“ጥሩ ነገር እስከሰሩ ድረስ እኛ የመቃወም ሱስ የለብንም። ጠ/ሚኒስትር አብይ ከህዝብ ጋር ያደረጋቸውን የተለያዩ ውይይቶችን ተከታትያለሁ ጥሩ ጅምር ነው። ተስፋ የሚሰጥ ነገር ይታያል።” – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት ፓርቲ ጸሃፊ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበር ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውንና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት የገለጹ ሲሆን በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።