
እድሜ ለነ በረከት ሰምኦን እንጅ ብአዴን ለአማራ የሚቆረቆር ሰው ትምኪተኛ እና ነፍጠኛ ብሎ ማባረር ቁጥር አንድ ተግባሩ አድርጎ ይዞታል ከ20 አመታት በላይ አስቆጥሯል። ታሪክ ባንድ ሰው ሊቀየር አንድ መነፀር አይኑ ላይ የደረነቀ ሰው ባልታሰበ ጊዜ ከፊት መስመር ተሰለፈ የአማራ ኘሬዝዳንት ሆነ። ህገ ወጥ መሳሪያ ህጋዊ አድርጎ ፈቀደ በህዋቶች ዛቻ፣ግምገማ፣ጥላቻ በየዓይነቱ ተደረደረበት እራስህን ጀኔራል አድርገህ ሹመሀል ተባለ አወ እኔ የአማራ ጀኔራል ነኝ አለ። #ትምኪተኛ ተባለ ህገወጥ መሳሪያ ህጋዊ ማድረግ ትምኪት ከሆነ አወ ትምኪተኛ ነኝ አለ። ከህዋቶቹ አባይ ወልዱ፣አባይ ፀሀየ፣ዶ/ር ደብረፅዮን ጀምሮ እስከ ስምኦን ልጅ አቶ በረከት ጣት ተቀሰረበት ሰውየው የአማራው እንባ አባሽ ፊት አውራሪው #ገዱ_አንዳርጋቸው ነው።
*ይህ ሰው የሚናገረው እዩኝ እዪኝ የሚል ዓይነት አይደለም ላመነበት ግን ወይ ፍንክች።
ህውሀት አማራ ነቃብኝ ብላ ገዱን ለማንበርከክ ብትሞክርም #የሽሮ_ድንፍታ ሆና ቀረች። አጅሬ ገዱ ለአማራ ሲል በይፍ ህውሀት ጋር ፊት ለፊት መፋጠጥ ጀመረ።
#ገዱን ለማንበርከክ እነእንቶኔ በቅማንት የማንነት ጥያቄ ጭምብል ለብሰው ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ የፓለቲካ ቁማሩን ቢጀምሩም ፈፅሞ መደንገጥ አይታይበትም ሰውየው–ፕሬዚደንት ገዱ ነው። ነገሩ በጠበቁት ልክ ውሀ አላነሳላቸውም አማራ ከዳር እስከ ዳር ተማምሎ በገዱ ድርድር የለም አለ።
#ገዱ ነገረ-ስራው ሁሉ አይነኬ ሆነባቸው ሰውየው በአማራነቱ ይኮራል፤በኢትዮጵያዊነቱ ይመካል። ከመገላመጥ ብዛት የተነሳ #ለህውሀትና_ለበረከት ከሚያጎበድዱት የብአዴን ፖለቲከኞች በተለየ ዓይኑን ነገ ላይ ያነጣጠረ የአማራ ባለራዕይ መሪ ነው። በመላኩ ፈንታ መታሰር ለምን ብሎ የተንገበገበ ከዛም ከሃያ በላይ የቤት ካርታ በስሙ የተገኘበትን የጉምሩኩን ቅልብ አቶ ገብረዋድ እንዲጠየቅ ያደረገ ቆስጣና መሪ ነው።
* በነ አባይ ወልዱ አጠራር ጀኔራል ገዱ በሚል ቅደጥያ መጠሪያ ስም ተሰቶታል።
ገዱ ከገብርየ ጀግንነትን ያነሳ፣ከቴድሮስ ወንድነት የተሸለመ፣ ከንጉስ_ሚካኤል ፍቅርን ጀባ የተባለ፣እንደ በላይ_ዘለቀ ለስልጣን የማያጎበድድ አይበገሬ የአማራ ልጅ ነው!(ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ለስልጣን የማይቋምጥ አንዴ እናቴ በላይ ብላኝ አለች አይደል ያለ።)
ጨዋታው ተጋግሎ የኢህአዴግ ምክርቤት ደረሰ ገዱ ላይ ትምኪተኛ የምትባል ኳስ ተቀባበሉበት ያኔ የጎንደሩ ግልገል ዶ/ር አምባቸው ፖለቲካን ያለጠመንጃ፣በሀሳብ የበላይነት ተቆጣጠረው።
ገዱ አንበሳ ሆኖ መቀሌወች ኮስመነው ወጡ ዓመቱ #ጎንደርና_ጎጃም አሻፈረኝ ያለበት ዓመት ነበር። ከዛማ አማራወች ከተዳፈኑበት አፈራቸውን እያራገፋ ለአማራ ጥቅም ትግሉን መጋፈጥ ጀመሩ። #ወሎየወችወልዲያ፣ቆቦ እና መርሳ ላይ ቀወጡት ውድ ህይወታቸውን ያብርሀም በግ በማድረግ ለውጥ እንፈልገለን በማለት ብአዴንን ከእንቅልፉ ቀሰቀሱት። እነ በረከት እንደ ድሮው ብአዴን መስሏቸው ገዱን ለማውረድ ወደ ባህርዳር አመሩ እንዳሰቡት ሳይሆን ውርዴትን ተከናንበው ተመለሱ። በሀሳብ ሲበለጥ ዋንጫ እንደተቀማ የአውሮፓ ሻምፒዮን ሊግ ተጫወች ማልቀስ የለመደው #የሰምኦን_ልጅ_በረከት ልቅሶው ተነቃበት። ፀጋ አራጌ እንዳለው ከፊት የበቀለች ጆሮ ከኋላ በበቀለች ቀንድ ትበለጥአለች ነው እና ነገሩ የአሁኑ ብዓዴን ስብስብ የድሮውን የነበረከት፣አዲሱ፣ታደሰ፣ካሳ፣ ህላዊ፣አለምነው ቡድን ተረት አደረጋቸው።
*#ፊት_አውራሪው_ኘሬድዛንት_ገዱ_አንዳርጋቸው ለነ ኦቦ ለማ መገርሳ እና ዶ/ር አብይ አህመድ ከህውሀት የመጋፈጥንና ለህዝብ የመኖርን እርሾ አበድሮ ለጠቅላይ ሚኒስተርነት አበቃቸው።
*ገዱ አማራን ከሩብ ክፍለ-ዘመን እስር መፍታት የሚችል ጎበዝ ይመስላል። ይህ ሰው ለእኔ ለአማራ በመከራ ሰዓት የተሰጣት ጋሻዋ ይመስለኛል።ከየአቅጣጫው የሚወረወርበት ጦርም ይታይኛል።ይሁንና ከልዩነታችንና ከጥላቻችን ባሻገር የሰላም አየር ወደ ሚነፍስባት ኢትዮጵያ ሊወስደን የተነሳ ነውና ገዱን እናዳምጠው፤እንከተለው።
የዳውንቱ ፈርጥ የአንዳርጋቸው ልጅ ገዱ ከራሴ ይልቅ አማራን የሚል ዕውነቱ ህውሀትን ያስፈራቸዋል። ” #የፈሩት ይደርሳል #የናቁት ይወርሳል” እንዲሉ ከብአዴን ተፈልፍሎ ህውሀትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያንገራገረ፣ በረከትን የገለመጠው ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ላይ ብዙ ለአማራ የሚቆረቆሩ መሪወች እየፈጠረ ነው #ዶ/ር #አምባቸው፣ #ንጉሱ ጥላሁን፣#እዘዝ ዋሴ፣#ፀጋ አራጌ፣#ላቀ አያሌው፣#ጌታቸው ጀምበሬ እና ሌሎችም አፍርቷል።
ገዱ አንዳርጋቸው የፊት መስመር አጥቂ ሆኖ ከሌሎች የብአዴን መሪወች ጋር በመሆን ዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሆኖ እንዲመረጥ የአንበሳ ድርሻ ተወቷል። ኦቦ ለማ እና ዶ/ር አብይ የአብነት መምህረቸው ገዱ መሆኑን አንድ ቀን ይመሰክሩ ይሆናል። #ታዲያ_ገዱን_አለማድነቅ_ይቻላንን?
#ገዱን ሳታደንቅ ለአማራ የሚቆረቆር መሪ መፈለግ #ሰማይ #ለመቧጨር_የመፈለግ_ያህል_እብደት ነው! ያለነን በመደገፍ እና በማረም #ብአዴንን እንደ ኦህዴድ የብረት ግድግዳ ማድረግ የሁላችንም ድርሻ ነው? በመጨረሻም
መንግስቱ ዘገየ ለገዱ የገጠማትን ጀባ ብየአለሁ:-
”ይወድቃል እያሉ ሲገፉ ሲገፋ
የብረት ግድግዳ አርገውት አረፉ!”
ዘሬ ከአማራ ደሜ ከቅዱሱ ቦታ ከአሸተን ማሪያም ግርጌ ላስታ ምድር ይቀዳል!!
