………#በመንበር_ዓለሙ ዘ-ላልይበላ………

#ኢትዮጵያ የማናት?

እናንተ በክፍ ቀን የተገኛችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ እናንተን አለማመስገን ፈፅሞ ኢትዮጵያን ከመጥላት የሚመነጭ ነው ምክንያቱ ደግሞ ሀገራችን ከመበታተን ለማዳን እየሰራችሁ ያላችሁት ተግባር እንዳመሰግናችሁ ያስገድደኛል።
ቀጣይ ግን ሳይውል ሳያድር መፈታት ያለበት ቁልፍ ጉዳይ በጋራ ትፈቱ ዘንድ በወክላቹህ፣በሾማችሁ እና ባከበራቹህ ህዝብ ስም እማፀናቹህ አለሁ?
*አገራችን ኢትዮጵያን ብዙወች እንዲጠሉባት፣ብዙወች እንዲሳደዱባት፣ጥቂቶች እንዲፈነጩበት፣ጥቂቶች ብዙወችን እንዲያሳድዱባት በልካቸው ሰፍተዋታል። ይህን እንቆቅልሽ ለመፍታት የምታደርጉትን ጥረት እያመሰገንሁ አሁንም ግን በብአዴን እና ኦህዴድ ከፍተኛ ትግል ዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው በተሾሙበት ማግስት አማራ ከኦሮሞ እንዲገለል እና እንዲሰደድ፣አማራ ከቤኒሻንጉል እንዲፈናቀል የተደረገበት ቁማር አልተፈታም ይልቅስ ለአለም በሚሰቀጥጥ ሁኔታ የ14 ዓመት ህፃን አበጥር ወርቁን ብልት ቆረጡት ይህን ድርጊት የፈፀሙ ሰወች በህግ ይጠየቅአሉ በሚል የሚታለፍ ሳይሆን ትልቅ ስራ መስራትን የሚጠይቅ ተግባር ነው። በዘለቄታው አማራ በቤኒሻንጉል ተከብሮ የሚኖርበት ስራ ካልተሰራ በቀር ብልቱ እየተሰለበ፣ሀብት ንብረቱ አየተዘረፈ የሚኖርበት ህግ ካልተፈጠረ መብቱን በጉልበት ማስከበሩ ግድ እና ብቸኛው አማራጭ ይሆናል እኔ ግን ይህ እንዳይሆን ምርጫየ ነው።
…….
ብዙወች የሚሸማቀቁባት ኢትዮጵያን በልካቸው የሰፏት ሽማግሌወችም ከስልጣን በቃችሁ የተባለበት እርምጃ መልካም ቢሆንም ከሚኒስተርነት የወረደን ባለስልጣን በጥገናዊ ለውጥ ካንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም በማዛወር አማካሪ ማድረግ ”አልሸሹም ዘወር” ነውና ነገሩ አደጋው እንዳይከፋ ፈራሁ?
ይችን ሀገር በአዲስ ትውልድ በአዲስ አስተሳሰብ ለመምራት ስርነቀል ለውጥ እንጅ ጥገናዊ ለውጥ መፍትሄ አይደለም።
……
#እናንተ በምትመሩት መንግስት
*አማራ ለዓመታት ከኖረበት ቢኒሻንጉል ተፈናቅሎ ባህርዳር ከትሟል
*አማራ ከኦሮሞ ተፈናቅሎ ራያ ከትሟል
*አማራ ከአፋር ተፈናቅሎ ባቲ ወረዳ ከትሟል
*አማራ በራሱ መሬት በወልቃይት ለምን የፋሲል ማልያ ለበስህ፣ለምን አማርኛ ሙዚቃ ትከፍታላችሁ፣ለምንስ በአማርኛ ታወራላችሁ እየተባለ ባላንጣ ተደርጓል
……….
#እናንተ በምትመሩት መንግስት
*ኦሮሞ ከሶማሌ ተፈናቅሎ ሱሉልታ ከትሟል። ይህ ለምን ሆነ? ከጀርባስ ማናለ?
የጌታቸው አሰፍን ደህንነት ጠይቁት።
ይህን የጥላቻ መንፈስ ማን ዘራው? ለዚህ መፍትሄው ምንድ ነው? ከዚህ መፈናቀል በስተጀርባ ያለው #ጋርድኤል ማነው? #(ጋርድኤል ማለት አዳምና ሄዋንን ዕፀ በለስ እንዲበሉ ያሳሳታቸው ሰይጣን ስም ነው።)
ህዝቡ በደም፣ባጥንት ተከፋፍሎ አሳዳጅ እንዲሆን ማን አሳሳተው ታሪክ ይፍታው……?
* (አብይ፣ገዱእናለማ) እናንተ የኢትዮጵያ መሪ ኮከቦች ባለ ጥልቅ አላማወች ናቹህ። 27 ዓመት የተጣመመውን እንድታርቁ የታሪክ አደራ የተጣለባችሁ ናችሁ ፈጣሪም ሚስጥሩን ይገልጥላችሁ፣ጥንካሬውን ያድላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው።
…………..
ዳሩ ከኛ ወዲያ ላሳር የሚሉ ሴረኞች አሉና ከነሱ ወጥመድ ለማምለጥ
#እርምጃ 1:- #የመላው ኢትዮጵያዊያን ህዝብ ጥያቄ የሆነውን በአንድ ብሄር የበላይነት የተያዘውን #የመከላከያ እና#የደህንነት ጉዳይ በጥበብ መፈተሽና ማስተካከል የብሄር ስብጥር እንዲኖረው በማድረግ ስራችሁን ጀምሩ
……….
#ሙሴ_የፈርኦን ልጅ ተብሎ ፤ የፈርኦንን እንጀራ እየበላ ፤ የፈርኦንን ስርአተ መንግስት እየተጋተ ፤ ሲገባና ሲወጣ እያጎነበሰ ቢያድግም በፈርኦን ወጥና እንጀራ ተደልሎ የፈርኦንን ባርነት እስከወዲያኛው ድረስ መሸከም አልፈቀደም ።ወገኑን ታድጓል ። የፈርኦን ልጅ ሆኖ ያደገ ሁሉ የፈርኦን አገልጋይ ሆኖ ላይዘልቅ እንደሚችል ሙሴ ምሳሌ ነው። እናንተም ከኢህአዴግ ተፈልፍላቹህ፣በኢህአዴ ተኮትኩታችሁ ብታድጉም #የነበረከት_አቦይ ስብሀት፣አባይ ፀሀየ፣አዲሱ፣ሳሞራና አባዱላ ወጥ እና እንጀራ ዩሉኝታ ሳያስይዛችሁ፤ እነሱ ሰፍተው በሰጧቹህ የዲሞክራሲ ምህዳር ሳይሆን በአዲስ አስተሳሰብ ይህን ህዝብ ማዳን የጃቹህ መዳፍ ላይ ነው።
*እናንተ የኢትዮጵያዊያን ሙሴ ሁኑ የሙሴ ዕድል ቢገጥማችሁ እንኳን ተረኞች እያሱወች እንቀበል አለን። እናንተ በመልካም ስራችሁ እስከወዲያኛው ትከብራላቹህ።
..
#እርምጃ 2:-የተፈናቀሉትን በፍጥነት ወደ ቦታቸው መልሱ የተዘረፉትን አስመልሱ። ዘለቂ መፍትሄም አስቀምጡ፣ አፈናቃዮቹ ላይ ህጋዊ ዕርምጃ ውሰዱ፣ #የኦሮሞና የአማሀራ ህዝብ የሞተለትን እና የታሰረበትን መሰረታዊ ጥያቄ ባፍጣኝ መልሱ። በኦሮሞ፣ቤኒሻንጉል፣አፍር እና ሌሎች ክልሎች የሚኖሩ አማራወች ማንነት ይከበር። በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞወችም በተመሳሳይ ማንነታቸው ይከበር።
………….
#እርምጃ 3:- ከሁሉ በላይ በርካታ አማራወች ታፍነው የጠፉበት፣በርካቶች የታሰሩበት፣በርካቶች የሞቱለት በርካቶች የተሰደዱበትን #የወልቃይት ህዝብ እና መሬት አለመፍታት ግን የጅልነት ሁሉ ትልቁ ጅልነት ነውና ቶሎ ድረሱለት። ህገመንግስታዊ መፍትሄም ይበጅለት።
ምናልባትም ህገ መንግስቱ መሻሻል ካለበትም በጃቹህ ነውና አሻሽሉት ከሰሞኑ ቡሩንዲ አዲስ ህገ-መንግስት አፀድቃለች ይህ ተግባር ለሀገራችን ትልቅ አብነት ነው።
………
በመጨረሻም አይን ያወጣው #ኢ-ፍታዊ የሀብት ክፍፍል ይቁም ለተጎዱ ክልሎች ማካካሻ መሰረተ ልማት እና ኢንዱስትሪ ይስፍፍላቸው። ”ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጥበታል” እንዲሉ በርግጥም ከአማራ ምድር የሄደ መብራት ለሌላው ብርሀን እየሰጠ አማራ በኩራዝ የሚኖርበት Systematic የበላይነት ይቁም። በአማራ መሬት አማራን የማይጠቅም የባቡር ሀዲድ በቃ ይባል (ኮምቦልቻ ጭፍራ ወልዲያ መቀሌ የባቡር ሀዲድ በሰሜን ወሎ ህዝብ መሳለቅ እና መቀለድ እንጅ የባቡር ሀዲዱ ወልድያን አይነካትም ተጠቃሚም አይደለችም)።
ይህ ሲሆን ኢትዮጵያ የማናት? የሚለው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ያገኛል። ኢትዮጵያም የሁላችን ትሆናለች።
የጥላቻችን ግንብ ፈርሶ እንደ ድሮዋ ኢትዮጵያ አንተ ትብስ አንች ትብሽ ብለን ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ዘር፣አጥንት፣ደም፣ብሄር፣ሀይማኖት ወ.ዘ.ተ ሳይገድበን በፍቅር ተከባብረን የምንኖርባት የሁላችንም ሀገር፣የሁላችንም እናት ኢትዮጵያ ትሆናለች።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!