~ ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ለኢሕአዴግ በሰጠው ምላሽ በኢትዮጵያ እውነተኛ ውይይትና ድርድር እንዲካሄድ ፣ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ፍላጎት እንዳለው ገልጿል ፤
.
~ ሆኖም ግን በድርድሩ ሂደት ነጻና ገለልተኛ አስማሚ ወይም አደራዳሪ እንዲኖር ሰማያዊ ፓርቲ በዋነኛነት ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል ፤
.
~ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ድርድሩ አግላይ ያልሆነ ሁሉን አቀፍ የሆነ፣ በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙትንም እንዲጨምር ሰማያዊ ፓርቲ ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል ፤
.
~ ሊደረገው የታቀደው ድርድር በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልና መሰዋዕትነት የተገኘ እንደሆነ እና ድርድሩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወሳኝ ጥያቄዎችን የሚመልስ መሆን አለበት ብሏል።

