እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው፡፡ አንዴ ሳያውቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ  ባለፈው የነደፈኝ ነገር በሎ መንገድ ላይ የተጠቀለለን እባብ በእጁ ነክቶ ለጓደኛ ሲያሳይ፡፡ ወያኔ የምትነድፈን ስንቴ ነው? የኢትዮጵያ ስፖረት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ምን እያደረገ እንደሆነ የገባችሁ ከአላችሁ በታብራሩት፡፡ ፌዴሬሽኑ እየሄደበት ያለው አካሄድ ግን ከኢትዮጵያውያን መብት አንጻር እጅግ አደገኛ እንደሆን ይሰማኛል፡፡ የአብይን በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ልገኝ የሚለውን ጥያቄ ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ለመወሰን ይረዳኝ ዘንድ በሚል የተከተለው ሂደት እኔን በእጅጉ አልተመቸኝም፡፡ ሕጋዊም አይመስለኝም፡፡ ከዚያም በላይ በውስጥ ለውስጥ ሸፍጥ እየተሰራ እንደሆነ የሚሸቱ ምልክቶች አሉ፡፡ ለማንኛውም የአብይን መገኘት ፈቀደም አልፈቀደም ለወያኔ ግብዓት የሚሆን ትልቅ ሥራ እየሰራ ነው ያለ የሚመስለኝ፡፡ ልብ በሉ ይህ ለዲያስፖራ ወይም ለሰሜን አሜሪክ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ይሁን የስፖርቱ አፍቃሪ ጉዳይ አደለም፡፡ ጉዳዩ በአገርና ሕዝብ ላይ የመጣ ትልቅ ሴራ እንጂ፡፡
እኔ አብይን በግሌ ከሚደግፉት ነኝ ግን የአብይ በዚህ ፌስቲቫል እንዲገኝ ጥያቄ የቀረበበት ሁኔታ በራሱ ጥያቄ ሆኖ በምንም መልኩ አብይ በዚህ ወቅት በሰሜን አሜሪካም ሆነ በአውሮፓ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ መገኘት የለበትም፡፡ ይህን አብራራለሁ፡፡ ግን ከዛ በፊት ጥያቄውን በራሱ እንደጥያቄ ላንሳው፡፡
እውን አብይ ራሱ አስቦ ነው ልገኝ ያለው ወይስ የወያኔው ኢመባሲ ጽ/ቤት? ሲጀምር አብይ በዚህ ጉባዔ ለመገኘት ፈልጎ ጥያቄ እንኳን ማቅረብ ቢኖርበት በቀጥታ በራሱ እንጂ በኢትዮጵያ ጠላት በሆነው በወያኔው ኢምባሲ በኩል አደለም፡፡ ይህም ሆኖ አብይ እዚህ መምጣት ፈላጎቱን በራሱ በምንሰማው አንደበት ለሕዝብ ይፋ ሊያደርገው ይገባል እንጂ በውስጥ ለውስጥ ጥያቄ ቀረበ ተብሎ ሕዝብን ለማወናበድ በየ ፌስቡኩ በሚነዛ ወሬ ባልሆነ ነበር፡፡ ያም ባይሆን የጥያቄው ደብዳቤ በይፋ ለሕዝብ በሚታይ መልኩ መለቀቅ ነበረበት፡፡ ይህ ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንጂ የፌዴሬሽኑም አደለም፡፡ የሰሜን አሜሪክ የሚኖር ብቻም ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይም ነው፡፡
ፌዴሬሽኑ ተጠይቄአለሁ ብሎ ያስወራል እንጂ ከእነአካቴውም ጥያቄ ላይቀርብለት ይችላል፡፡ ሴራው በራሱ ውስጥ በአሉ የተጠነሰሰ ነው የሚመስለው፡፡ በእርግጥ ነው ከወያኔው ኢንባሲ ጋር ተነጋግረው እናነተ ደብዳቤ ጻፉልን እኛ እናሰወራዋለን ብለው የወየኔውን ኢምባሲ ደብዳቤ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሕዝቤ ሆይ እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው ነው ነገሩ፡፡ እኛን ግነ ወያኔ ስንቴ ይነድፈናል፡፡
በጥቅሉ ይህ ጥያቄ ከአብይ ሳይሆን የመጣው ከራሱ በፌዴሬሽኑ በኃላፊነት ከአሉና ከወያኔው ኢመባሲ ጥምር ሴራ ነው፡፡  ይህም ባይሆን ፌዴሬሽኑ ከአብይ እንኳን ቀርቦለት ቢሆን የራሱን ሕገ-ደንብ ማክበር ግድ ይለው በነበረ፡፡ ጭራሽ የሕዝብ አስተያየት በሚል ድምጽ ማሰጠት ጀመረ፡፡ ሲጀምር የህን ድምጽ የሚቆጣጠረው አሁንም ግልጽ ያልሆነው ራሱ ፌዴሬሽኑ ነው፡፡ በብዙ አስተያየቶች እንደምናየው ሌላ ቀርቶ ራሰ ለድምጽ  ያወጣው ጥሪ ላይ ስናይ አብዛኛው ሰው የአብይን መምጣት እየደገፈ አደለም፡፡ ከዛም በላይ የሚነሱት አስተያየቶች በጣም በሳልና ትኩረት በሚገባቸው ወሳኝ ጉዳዮች ነው፡፡ ይህን የሚይ ታዛቢ በድምፁ አሰጣጡ ላይ የሚታየውን የቁጥር ልዩነት ይታዘባል፡፡  ፌዴሬሽኑና የወያኔው ኢምባሲ ለሚሰሩት ሴራ ደግሞ አብይ እንዳይመጣ የሚለው ቁጥር በልጦ እንዲታይ አይፈለግም፡፡ ይህ ወያኔ የለመደችውን ክህሎት ነው በፌዴሬሽኑ በኩል እየተጠቀመች ያለችው የሚል ትልቅ ስጋት አለኝ፡፡
ከላይ እንደጠቆምኩት እኔ ከአብይ ጋር ምንም ጸብ የለኝም፡፡ በእርግጥ ነው ከአብይ በላይ የማምናቸው ሰዎች አሉ፡፡ ለማና ቡድኑ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ በኦሮሚያ አልፎ እልፎም በገዱ ቡድን እየተደረገ ያለውን ትግል በማስተዋል ነው የምከታተለው፡፡ ከመስከረም በፊት ብዙዎች ጉዳዩን የምንከታትል ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ነበርን፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ስጋታችን የነበረው  ሕዝባችን ብዙ ይጎዳል እንጂ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚለው ሥጋት አልነበረንም፡፡ ወያኔ ለአንድ ሳምንት ሚዲያውን ሁሉ ዘግታ አብይ የተመረጠበትንም ሂደት ለእኔ ስጋት አልነበረም፡፡ አማራጭም እንደሌለ ብዙ የሚጠቁም ነገሮች ነበሩና፡፡ በዛ ላይ የበዓዴን ወኪሎች ከኦህዴድም ልቀው የተገኙበት ሂደት ነበር፡፡ ከኦሕዴድ በኩል ቀድሞውንም ቁርጠኝነቱ ግልጽ ነበር፡፡ የወሮበሎቹን የህዝብን የመግደልና የመዝረፍ አዋጅ እንዳይወጣ ከኦሕዴድ ተወካዮች ምን አልባትም ከአባ ዱላና ጥቂቶቹ በቀር በስብሰባው የተገኙት በሙሉ በመቃወም የሽብር አዋጁን ውድቅ እንዳደረጉት አይተናል፡፡ ይህ ብቻ አደለም ያ የፈጸሙት ገድል ቀጥሎ በሁሉም የፓርላማ አባል ከወያኔ በቀር ድፍረትንና ቁጭትን አሳድሯል፡፡ ያ ስብሰባ ከሳምንት በኋላ ቢደገም ከፅቂቶች ሆድ አደርና ዋናዎቹ ወያኔ በቀር በአብዛኛው ይቃወመው ነበር፡፡ ያም እንደሚሆን ስለታወቀ ነው ቁጥር ተሳሳተ ማለቱ ሳያንሳቸው ድጋሚ ፓርላማውን ሰብስበው እንደገና ድምጽ ከማሰጠት ይልቅ በወሮበሎነት ያወጁት፡፡ ይህ የኦህዴድ ፓርላማ አባላት የፈጠሩት ጀግንነት ነበር መጨረሻ ላይ ሙሉ በዓዴንና ኦህዴድ ድፍረት የሰጣቸውም ያስገደዳቸውና አብይ እንዲመረጥ ምክነያት የሆነው፡፡
ወያኔ ዛሬ የሚፈራው የለም፡፡ አረመኔና ወሮበላ እንደሆነ ዛሬ ሕዝብ በይፋ ተረድቶታል፡፡ እስከዛሬ እንደ ሕጋዊ አካል ስላየው ነበር ብዙ የተጎዳው፡፡ የሆነ ሆኖ አብይ በጣም በግሉ በሚያስብል ሁኔታ የሚያደርጋቸውን ጥረቶች እያደነቅሁ እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነትና እንደ መንግስት እስካሁን ድረስ ሊያሳየን የሚችለው ሥራ አልሰራም

እስረኞች ለቀቀ አዎ ግን የእስረኞች መለቀቅ የሕዝብ ፍቃድና ማስገደድ እንጂ የአብይ ይሁንታ በራሱ ያመጣው አደልም፡፡ በተለያየ ቦታ ያሉ ኢትዮጵያውያንን አስፈታ፡፡ አዎ ይህ መልካም ከሚያስብሉት የአብይ የግሉ የሥራ ውጤቱ ነው፡፡ በእርግጥ ጠ/ሚኒስቴርነቱን ተጠቅሞ ያደረገው ነው፡፡  እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነት ሕዝብ እየጠየቀ ያለውን አንዱንም አለፈጸመም፡፡

1.     ካቢኔ መሾም፡- ሕዝብ ለሕዝብ የወገኑ ሰዎች ወደ ሥልጣን ይመጣሉ ብሎ ሲጠብቅ ጭራሽ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ግለሰቦችን በካቢኔው አቆይቷል፡፡ ጡረታ በሚል ያገለላቸውን እንዳለ ሆኖ (ይህ ጥሩ እርምጃ ነበር ግን የተሾሙትስ)
2.    አስቸኳይ ጊዜ በሚል የወጣው ሕገወጡ አዋጅ አሁን ድረስ አልተነሳም፡፡ ሰዎችም እየተገደሉ ነው
3.    ሌሎች አፋኝ ሕጎች እንዳሉ ናቸው
4.    ስለምርጫ ለቅድመ ሆኔታ ፍንጭ እንኳን የሚሰጡ ሥራ የለም፡፡ ጭራሽ አስቸኳ ጊዜ አዋጅ በሚል ተፎካካሪዎች ከሕዝብ እንዳይገናኙ ተደርጓል፡፡ የኦፌኮው የነቀምት ሙከራ አስታውሱ፡፡
5.    ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነቱንና  ኢሕአዴግ የተባለን ሊውም ዩሕዝብ ጠላት የሆንን ቡድን ለማስተዋወቅ ይጠቀምበታል፡፡ አብይ ጠ/ሚኒስቴርነቱን ወክሎ በሚገኝባቸው ቦታዎች ስለኢሕዴግ ማውራት አይችልም፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩ ሥልጣን የመንግስት ሥልጣን እንጂ የቡድን ሥልጣን አደልም፡፡
ልብ በሉ እንደ ጠ/ሚኒስቴርነትና እንደመንግስት እነዚህ ከላይ የጠቆምኳቸውና የመሳሰሉ ሥራዎች ናቸው መሠራት ያለባቸው፡፡ ይህ ሁሉ በአለበት ዛሬ ሕዝብ ስለአስጨነቃቸው የሚፈቱን ታሳሪዎች እያየን እንወናበድ፡፡ የሕዝብ ደግንነት እንዲከበር መጀመሪያ በሕዝብ ላይ የታወጁ አዋጆች ይነሱ፡፡ ዛሬ ሲለቅ ያያችሁትን ነገር በዛው ሕግ መልሶ ላያስር ዋስትናው ምንድነው፡፡ የዜጎችም ሞትና መፈናቀል እስካሁን እንደቀጠለ ነው፡፡ አብይ እንደ ጠ/ሚኒስቴርነት ይህን ነው መስራት ቅድሚያ ሊያደርገው የሚገባው፡፡ ያልቻለበት ነገርም ከአለ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፡፡
ይህ ሁሉ በአለበትና እንደ ኤስ አር 168 የመሳሰሉ ሰነዶች ለሕዝብ ዋስትና በሂደት ላይ በአለበት ሁኔታ አብይን የኢትዮጵያ ልዩ መገናኛ በሆነው ፌስቲቫል ላይ እንዲገኝ ማድረግ ለወያኔ ሁለተኛ እድል መስጠት ነው፡፡ ሰሞኑን ከመቀሌ ወያኔ ትግሬ የተባለ ሁሉ ምን እየተናገረ እንደሆነ አድምጡ፡፡ ዛሬም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንዳይኖር ትግሬን ሁሉ በእነሱ ጭንቅላት አስረውታል፡፡ ኢትዮጵያዊ ነን የምትሉ ትግሬዎች ቅድሚያውን ቦታ ይዛችሁ እነዚህን ዝም ስታሰኙ እንያችሁ፡፡ አይምሰላችሁ ሕዝብ ብዙ የተሸከማቸው የወያኔ ትግሬ ጥላቻዎች አሉ፡፡  አሁንም ሌላ ተጨማሪ ጥላቻን እየተፉ ነው፡፡ ከሕጻንነት ጀምሮ በጥላቻ ያደጉ ጭንቅላቶች ከዚህ በኋላ እንደማይቀየሩ እናውቃለን፡፡ እነዚህን ኧረ ልብ ግዙ አንልም፡፡ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትሉ ትግሬዎች በቋንቋቸው ልትነግሯቸው ይገባል፡፡ የመቀሌው ስብሰባ በትግሪኛ ቢሆን በጣም ጥሩ ነበር ብዙዎች ስለማይሰሙት ቢያንስ ትግሬ ሁሉ እንደዚህ ነው የሚለውን ከብዙዎች ያርቅ ነበር፡፡ እንዴት ሰው ከእስር ይወጣል ብለው እብድ የሚሆኑ፡፡ በጭሩ ወያኔ ትግሬ ወሮበላ ወንበዴ ነው ሲለን ደርግ ሲነግረን  ከነበረው ብዙ እጥፍ በተግባር አይተንዋል፡፡ ግን ትግሬ ሁሉ እንደዚህ ነው? ከአላችሁ የት ነው ያላችሁት?  ዛሬ ዳንኤል የተባለ ሌላ ጭንቅላቱ የመረቀዘ ወያኔ አንዳርጋቸው ቪዛ ሳይኖረው እንዴት ስለኢትዮጵያ ያወራል እያለ ሲፈነጭ ነበር፡፡ ዳንኤልና መሰሎቹ ማወቅ የሚገባችሁ እናነተ ገና ድሮ ከኢትዮጵያ ተገንጥላችሁ ሄዳችኋል፡፡ በዚህ አካሂድ በታሪክ በምድር ላይ ለመጀምሪያ ጊዜ ከእኛ ሂዱልን ብሎ ትግራይን ከኢትዮጵያ እንድትነጠል በግድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያባረራችሁ መልኩ ነው አካሂዳችሁ፡፡ ይን ለማስፈራራት ሳይሆን ስጋቴን ነው የምናገረው፡፡ ይህ የማይሆን ይመስላል ግን የሕዝብ ምሬት ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ ምን ጉዶች ናቸው ከመባል ይሰውረን፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ