ዶክተር ደብረጽዮን በትላንትና ጉንበት 20/09 / 2010 ዓ ም ማታ ከምሽቱ 1 .30 በጋዜጠኛ ታጋይ ብርሀኑ አባዲ ጥየቄ ሲያቀርብልህ ሰማሁ ።
ጥያቄው ምንም እንኳን አድር ባይነት ያዘለና ፈሪ ቢሆንም ብርያኑ የጠየቀው ነጥብ እናንተ ለነባር ታጋዮች ምንም እንኳን ልዩነት ቢኖራቸው ያሳለፉት መራራ የትግል ጊዜ ፣የጓደኝነት ፍቅር አስታውሳችሁ የእግዚአቢሄር ሰላምታ እንኳን እንደመስጠት በቂም በቀልና በጥላቻ ነው የምታዩዋቸው ለምን እንዲህ ይሆናል?
የኦሮሞ ኦሆዴድ አማራር ለእንደ ዶክተር ኖጋሶ ጊዳዳ እንክብካቤ ከማድረግ አልፎ የክብር ሽለማትም ሰጥቶዋቸዋል እንዳው ህወሓት ኢህአደግ ህገመንግሰት መብታቸው ነጥቆ ደሞዛቸው ፣ቤታቸው፡፡መኪናቸው ቀምቶ የሰደዳቸው። ታድያ እንደዚህ አይነት በጎ ምግባር የህወሓት መሪዎች ለምን አይከተሉትም ?? የሚል የአብዛኛው የትግራይ ህዝብ ነው ? ጥያቄ ነው ብሎ ሲጠይቅ ጠያቂው ፣
ደጉተር ደብረጽዮን የሰጠው መልስ ይላል ፣እኔ እንደዚህ አይነት የህዝብ ጥያቄ አላውቅም አሁን የቀረበ ጥያቄ ለእኔ አዲስ ስለሆነ በፍጥነት አጥንቸ በአጭር ጊዜ መልስ እሰጥበት አለሁ ብለዋል ።
አሳዛኝ ነገር ፣ዶክቶር ደብረጽዮን አንተ የማትረሳው ነገር ላስታውስህ ?
1ኛ — በ1984 እና 1985 ዓ /ም 32 000 ታጋዮች አንዳ አንዶቹ በውሀ ቀጠነ የታሰሩ ፣ አብዛኞቹ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ የአገርና የዜጎች ሉአሏውነት አነስተው የታሰሩ በድምር 32000 ታጋዮች በመላው የሀገራችን ወታደራዊና ማረምያ ቤት ታስረው ጥቂቶቹ ከ 1 አመት እስከ 3 አመት በላይ ታስረው አብዛኞቹ ተባርረው ጠቂቶቹ ተመልሰው ታስረውበት የነበረ ወህንቤትና በድህንነት መስራቤት ኮኖሌኔል መአርግ የነበራቸው በተራ ወታደርነት ዘበኛ ፣ተላላኪ ሆነው ተቀጥረው በየተመደቡበት ቦታ በአቶ ክንፈ ገብረመድህን የተነገራቸው ቢኖር ፣እናንተ የምትመደቡበት ያለችሁ ነጻ ሆናችሁ የምትሰሩ ሳትሆኑ መንነታችሁ እስከሚረጋገጥ በእስር አንዳላችሁ እወቁ ብሎ እንደመደባቸው ዶክቶር ታውቃለህ በወቅቱ አንተ በድህንነት መስራቤት ሰለነበርከ ። ለዚሁ የሚመሰክሩ የሽግሩ ተቋዳሽ የነበሩ አንድዶቹ በሆሎታ እሱርቤት ባጋጠማቸው ሰቆቃ ታመው ከሞቱ የቀሩ የፖሊስ ጀነራል አክሊሉ ተጠምቀ ከአክሱም ፣አበበ ዘምቸአል ከአክሱም ፣ ፍስሀ ማንጁስ ከአክሱም ፣ አራፋይነ ነጋሽ ጣሰው ከአክሱም ፣በያን ፍትዊ ከሽሬ ፣አጽብሀ ሀይለማርያ ከሽሬ ፣ ኮኖሬል አለምሰገድ ወረታ ከሽሬ ወ ዘ ተ ሊመሰክሩ ይችላሉ ።
የቀሩ በአስርሽ የሚቆጠሩ የጦር መሪዎች ፣የፓለቲካ መሪዎች እንደ ሞተር ለፓርቲው እየአንቀሳቀሱ የኖሩ ፣የበታች ሽማሙንቶችና ቡዙሀን ታጋዮች ያለአንዳች ማቋቆምያ ፣መጓጓዣ ፣ስንቅ ተባርረው በመላው የሀገራችን ከተሞች ተበታትነው ወደ ትውልድ ቃያቸው እንዳይመለሱ መሳፈሪያ አጥተው አጅግ ቡዙ ታጋዮች በዛው ጠፍተው ሲቀሩ ቤተሰብ ያሉዋቸው አቅምያላቸው ወላጆቻቸው ልጆቻቸው ወደ አሉበት የተባለ ክልል ሄደው ወደ ቤታቸው ወሰዱዋቸው ።ቡዙ ወጣት ጀግኖች ሴቶች ጦር መሪዎች የፓለቲካ መሪዎች በየትላልቅ ከተሞች ተበታትነው ሲጨንቃቸው ወደ ሴትኛ አዳሪነት ተሰማርተው ለበሽታ ተጋለጡ አብዛኞቹ የተሰው ጀግኖች አያሳደጉዋችሁ እመራችሁ የመጡ እስከሞት ሲደርሱ ። እነ ሀይለዮሱስ ሰሎሞን የኮር ፓለቲካ ሀላፊ የነበረ ከአድዋ ፣ቀሺ ማአር አድስ አባባ ስንገባ ክፍለጦር አዛዥ የነበረ ሁለቱ አዲስ አባባ ታመው ማሳከምያ አጥተው ቀሺማኢር በተክለሀይማኖት ብራንዳ ሞቶ መዛገጃ ቤት ቀብሮታል ፣ሀይለየሱስ አለቃቸው የነበሩ ከነሬል ፍስሃ ማንጁስ፣ ሳኢሊ ጸጋይ ጦቆሽ አድዋ ወስደው ቀብረውታል ። ወላጆቹ ጥሮቶኛ መምህር ሰሎሞን እናቱ መምህር የነበሩ ተደናግጠው ታመው ተበላሽተው ሞተዋል ። በእሱርበት በተለይ በሆሎታ በሌሎች ቦታወችም የሞቱ አሉ ።
በሌላ በኩል ከተበታተኑ በኃላ በቡዙ ሽግር ክልላቸው ገብተው በተወለዱባት መንደር በዚያች ድሮ ጥለዋት የወጡ ጎጃቸው በሰላማዊ መንገድ ድህነታቸው ችለው እንዳይኖባት የህወሓት መሪዎች እሀለቃ ጸጋይ በርሀ ፣ሓሰን ሽፋ ፣አባይጸሀዬ ፣ስብሀት ነጋ ሌሎችም በነዛ የውሼት መርዝ መሳረጫ የትግርኛ ሚዲያዎቻቸው አድርገው ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፉት የግፍ ግፍ ቀጭን ትእዛዝ በመስጠት አሉ ፣ስማ የትግራይ ህዝብ የታጋዮች ወላጆች ፣ቤተሰብ ዘመድ ፣እነዚህ የታገሉለት አላማ ከድተው ፣ ወደ መጥፎ ተግባር ተሰማርተው ቡዙ ምክር ተሰጥቷቸው ባለመስማታቸው ፓርቲያችን ስለአባረራቸው በየትውልድ ቃያቸው ሄደው ለዚያ ንጹህ ህዝባችን እንዳይመርዙ ሁሉ ህዝብ ይጠብቃቸው ብለው በተደጋጋሚ ቡዙ ሳምንታት አሰራጩት ።ይህ ግፍ ዶክተር አታውቀውም በእውነትም ያስታዛዝባል !!! እኒህ ጅግኖች ይህ ነበር ዋጋቸው ?
***** አንድ ነገር ላስታውስህ መለስና እሱ ሲነዳው የነበረ የህወሓት ማእከላይ 17 አመት ታግለው ወደስልጣን ያወጡት ባገራቸው ቁመው እንዳይ ሄዱ አድርጎዋቸው በጎደና ሲምቱ ለጓደኛቸውና ወንድማቸው የኢሳኢያስ መንግስት አካል ጉዳቶኞች ግን ከ 1. 6 ቢሌን ብር መቋቋምያ ሰጥተዋል ። ይህ አያሳዝን ? እነዚህ ዜጎች በየተኛው መስፈርት ዜጎች ናቸው እንላቸው አለን ??
2ኛ —-ሌላስ በስመ በመመጣጠን ተብለው በአስርሽህ የሚቆጠሩ ታጋዮች ባልፈለጉት ቦታ አንሄድም ብለው ወደ የድሮዋ ጎሳሳ ጎቻቸው የሄደው እንዳይኖሩ በእሱር ቤት የገቡም አሉ ። ሌሎች ደግሞ ከሄዱ በኃላ ህዝብ ተቃውሞ አሳይቶ ጥያቄ ስለተነሳ ማስታገሻ አድላዊ በሆነ መንገድ ለግማሹ 2000 ብር ለግማሸቹ 3000 ብር ተሰጣቸው ፣ከ10 000 በላይ ጅግና ሴቶች ታጋዮችም በ 3000 ብር ተባረሩ ፣እነዚህ ሴት ታጋዮች ሁሉም ለማለት ይቻላል ከሁለት በላይ ልጆች የተሰው ልጆች ይዘው የሚያሳድጉበት ተበታትነው ለነሱ በማይመጠን ዘግናኝ ስራ ተሰማርተው ይኖራሉ አብዛኞቹ ሞተዋል ። በተለይ በመቀለ ፣በኪሓ ፣ ዓዲ ግራት ፣ በአክሱም ፣ በሽሬ ፣በሕሞራ ፣በተንቤን ፣በውቅሮ ወ ዘ ተ ተሸግረው ይኖሩ ነበሩ ። በአንጻሩ ግን ለሻአብያ ሰራዊት ከ30 000 እስከ 50000 ብር መቋቋምያ ተሰጥቶዋቸል ።
3ኛ በትግራይ ክልል ጥሮታ ፣የሀኪሞች ቦርድ ውሳነ የሌላቸው አበል የማያገኙ 118 000 አካል ጉዳቶችኞች በልመና ተሰማርተው ክፉ ንሮ የሚነሩ አሉ ።በአነጻሩ በነዚህ አካል ጉዳተኞች ስም የሚነገድላቸው በአስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነብሶ ) እና አጽብሀ አረጋዊ አብርሀለይ ባርኖስ የሚባሉ ፣ሁለቱ የፓርላማ አባላት ስም የሚታወቅ መረዳጃ የአካል ጉዳቶኞች ማህበር ከ80 በላይ የደረቅ ጭነት መማላለሻ መኪኖች አሉዋቸው ። ሌሎችም በአዲስ አበባ ይሓ ህንጻ በለጋህር አካባቢ የሚገኝ በሞቶዎችች ሚሊየን የተሰራ በአሁኑ ጊዜ በየወሩ በሚሊዮን ብር የሚቆጠር ኪራይ ቤት ገቢ ያለበት ፣በመቀለ ዓዲ ሓቂ ቀበሌ ሁለቱ ሰማይጠቀስ ህንጻዎች በሚሊዮኖች ብር ገቢ ያላቸው ።በሌሎችም የሚከራዩ ቤቶች ፣የመጠጥ መከፋፈያዎች የናይስ ንጹህ ውሀ ፋብሪካ አላቸው ።በተጨማሪ በነዚህ ስም ከአለም አቀፍ ምግባረሰናይ ተለምኖ የሚገኝ እርዳታ እንዳለም ይነገራል ፣ የጠቀስኳቸው አካል ጉዳተኞች በጸረ ደርግ የ17 አመት የፈጀ ጦርነት የተጎዱ ሲሆኑ ፣በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተጎዱ የተሻለ የጡሮታ አበል ቢኖራቸውም ንሮዋቸው እስከዚህም አይደለም የተጎሳቆለ ነው ።
እነዚህ ድርጅቶች ለአካል ጉዳቶኛች በአክስዮን ባለቤትነት ቢሰጡዋቸው ንሮ ወደ ልመና አይሰማሩም ነበር ግን ምን ይሁን የህወሓት መሪዎች ስለ ራሳቸው ዘርዘራቸው የሆኑ ትጃሮች ይቆረቆራሉ እንጅ ስለ ጉዳቶኞች ምናቸው ሆኑእና ??
4 —- በ1997 ዓ / ምረት ህወሓት በማኸሉ በተፈጠረው ውስጣዊ ብልሽት እና የሀሳብ ልዩነት በሁለት አንጃ መሰናጠቅ ተከትሎ የመለስ ቡዱን የተሳሳተ መስመር ይዞ እያለ ለነዛ የተሻለ መሰመር ለያዙ ቡዱን ከመታ በኃላ ከተሻለ መስመር ይዞ ያለአግባብ ለተሸነፈ ቡዱን ተከታይ ያሉዋቸው ነባር ተጋዮች በመፈናቀል በውሀ ቀጠነ ከስራቸው ተባርረው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ሽግር ላይ ወድቋል ። ታድያ ዶክተር ደብረጽየን ለዚህ ችግር ተጠይቀህ ስትመልስ የማታውቀው መስለህ መታየትህ ሁሉ ግፍ የተፈጸመበት ታጋይ ሁሉ ትእዝብት ላይ ጥሏሀል ።
ወደ ግል ጥቅም መጣህ እንዳትሉኝ ይቅርታ ሀቅ ተሞኩሮ ለሁሉ ህዝብ ሊያስታላልፍ ስለሚችል ልገልጸው የግድ ይለኛል ። ባለፈው አመት የልቤን ደመም መታላለፍያ የደምስር ቦንባ (Arteri) 100% ተዘግቶብኝ ለአፍ ሞት ደርሼ የልብ ህክምና ከባድ ክፍያ የሚጠይቅ በመሆኑ ቢያንስ በዘመናዊ የልብ ቀዶ ጥገና በሚሊዮን የሚገመት ዶላላር ስለሚጠይቅ የመንግስት ወይ ትላልቅ ድርጅቶች ክፍያው ካልሸፈኑልኝ ቤት ዘግቼ ሞሞት ነበር የሚጠብቀኝ ። በመሆኑ ለሚከተሉ መንግስታዊና ዘይመንግስታዊ ድርጅቶች መጠየቅ የግድ ይለኝ ነበር ? በመሆኑ ለህወሓት ፣ለክልል ትግራይ አስተዳደር ፣ ለትግራይ እርዳታ ማህበር ፣ ለኤፈርት ፣ጽፈት ቤቶች ፣ ለሀገር መከላከያ ምንስቴር ፣ለጠ/ ምኒስቴር ቢሮ ፣ለበአዴን ፣ለበአዴን ጥረት ፣ ለኦሆዴድ ፣ በተለይ ደግሞ ተጽእኖ ፈጣሪ ልትሆን ትችላለህ ብዬ በመገመት ለዶክተር ደብረጽየን ጨምሬ በኢኤምኤስ ፓስጣ አድርጌ300 000 ዶላር እንደሚያስፈልገኝ ልኬላችሁ በጠየኩዋችሁ ጊዜና ሰአት መሰረት አንድ መስሪያቤት ወይ ግለሰው መልስ አልሰጠኝም ። እኔ ግን መላው የኢትዮጱያ ህዝብ ቢሄር ሀይማኖት በማይለይ በሚሌን ዶላር የሚጨርስ በአመሪካ በከፍተኛና ምርጥ የልብ ቀዶ ጥገና ( katlab srgeri ) ህክምና እንዲደረግልኝ ኖች እና ታክሜ እንድድን በመላው ክፍለአለማት የምትገኙ ወገኖች ላደረጋችሁል ወሎታ እጅጉን አመሰግናችሁ አለሁ !! በተጨማሪ አምና ባማቻቹልን ዘንድሮም የሀኪም ቀጠሮ ስለነበረኝ በሞቶ ሽ የሚቆጠር ዶላር የሚፈጅ ህክምና አድርገውልኛል ።
የህወሓት ኢህአደግ ፓርቲዎች እና የግል ኪሳችሁ ሞምልያ የዘር መንዝራችሁ መንደላቀቅያ የሆኑ ድርጅታችሁ ሰለ ኢትየጱያዊ ዜጋ ሊቆረቆሩስ ይቅር ለ17 አመት ያገለገልናቸው ዜጎች የሸግራችን ደራሽ ለመሆን ፍላጎት ሊኖራችሁስ ይቅር በጠላትነት ደረጃ ነው የምታሰሉፍን ። ዶክቶር ደብረጽዮን እስከ 1997 ዓ ም በአንጋፋዎቹ ተደማጭ ባለሞኖርህ ከታችኛው መደብ እረቀህ ወደ ገዥ መደብ እየተጠጋህ በሀድክ ቁጥር ቁጥር በጓዶች የጭካኔ መንፈስ እያሳየህ መምጣት ተገንዝቤ አለሁ ። ሌላ ስለ ከህወሓት በአቋማቸው ተለይተው የሚንቀሳቀሱ ፣ በአካል ጉዳተኞች እና የሚያቋቁማቸው ያጡ ድሀ ታጋዮች ያለው ችገርም ዝቅተኛ ከነበርክበት ስልጣን ከፍ ባልክበት ወቅት ግን የአንጋፋዎች ባህሪ እተላበስክ ሂደሀል ። በመሆኑ እንደገና የህዝብ ልብ ትርታ ብትመለከት የተሻለ ነው ።
5ኛ —- ዶክተር ደብረጽዮን ስለ ኤፈርት በሚመለከት ተጠይቆ ፣ የአፈርት ተቋማት የህዝብ ናቸው ፣የውስጥና የውጭ አዲተር አላቸው ብለዋል ። ስለየኤፈርት ባለቤትነት ግን 1ኛ ኤፈርት ማምረት ከጀመረ በ1987 ጀምሮ በየአመቱ ያገኜው ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ የተጣራ ትርፍ ገልጽ በሆነ መንገድ ለህዝብ ቀርቦ አያውቅም ።
አንድ ነገር ግን ግልጽ መሆን ያለበት ትራንስ ኢትዮጱያ የደረቅና የፈሳሽ መጓጓዣ ፣መስፍን እንጅነሪንግ ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ሱር ከንስትራክሽን ፣ በውጭ የነበረው ታዎር ኮርፕረሽን ፣ወጋገን ባንክ ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ ወዘተ ከ1984ዓ ም ማምረት እና ትልቅ ገቢ ያኙ ነበር ። ይህ ገቢ ሚስጢሩ ከስብሀት ነጋ ፣አርከበ እቁባይ ፣መለስ ዜናዊ ፣ስዩም መስፍን ፣አዜብ መስፍን ወዘተ በዋናነት በአጠቃላይም የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውጭ ፣ማእከላይ ኮሚቴም ለነስብሀት ታማኝ የሆኑ አንድ ሁለት ብለህ የምታስቀምጣቸው እንደነ ተክለወይን አሰፋ ያሉ ጥቂት ሚስጢር የሚያውቁ ነበሩ እንጅ አብዛኛው ማእከላይ ኮሚቴ ስለ ኤፈርት ኩባንያዎች ገቢ ፣ወጭ ፣ስንት ነው ብሎ ፣ገንዘቡ በማን እጅነው ፣የትስ ይሳማራል ብሎ አያውቅም ነበር ። ምናልባት ደኩተር ደብረጽዮን ወደ ስራ አስፈጻሚ ከመጣት በኃላ የሚያውቀው ከነበረ ራሱ ይመስክር ። ዶክተር ደብረጽዮን ሀቁን እያወቀ የኤፈርት ውስጢር ሳያጎላ አድበስብሶ ማለፉ ሀቁን ለምናውቅና ለአድማጭ ለክልላች ህዝብ ግልጽ ሳያደርግ አልፈዋል ።እንዳው አንጋፋዎች ከአሁን በፊት ይሰጡት ከነበረው ስለ ኤፈርት መረጃ በባስው ድብቅ እና የወረደ መልስ ነው የሰጠኸው ።
የኤንፈርት የባለቤትነት መብት እኮ ከ1984 ዓ ም ጀምሮ ሲቋቋም አኮ የህወሓት ፓሊት ቢሮና ታማኝ ማእከላይ ኮሚቴ ፣እንዲሁም ለማጭበርበር ሲባል ጥቂት የነሱ ታማኝ አርሶ አደሮች በባለቤትነት ተይዘው የኖሩ ናቸው ደብረጽዮን ወደ ስራ አስፈጻሚ ከሚቴ ከወጣህ የኤፈርት ገቢና ወጭ በሚገባ ታውቅ ነበር በመሆኑ የውስጥና የውጭ ኦዲተር አለን የሚለው ለፓለቲካቹህ እና ለትግራይ ህዝብ ለማጭበርበር የሰጠኸው መግለጫ ነው እንጅ የኤፈርት የንግድ የእንድስትሪ ተቋማት ከ1988 ዓ ም ጀምሮ በቡዙ ቢሊዮን የሚሰላ በየአመቱ ገቢ ነበረው አሁንም በየአመቱ በአስር ቢሊዮን የሚቆጠር የተጣራ ገቢ እያተረፈ ነው ።ስለዚህ ከላይ ያስቀመጥካቸው 6 ኩባንያዎች ከ1984 ዓ ም ጀምረው አያመረቱ የቆዩ ኩባንያዎች ሲሆኑ የቀሩ በአስር የሚቆጠሩ ኩባንያዎች ግን 22 አመት ሙሉ እመረቱ ቆይተዋል አሁንም ሁሉም እመረቱ ናቸው ያተረፈው አለ ፣ ህዝብ እያነሳው ያለው ጥያቄ የኤፈርት ድርጅቶች 5 ሚሊዮን ህዝብ የባለቤትነት መብት የሌለው የህዝብ ሀብት ነው እያላች በባዶ ሆዳችን ትነግዳላችሁ ነው እያለው ያለ ?
ሌላ የኢፈርት ኩባንያዎች የህዝብ ናቸው ካላቹሁ ለእድመ ደረስ ለትግራይ ህዝብ በአክስዮን መልክ የባለቤትነት መብት እጣ ይኑረን ነው እያለ ያለው ? የአመራሩ ጉዳይ ደግሞ ህዝቡ ገቢው ሊከፋፈለው ሳይሆን ፣መጀመሪያ መታሰብት ያለበት በመተዳደሪያ ደንቡ ሊያስቀምጡት የሚገባቸው አላማዎች የጠቅላላ ገቢ ወጭ ተቀንሶ ቀሪው በየትኛው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ይውላል ወይ ይፈታበታል ? እንዴት አይነት እንድስትሪ የሰራበታል ፣የእርዳታ(ምግባረሰናይ) ለትምህርት ቤት ፣ለጤና ተቋማት ፣ ለአካል ጉዳተኞች ቤት መስሪያ ፣ ይሰጥ ከሆነ ?ለመስኖ ስራ የሚሆን ግድብ መስርያ ፣ለእንድስትሪ መስፋፍያ መስርያ ፣በድርቅ ለተጠቁ ዜጎች ፣ለስራጥ ወጣቶች ስራ መፍጠር ማገዝ ፣ለዜጎች የውሀ ሽገር መፍቻ እርዳታ መስጠት ወ ዘ ተ በአጠቃላይ መንግስት ሊሰራው የማይችል ሽግር ካለ መፍቻ እንዲውልና ለሌሎች ሰራዎች አንዲውል የህዝቡ ባለ አክስዮኖች ማህበር በጉባኤ ይወስናሉ ። የአማራሩ ቦርድ ዳሪክቶሮች ፣ስራ አስፈጻሚዎች የሁሉም ኩባንያዎች ዳሪክቶር በባለ አክስዮን ማህበር ተመርጠው መመደብ አለባቸው የሚመደቡም በዘመድ አዝማድ ሳይሆን ሙያ ብቃታቸው የተካኑ ሆነው በውድድር የሚቀጠሩ መሆን አለባቸው ። የውጭ አዲቶሮች ፣ የውስጥ አዲተር በባለ አክስዮን ማህበር በጉባኤ ይመረጣሉ ፣ተጠሪነታቸውም ለጉባኤ ይሆናሉ ። ከነዚህ ኩባንያ የህወሓት ማከላይ ኮሚቴ ወይ ከመንግስት ባለስልጣናት የክስዮን ባለቤትነት ሊኖራቸው ይችላል ።መመረጥ ግን የለባቸው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከኤፈርት እጁ መግባት የለበትም ።ከአሁን በፊት የነበሩ ኩባንያዎች ማምረት ከጀመሩበት ዘመን እስከ አሁን በገለልተኛ በውጭና በውስጥ ኦዲቶሮች ኦዲት መደረግ አለባቸው ። ሌላ መጠናት ያለበት የኤፈርት ከገቢ ትርፍ ተሰብስቦ የተቀመጠ ገንዘብ ፣ንብረት የት አለ በማን እጅ ኧአለ ግልጽነት ባለው መንገድ ለህዝብ ይነገረው ነው ህዝብ አየጠየቀው ያለው? የትግራይ በየአለበት ሆኖ ፣ አነዚህ ኩባንያዎች በባለቤትነት ካልተረከበ በስሙ መነገድ የለበትም ። ይህ ካልተደረገ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኮሚቴ የተጠራቀመች ገንዘብ እዛቀ ግለጽነት በሌለው በህዝብ መነገደ ይህ ትውልድ ተቃውሞው በማሰማት እንዲስተካከል ማድረግ አለበት ።
የተከበራቹ አንባብያን የኢፈርት የባለቤትነት ጉዳይ በሚመለከት ገና ኢፈርት እንደተጀመረ ረጅም ጊዜ ሳይቆይ በወቅቱ በ1984 / 03 /84 ዓ ም በመቀለ ቀበሌ 17 ስለኤፈርት የኤፈርት አደረጃጀት አጀማማመር ፣ የባለቤትነት መብት የት እና እንዴት ይመስረት ( ይቋቋም) የሚሉ የባለቤትነት መብት ሌሎቹም አጀንዳዎች ተነስተው ከብዙዎቹ ዋናዎቹ 1ኛ
የት የት ይቋቋሙ 2ኛ የባለቤትነት ጉዳይ ነበር ፣
ተሰብሳቢዎች ፣ስብሀት ነጋ ፣አርከበ እቁባይ ፣ አስገደ ገብረስላሴ ቴድሮስ ሓገስ ፣ ወለገብርኤል ታደሰ ፣ አጽብሀ ሀይለማሪያም ፣ በህረ የሚባል ፣ወለገብርኤል ሞዶረን ፣ሌሎችም ነበሩ ። ዋናውና አጨቃጫቂ አጀንዳ የነበረ የባለቤትነት ጉዳይ ነው። እዚህ ላይ እስብሀት ነጋና ቴድሮስ ሀገስ እና የነሱ ሎሌዎች የሆኑ ባለቤትነት በሚመለከት ። በህዝብ በጉባኤ የተመረጠ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስላለ ተጨማሪ ህዝባዊ መልክ እንዲኖረው ከህዝብ አምስት አርሶ አደሮች ፣ከታጋዮችም ታማኞች የሆኑ ከአምስት የማይበልጡ ተወካዮች እናስቀምጣለን ተባለ ።
በሌላ በኩል እኛ ያለንበት ደግሞ የቀረበ ተቃውሞ ፣ እኛ ከደፈጣ ተዋጊነት ተላቅቀን ወደ መንግስትነት ነት ተቀይረናል በመሆኑ ይህ አክስዮን በህዝብ ስም እየነገድን ቆይተን መንግስት ሲቀየር ወይ አንድ ቀን እንደቁማር ወግድ ለማለት ይቻላል።በህግም ንችላለን። ስለሆነ ኤፈርት የህዝብ የምንል ከሆነ ሁሉ ህዝብ የሼር እጣ ይኑረው ። ህዝቡ ባለቤትነቱ ካራጋገጠ በኃላ ገንዘቡ ምን ላይ ይሰማራ የሚል በመተዳደርያ ደንቡ ይቀመጥና ህግ ሆኖ ያገለግላል በኢትየጱያ ንግድ ህግ ብንልም በጠላትነት ተፈርጀን ባለመስማማታችን እስከ በነፍጥ ተማዝዘን ለአደጋ ተጋልጠን ነበር በጊዜው እግዚአብሄር አግዞናል እንኳን አልተጋደልን ።
ለሁሉም በኢትዮጱያ ንግዲ ህግ መሰረት ብንሄድ ይሻላል ብነለን ተቃውሞ ስናቀርብ ምን እያሉ ነው ያሉ ብለው እንደማዳመጥ ፈንታ የደርግ የኢሰፓ ፣የኢዲዩ ፣ እረ ስንት ፓርቲዎች የህወሓት ማእከላይ ከሚቴ በጠላትነት ከሚያያቸው ጋር በመፈረጅ ከዝግጅቱ አባረሩን እኛ ምን ከፋን ከህዝብ ሀሜት ድነናል ።
በመጠቃለል ዶክቶር ደብረጽዮን ይህ ደቡቅኝ ደቡቁኝ አይነት የኢሳእያስና የመለስ ሌጋሲ ተከትለህ ያደረከው ቃለመጠዮቅ ኃላም ይደረጋል ብለው የአለቃቸው ተከትለው ይሰሩበት የነበረ የነ ጸጋይ በርሄ ፣የአባይ ወልዱ ወደ ህዝብ ወርደው ፊት ለፊት ላለመቅረብ ይከተሉት የነበ ስልት ተከትለህ በዝግ ቤት ቃለ መጠዬቅ ማድረግህ ትተህ ወደህዝብ ወርደህ ፊት ለፊት የህዝብ የብሶት ጥያቄ ብታዳምጥ የተሻለ ነበር ። ደጉተር አብይ እኮ ወደ ህዝብ ወርዶ ያለው ተጨባጭ ችግር በመገንዘቡ ለቡዙ ጊዜ የሚሆን ስንቅ ይዞዋል በመሆኑ ዶክተር ወደህዝብ ውረድ ህዝብ ባለመዋያየት ህዝብ በግለጽ እያማህ ነው ። ባለፉት ሳምንታት የሙሁራን ፣የወጣቶች ፣የባለሀብቶች እላቹ እስዩም መሰፍን አለም ገብረዋህድ ፣ደኩተረ አዲስ ባሌማ እድሜ ልካቸው ከህወሓት አብረው ያረጁ የተለመዱት ሰዎች ነው የሰበሰባቹ ። ያትክክለኛ ሙሁር ተማሪ ፣ባለሀብት ፣ወጣት ፣ አስተማሪዎች ፣ሴቶች አላገኛችሁም ።በዚህ ምክንያት ወደ ህዝብ ውረዱ ።
ሌላ ለጥያቀውና መልሱ አቅራቢ ብርሀነ አባዲ በዜጎች ቀርበዋል የተባለው ጥያቄ እየፈራና እየከለሰ ያቀረበው ጥያቄ ምንም እንኳን ከ30 አመት በላይ ይዞት የመጣ ባህሪ መሆኑ ባውቅም ግን በሌሎች የግልና የመንግስት ፣የውጭ ሚዲያዎች ተሳትፈው የህዝብ የልብ ትርታ የሚያረካ በሆነ መንገድ በሆነ ሀቁን ይቆፈር ነበር ። ግን ምን ይሆን በህወሓት መንደር ለይህ ትውልድ ለግልጽነት አልታደልም ።
የተከበራቹ ወገኖቼ የኤፈርት ጉድ ቡዙ ጉድጓድ በተቆፈረ ነበር በዚህ አጭር ጽሁፍ ለመግለጽ ሰለማልችል ወጣት ቡቁ ለዜግነታችሁ ተቆርቋሪ የሆናቹሁና የግል ነጻ ሚዲያዎች ብትቆፉሩት መልካም ነው እላለሁ ። በብርሀኑ አባዲ የሚመሩ የመንግስት ጋዜጦኞች ግን ሀቅ ለመስማት አትጠብቁ ለራሳቸው ነጻ ያለወጡ ለህዝብ ያገለግላሉ ተብሉ አይታሰብ ።በተለይ የትግራይ ። የመንግስተና የህወሓት ጋዜጦኞች ለዚህ ህዝብ ትርጉም የላቸውም ።
a ይቀጥላል
ከአስገደ ገብረስላሴ
23 / 09 20 10