
ከአንድ ሳምንት በፊት ESFNA ዝግጅቱን ሊያደርግ ባቀደበት ቦታ አቅራቢያ ካለ ሆቴል ሪዘርቬሽን ይዣለሁ። መልካም ጊዜ ከመላዉ ሀገር አፍቃሪ ጋር እንደሚኖረኝ በመገመት በጉጉት እየጠበኩ ነዉ። እድለኛ ከሆንኩም ጀግናዉን እስክንድር….. ማንያዉቃል መሪዬን አንዳርጋቸዉንም እመለከት ይሆናል ……ቴዲም አይጠፋም. ይሁን እና ESFNA እርሶን ይምጡ ብሎ ቢወሰን ግን እኔ እቅዴን እሰርዛለሁ። በእርሶ ላይ ቂም የለኝም ….ይልቁንም አክብሮት!!…ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ወዳጅ የሚያሰኘን በቂ ትስስር የለንም።
ዶር አብይ
ዛሬም በወታደራዊ አገዛዝ ስር ነን
ዛሬም አዜብ መስፍን የምትፈነጭበት ሀገር ነዉ ያለን
ዛሬም በርካቶችን በሌሉበት በወነጀለ አምባገነን ስርሃት ውስጥ ነን
ዛሬም አባይ ፀሐዬና ደብረሴይጣን የፈለጉትን የሚሆኑበት ሀገር ነዉ ያለን
ዛሬም ዶ/ር ብርሃኑ በርሃ ነዉ
ዛሬም ወታደራዊ መሪዉ ባብዛኛዉ ወያኔ ነዉ
ዛሬም ፋናና ሪፖርተር የሚፈነጭባት ሀገር ነዉ ያለን
ዛሬም ዜጎች በእብሪተኛዉ ወያኔ የሚንገላቱባት ሀገር ላይ ነን
ዛሬም የሀገራችን ኢምባሲዎች በአንድ ዘር ተሞልተዉ እኛን አይመስሉም
ወዘተ ወዘተ……
ስለዚህ ESFNA እርሶን ጋበዘ ማለት ይህን ሁሉ መርሳት በመሆኑ በፍፁም አልቀበለዉም። ስለዚህ ማስጠንቀቂዬ ለ ESFNA ይድረስ። ጊዜው ገና ነዉ። አበቃ!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር።
መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)
