ከታምራት ይገዙ

ጉዳዩ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ አሊን በዳላስ 2018 ዝግጅት ላይ መጋበዝን ይመለከታል።

በሴሜን አሜሪካ የተመሰረተው የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽኑ ላለፉት 35 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን በሰሜን አሜርካ በማቀራረብና የሀገራዊ አንድነትን መንፈስ በስፓርትና በባህል ፌስቲቫል በማክበር ያሳየው ታታሪነትና ጽናት በዲያስፓራ አሉ ከሚባሉ የኢትዮጵያውያን ተቋማት አንዱ እንዲሆን አድርጎታል። በነዚህ 35 ዓመታት ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ያለፈው ፌደሬሽናችን የዲያስፓራ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ጭምር ትልቅ ኩራት ነው የሚል እምነት አለኝ::

የወቅቱ የአገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ ዳላስ በሚደረገው አመታዊው የኢትዮጵያዉያን እግር ኳስ ውድድር ላይ ለመገኘትና ንግግር ለማድረግ  ጥሪ እንዳቀረቡና የፌዲሬሽኑም የቦርድ አባላት በጉዳዩ ላይ እየተነጋገሩ እንደሆነ ሰምተናል።  በሌላ በኩልም  በመላው ዓለም የሚኖረውም ኢትዮጵያዊ ይህ ጉዳይ ያገባኛል በማለት እየተነጋገረበት ይገኛል ይህም ይበል የሚያስብል ነው::

እኔም በዋሽንግተን  ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ለኢትዮጵያውያን የስፓርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ የቦርድ አባላት የማቀርበው ጥያቄ እነንት ሁለት ክፍሎች ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሚመጡበትን መንገድ እንድታመቻቹ  ቅንነት; ተጠያቂንተንና ሃላፊነትን በመቀበል እንድትሰሩ አበክሬ እጠይቃለው::

እግረ መንገዴንም ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመደ በሚመጡበትም ግዜ የሚከተሉትን ቢያደርጉ በውጪ ባለነው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የበለጠ ተቀባይነትን ያገኛሉ የሚል የግል እምነት ስላለኝ እንደ ሀሳብ አቀርባለው ያ ማለት ግን ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጤ እንዳልሆነ በትህትና እገልጻለው:: በኔ እምነት ጠ/ሚ አብይ አህመደ ሲመጡ በኢትዮጵያ ቀን ለመላው ኢትዮጵያዊ ንግግር ካደረጉ ቦሃላ   በውጪ የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች የሚወክሉ  የህዝብ ተወካዮች በአዳራሽ ውስጥ ሰብስበው እንዲያናገሩ በኢትዮጵያዊነት ባህላችን ከወገቤ ጎንበስ ብዮ እጠይቃለው::

ይህንን ጥያቄ የምጠይቀው ከምንም ተነስቼ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተለያየ የሚዲያ ተቆማት እንደተከታተለው ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአገር ውስጥ እየዞሮ ህዝብን በስታዲዮም አሊያም በአደባባዮች  ሰብስበው ንግግር ካደረጉ ቦሃላ የአካባቢውን ህዝብ የሚወክሉትን በተለየ ቦታ በአዳራሽ ውስጥ እየሰበሰቡ የጥያቄና መልስ ውይይት እንዳደረጉ አይተናል ሰምተናል ያ በአገራችን ውስጥ ያደረጉትን አይነት የጥያቄና የመልስ ውይይት አሜሪካንም ሲመጡ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያውያን የስፓርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ የቦርድ አባላት ለጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ጥያቄ አቅርበው ሁኔታውንም በየግዜው እየተከታተሉ ለህዝብ እንዲቀርቡ ሃላፊነት ወሰደው ከልባቸው እንዲሰሩ በትህትና እጠይቃለው::

በመጨረሻም በኔ እምነት መጠራት ያለባቸውና እኛን በዊጪ ያለንን ኢትዮጵያኖችን የሚወክሉት ከዚህ በታች የምዘረዝራቸው ሲሆን የረሳዋቸው ካሉ ኮሚቴው  ሊጨምራቸው ይችላል::

1ኛ በውጪ ያሉትን የተለያዩ ሐይማኖቶች መሪዎችና ተወካዮች

2ኛ በውጪ ያሉ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን የሚሉ የደርጅት መሪዎችና ተወካዮች

3ኛ በውጪ ያሉ መሳሪያ አንስተው በመሳሪያ ሃይል መንግስት እንለውጣለን  እንታገላለን የሚሉ የደርጅቶች መሪዎችና ተወካዮች

4ኛ በውጪ ያሉ የሰባዊ መፍት ተሞጞች  መሪዎችና ተወካዮች

5ኛ በውጪ ያሉ አክቲቭስቶች  ተወካዮች

6ኛ በውጪ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችና ሙህራኖች

7ኛ በውጪ ያሉ ወጣት ሴቶችና ወጣት ወንዶች ተወካዮች ወዘተ የሚገኙበት ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱ ተወካዮችን ለብቻ የሚያገኙበትን መንገድ ፈጥረው እንዲያነጋጉራቸው ማመቻቸት ከሁሉ ቅድሚያ ሊሰጠው ተግባር ነው ብዪ አምናለው ይህም ሲሆን ነው የጠ/ሚ አብይ አህመድ ህልም የሆነው በኢትዮጵያውያንን መካከል የተፈጠረውን መራራቅና መከፋፈል ማስወገድ ከዛም ከፍ ሲል የሰላም፣ የዕርቅና የአንድነት  ተግባሮች እውን ሆነው የሚወጡት የሚል ከፍተኛ እምነት አለኝ::

ስለሆነም  በዋሽንግተን  የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የፌደሬሽኑ ቦርድ እጅና ጎንት ሆነው ሰርተው ጠ/ሚ ዓብይን በ35ኛውን አመታዊ የስፓርትና የባህል ፌስቲቫል በዳላስ ቴክሳስ በእንግድነት እንዲጋበዙ በትህትና እጠይቃለሁ ::

ግልባጭ:      ለጠቅላይ ሚንስቴር ቢሮ

በአሜሪካና  ከአሜሪካ  ውጪ  ለምንኖር ኢዮጵያኖች በሙሉ

ዘመኑ  በአገራችን የሰላምና የፍቅር ብሎም የመተባበር  እንዲሆን የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁን አሜን!