ይሄን ምን ትሉታላችሁ ? “I have spoken to the Prime Minister on a number of issues. We have discussed so many important issues, but I would not go to the details,” ሲል አንዳርጋቸው ከዶር አብይ ጋር ስላደረገው ንግግር የሰጠው ዝርዝር አስተያየት የለም። በጣም ቁልፍና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተነጋገሩ ግን አንዳርጋቸው አረጋግጧል።
ከዚህ በኋላ ግንቦቴዎች ፣ ፖለቲካውን መቀጠል ከፈለጉ፣ ጣጣ ሳያበዙ ፣ እናደርጋለን የሚሉትን፣ ግን የቁጩ የሆነውን፣ የትጥቅ ትግላቸውን አቁመናል ብለው ፣ ወደ አገር ቤት ይመለሱና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለምርጫ ይወዳደሩ። ወይንም ደግሞ ድርጅታቸውን አክስመው ያው የነርሱ “ቅርንጫፍ” የሆነውን ሰማያዊ ይቀላቀሉ።
አንዳርጋቸው ከዚህ በኋላ መቼም የነ ዶር ብርሃኑን ባዶ ከበሮ በመምታት በነ ዶር አብይ ላይ የትጥቅ ትግሉን እቀጥላለሁ ይላል ብዬ አላስብም። ያዉም ከወያኔ ጋር ተነጋግረው ያሳሰሩትን ሻእቢያዎች እንደገና አምኖ !!!
ስለዚህ ግንቦቴዎች ምንም ምርጫ አይኖራቸው ወይም መሞት አለበለዚያ ወደ አገር ቤት ገብቶ በሰላም መታገል።
በነገራችን ላይ ይህን ዶር አብይ ነው ግንቦቴዎች በኢትዮጵያ የ እግር ኳስ ውድድር ላይ እንዳይጋበዝ ሎቢ እያደረጉ ያሉት። በነገራችን ላይ ግንቦቴዎች ለፌዲሪሽኑ ደብዳቤ አስገብተዋል። ዶር ብርሃኑም ካልተጋበዘና ንግግር ካላደረገ ብለው። ይኸው ለንስት አመታት በዉሸት ሲያደነቁረን የነበረን፣ አሁንም የኢሳያስ አፈውርቂ አሽከር የሆነን ሰው መጋበዝ ማለት የኤርትራን ህዝብ መስደብ ፣ ዉሸትና ማጭበርበርና ማበረታታት ነው።
ዶር ብርሃኑ ከተጋበዘ ዶር ታዬ፣ ዶር መራራ፣ ዶር በየነ፣ ዶር በዛብህ፣ ዶር ጫኔ፣ አቶ ስለሺ ጥላሁን አቶ ተክሌ፣ አቶ ዳዊድ ኢብሳ፣ አቶ ልንጮ ለታ…..ሁሉም የፖለቲክ መሪዎች መጋበዝ ይኖርባቸዋል።
ግርማ ካሳ