Adda Bilisummaa Oromoo(ABO)
Oromo Liberation Front(OLF)
Guyyaa:Caamsaa/30/2018
Date: May/30/2018

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (የተዋሃደ ኦነግ OLF-U) የስራ አመራር ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባዉን በግንቦት 20, 2010 አካሄዱዋል:: በዚህ መደበኛ ስብሰባ ኮሚቴው የወቅቱን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል, በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በኦሮሞ ሕዝብና በሌሎችም ወገኖች የሚከፈለው መስዋእትነት, እና ትግልን አስመልክቶ በመወያየት,

የድርጅታችን ትግል ዋና ዓላማ የኦሮሞ ሕዝብ  ዕጣ ፈንታውን እንዲወስን ማድረግ ነው ::እንዲሁም በአገራቸው ውስጥ በእራሳቸው የገዳ ሥርዓት ወይም በኢትዮጵያ ክልሎች ህዝቦች ጋር ባዲሞክራሲያዊ ትስስር እንዲተዳደሩ ማድረግ ነው :: የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት, ነፃነት እና ፍትህ በህግ የበላይነት ስር ከተለያዩ ህዝቦች ጋር ለመኖር ያ ካልሆነ ወይም የራሱን ሉዓላዊ መንግስት መመሥረት ነው::

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየሰፋ ያለው የለውጥ ነፋስ የመንግሥት ስጦታ እንዳልሆነ ድርጅታችን ያምናል:: ስለሆም ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ነፃነታቸውን ለማስከበር በኦሮሞ ቄ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት የሆነ መሆኑን በማመን የኦሮሞ ቄሮዎች ከፍተኛ መስዋዕትነት, ድፍረቱንና ውጣ ውረድን ጨምሮ ሌሎች ህዝቦቿን በማስከተላቸዉ, ለነፃነት, ለዴሞክራሲና ለፍትህ ተነሳሽነት እንዲነሱ አድርገዋል::

በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ቆራጥ ትግል “የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት” ኦሕዴድ በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የኦሮሞ ብሔርተኝነት ህዝባዊ አመራር አባላት ትግሉን ተቀላቅለዋል :: ወደ ትግሉም መቀላቀላቸዉ እና የለማ ቲም የኢትዮጵያ ህዝቦች እውነተኛውን ትግል ለመምራት ማሰባቸዉ የላማንና የዶክተር አቢይ አህመድ ቡድንን እንድናደንቃቸው ኣድርጎናል :: የኦሮሞ ህዝብ ትግል የአለመበት ግቡን ባይደርስም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ጥቅም በሁሉም መዕዘን እንድምቀጥል በማመን እንድሁም በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ለውጥ መደገፍ ያለበት መሆኑን በመገንዘብ:-

የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል ::

  1. በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ነፃነት እና ዴሞክራሲን ለማምጣት ሁሉንም የፖለትካ ድርጅቶችን የምያካቲት ብሔራዊ መግባባትን ለመጀመር አስፈላጊ እና ወሳኝ ናው:: በኢትዮጵያ ውስጥ የተካተቱ የፖለቲካ ውይይቶችን ለማጠናከር የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ / ር አቢዬ አህመድ እና በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ወገኖች የሚያካቲት የፖለቲካ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ በመሆናችን,
  2. የውይይቱ አጀንዳ ዉይይቱ ከተጀመረ ብሗላ ሊነሳ የሚገባ መሆኑን እንገልፃለን,
  3. ድርጅታችን በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ መንግስት ማድረግ ያለበት,

(ሀ) በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችን የሚገድብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳት ኣለበት::

(ለ) የኢትዮጵያ መንግስት የእኛን ድርጅት ጨምሮ ሌሎች የፖለትካና የሶሻል ድርጅቶችን በሽብርተኝነት የምፈርጀዉን ህጎችን ማንሳት ኣለበት::

(ሐ) ከ 1991 ዓ.ም. ጀምሮ በኦነግ አባልነት ወይንም ደጋፊነት ተፈርጀው በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በምታወቅና በስውር እስር ቦታዎች የታጎሩትን ያለ ቅድመ ሁኔታ መለቀቅ ኣለባቸው::

 

በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የኦሮሞን  ህዝብ  ሁለንተናዊ  ግብ  የምያራምደውን ማንኛውንም ዉይይትና እንዲሁም እኩልነት ፍትህና ነፃነትን ከሚያራምዱት አካሎቾ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን እናስታውቃለን::

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ! ግንቦት 30/2010