የ ” ይጋበዙ” ወይም “አይጋበዙ ” ውሳኔ ፌደሬሽኑ ባለው ደንብ ላይ ተመስርቶ ፤ በስፖርትና የባህልፌስቲቫሉ ሀላፊዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደትና የሀላፊነት ትከሻ ላይ የወደቀ ነው። ይሁን እንጂ፤         በዜግነታችንና ነዋሪነታችን፤ የውሳኒያቸው አካል ለመሆን ድምጻቸንን በእጅጉ ማሰማቱ ፤ የፌዴሬሽኑን ዲሞክራሲያዊ አስራር የሚያዳብር ፤ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ጎዞ በውጭው ነዋሪ  በሆነው ዜጋ የመታገዙን ባህርይ  የሚያጎለብት  ይሆናል ።

በግል አመለካከቴና ይህንኑ በሚጋሩ የቅርብ ወዳጆቼ በደረስንብት ግንዛቤ መሰረት ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርቡት ጥያቄ በሶስት አበይት ምክንያቶች ተቀባይነት እንዲያገኝ ፍላጎታችን ነው ፤

በመጀመሪያ – በሀገራችን የመሪዎች ታሪክ ለዜጎቹ “በባዕላችሁ ጋብዙኝ” ብሎ ጥያቄ ያቀረበ መሪ አላየንም፤ አልሰማንምም። በታሪክ ምሁራን እስከአልታረምን ድረስ ፤ በራሱ ጥያቄው – ታሪካዊ ተብሎ እሚመዘገብ ነው፤ መሪዎቻችንን እምናውቀው ከላይ ወደ ታች በሚወርድ ፤ በግድም ሆነ በውድ በሚፈጸም ጥያቄና ትዕዛዛቸው እንጂ፤ ራሳቸውን ወደ ህዝባቸው በማውረድና ህዝባቸውም ጥያቂያቸውን በጥሞና ተመልክቶና ወስኖ በሚያሳውቃቸው ሂደት ውስጥ በማለፍ አይደልም ፤ ዶ/ር አብይ ለዚህ መስል ባህላዊና ዲሞክራሲያዊ ሂደት በፈር ቀዳጀነት ሊታዩ የሚገባ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ – ግለሰቡ ፤ በፓርቲያቸው ኢህአዴግ ተመርጠው የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሀላፊነት ከተርከቡባት ዕለት ጀምሮ ፤ ፓርቲያቸው ላለፉት 27 ዓመት አድምቆ ያልዘመረለትን ኢትዮጵያዊነት እንዲዘመርለት ፤ ከፍ አድርጎ በክበር ያላውለበለበውን ባንዲራ በሀገርና በውጭው ዓለም እንዲውለበለብ  እያደርጉ ያሉ መሪ ናቸው ። በለውጡ መግቢያ ላይ  የ 5 ዓመት  ዕድሜ  ለነበረውና  ዛሬ  በወጣት የዕድሜ ጣሪያ  ለሚገኘውና   ቢያንስ  32  ዓመት ለሆነው ወጣት ፤ ብሄራዊ ፍቅርና አንድነት ስለሚያስገኘው ሁለንተናዊ ፋይዳ በመንገርና በማሳየት ፤ እርሱም  ከተከለለበትና  ከተከለለለት የልዩነትና  ጥላቻ ህይወት ራሱን አውጥቶ፤ በነጻነት የአንድነት ባንዲራዋን ቀና ብሎ እንዲመልከታት እያስቻሉ ያሉ ናቸው። ለወጣቱ ላላቸው ውክልና በዕለት ተዕለት ለሚያስመዘግቡዋቸው ለዕያንዳንዱዋ ተግባራቸው ምስጋና ሊደርሳቸው ይገባል ።

በሶስተኛ ደረጃ- 60 ቀናትን እንኩዋ ባልደፈነ የሀላፊነት ዕድሜ ፤ ቃላቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የወሰዱዋቸው እርምጃዎች

፤ ይህንንም ለማድረግ ያለፉባቸው መንገዶች በቀላል ሊታዩ አይገባቸውም ። ጉዞዋቸው አልጋ ባልጋ አይመስለንም፤ ምላሽ እንዲሰጡባቸው ለተጠየቁባቸው እንደ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ መነሳት፤ የመፈናቀል፤ የመታፈንና የመታሰር ሂደቶች መቆም ፤ የህዝቡንና በፓርቲያቸው ውስጥ ያሉ ለውጥ ፈላጊ ሀይሎችን እጋዛ ጭምር የማሻ ነው፤ የትግሉ ሚዛንና አቅጣጫ ከውዥንብር በፀዳ የህዝብ ድጋፍ የመመራቱ አስፍልጊነት በግልጽ ቁዋንቁዋ ሊነገር ይገባል ፤ የጠ/ሚኒስትሩም የ “ጋብዙኝ ጥሪ” አዎንታዊ ምላሽ መሰረታዊ ዓላማም በእስካሁን ላሳዩት የለውጥ ፍላጎትና ድርጊት አክብሮት ማሳያ በቻ ሳይሆን፤ ነገና ተነገወዲያ ለሚውስዱዋቸው እርምጃዎች ለስፖርት ታዳሚው ቤተሰብ ፤ እንዲሁም ለመላ ዜጎቻቸውቹ መልዕክት እሚያስተላልፉበትንና ፤ በዋናነትም ” የአግዙኝና

፤ ከጎኔ ቁሙ ” ጥሪ   እሚያቀርቡበትን  መድረክንም ጭምር  የሚያመቻቻ  ነውና  አዎንታዊ መልስና  ድጋፋችን እንዳይለያቸው ፍላጎታችን ነው።

 

በመሰረቱ ፤  በጠቅላይ  ሚኒስትሩ መሪነት የተጀመረው ለውጥ ወደግባችን እንዲወስደን ቢያንስ ሁለት አማራጭ መስመሮች ይዘን እንድንጉዋዝ በፖለቲካው ዙሪያ የተሰለፉ ወገኖች አበክረው እየነገሩን ነው። የመጀመሪያው፤ ላለው ህገመንግስታዊ መሻሻል፤ በዚህም ላይ ተመስሮቶ ለሚመጣው አዲስ የሰርዓት ለውጥና ፤ በእርሱም መሪነት ሁሉን በእኩልነት ላሳተፈ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ

 

ሀገሪቱ የምትበቃበትን መንገድ ማስተካከል ነው፤ ሁለተኛው በህዝብ ግፊት ብቅ ያሉት የኢሕአዲግ ለውጥ ፈላጊ ሀይሎች ራሳቸውንና ፓርቲያቸውን ፍትሃዊ ለሆነ ነፃ ምርጫ የማዘጋጀቱና የአዲሱ ስርዓት አካል ሆነው መጉዋዛቸውን የማረጋገጡ ሂደት ነው። በዚህ ጉዞ በርካታ ጥያቄዎቻችን እንደየወቅቱና አግባብነቱ እየተመለሱ የሚሄድበት ስር አት እንደሚሰፍን ተስፋችን ነው፤ ሂደቶቹ እንዳይዛቡና ፤ ከፈረሱ ኮርቻውም ዓይነት ሁኔታ እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው ። በተቃራኒው ሊከሰቱ ለሚችሉ፤ ለመጥቀስ ያህል፤ የፓርቲያቸው የአለመለወጥ እንቢተኝነት ባህርይና መፈንቅለ መንግስታዊ አደጋ ሀገሪቱ እንዳትጋለጥ የምናደርግው ቁርጠኝነት

፤ በዛሬው ውሳኔያችን ላይ ጭምር የሚወድቁ ናቸው፤

ዶ/ር አብይ በውጭ ባለው ህዝባቸው መሀከል ተገኝተው ሃሳባቸውን የማካፈሉ ተግባር ከ እነዚህ መገለጫዎች አንዱና ትንሹ እርምጃ ነው ፤ ግብዣው፤ በዕለቱ የክብር እንግዳ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ በውጭው ዓለም  በጉብኝት  ላይ  እንዳሉ  ከሚነገርላችው

፤ እንዲሁም ተቀምጭነታቸው በዚሁ በአሜ ሪካ ከሆኑ ታዋቂ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፤ የሰበዓዊ መብት ተሙዋጋቾችና መላ

ዜጋቸው ጎን ቆመው መድረኩን በግልጽ ውይይት፤ ጠያቂነትና ተጠያቂነት ጭምር እንዲካፈሉት መልካም አጋጣሚ  የሚፈጠርበትና የአብዛኛውን        ኢትዮጵያዊ ድጋፍ በእጅጉ የሚገኝበትም ነው፤ የስፖርት ፌዲሬሽኑም ይህንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ፤ከስሜት የጸዳና አብዛኛውን ዜጋ የሚያሳትፍ ሚዛናዊ ውሳኔው እንዲሚያሳልፍ ተስፋችን ፅኑ ነው ፤ ዕለቱ ኢትዮጵያዊነትን በሚያስተጋባ የአንድነት ድምፅ ደምቆና በባንዲራዋ አሸብርቆ እሚውልበት እንዲሆን እንመኛለን ።