያህል ይህ የዛሬው ኦዴግ የትላንቱና የአሁነም ኦነግ ከህወሃት ጋር ግንባር ፈጥሮ ቀጥሎም በሐረር ሲዋጋ OLF 1973 ምስረታው ዓላማ የሻዕቢያ ኮንዶም አጥልቆ፣ ርዕዮተዓለማዊና ወታደራዊ ትጥቁ የሆነው ሻዕቢያ ስለከዳውና ከወያኔ ጋር በማበሩ ለወያኔ 20ሺ ጦር በ30 ደቂቃ ገብሮ እስዬ አብርሃ “ጦርነት ለማንም አይበጅም:: ጦርነት እንኳን ለኦነግ ለህወሃትም አይበጅም” ብሎ እንደተሳለቀበትና እንዳላገጠበት ትዝ ይለናል (fresh memory)። አላገጠባቸው:: የማይታመኑ ሃይሎችን ማመን በራሱ እራስን ማጥፋትም ነው።
«ህወሃት “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ሀወሃት ነው። ህወሃት ያለ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ያለ ሀወሃት አይኖሩም። አልኖሩምም!!»
አክራሪ ብሄረተኝነት ለህብረ-ብሄራዊነት ጠንቅ ነው። “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ህወሃት ለጋራ አላማ የሚሰሩ ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ናቸው። በሁለቱ መካከል የታክቲክ እንጂ የስትራቴጂ ልዩነት የለም።
ህወሃት ያለ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ”፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ያለ ሀወሃት አይኖሩም። አልኖሩምም። አንዱ ያለሌላው ስለማይኖርና ኢትዮጵያን በማፍረስ ተግባር የተሰማሩ በመሆኑ ሁለቱንም በጋራ ታግሎ መጣል የወቅቱ ጥያቄ ነው። አንዱን ከሌላው በቀዶ ጥገና ዘዴ ለይቶ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ» በሚል የፖለቲካ ቧልት መጃጃል ክስረት ብቻ ነው።
ህወሃት “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ፤ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ሀወሃት ነው። ኢትዮጵያን ማዳን የምንችለው እነዚህን “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” የተሰኙትን ጣምራ ጠላቶች በጋራ ስንታገል ብቻ ነው። ጊዜው የሚጠይቀው ለኢትዮጵያዊ ሃይሎች የማይሰራና ወቅቱ ያራከሰውን ፖለቲካዊ ስሌት በመተው በጋራ ተነስተው እነዚህን ጠላቶች በጋራ ተፋልመው የጋራ ሃገራቸው ኢትዮጵያን መታደጉ ነው። በሃገር አቀፍ ስሌት የተዋቀሩም ድርጅቶች አቁዋማቸውን ገምግመው ለህዝቡ የማሣወቂያ ጊዜ አሁን ብቻ ነው። በመንታ መንገድ ላይ የምትገኘውን አገራችንን የምንታደግበትና ለአንድነቷ በጋራ የምንቆምበት ብቸኛው ወቅትም አሁን ነው።
ለማጠቃለልም ይህ እንደ ወረርሽኝ ደጋግሞ የሚከሠተው “የህወሃት ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ጥምረት ጊዚያዊና የእንቡዋይ ካብ ቢሆንም እንደቀድሞው “በፀረ-አማራነት” ላይ የሚቃጣ ትብብር የሚሆን ስለሚችል ይህን የነብሰ ገዳዮች ጥምር ለመመከት አማራው በንቃት መከታተልና መመከት ይገባዋል። አማራ ኢትዮጵያን ከወራሪዎች ማዳን የቻለው እራሱን አደራጅቶና ሌሎች ኢትዮጽያውያንን አስተባብሮ ነው። “ህወሀት፣ ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ሲነፃፀሩ ህወሃት ልክ እንደ ጣሊያን፣ “ኦነግ ወይም ኦዴግ ወይም ኦህዴድ” ደግሞ ልክ እንደ ጥንቱ የወያኔ ባንዳዎች ናቸው። የጋራ ጠላቶቻችንም ናቸውና በጋራ እንፋለማቸው።
[“የጎሣ ፌደራሊዝምን” እና የወያኔን አፓርታይድ ስርዐት በጠላትነት ያልፈረጀ የአንድነት ትግል በራሱ ልዩነት ነው]
[‘ግራ የገባው ኢትዮጵያዊው ፓለቲካና ፓለቲከኞቻችን’]
[ሞት “ለጎሣ ፌደራሊዝም”]
