ግዛቸዉ አዳነ በዘጠኝ ጥይት ተገደለ። የወገራ አዉራጃ የቀድሞዉ አስተዳዳሪ የቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ አቶ ግዛቸዉ አዳነ መኮነን በወልቃይት የአማራነት ማንነት እንቅስቃሴ አጋዥ ሚና ነበረዉ። ግድያዉ የተፈፀመዉ በህዉሓት ወታደሮች ነዉ። የወልቃይት የአማራነት ኮሚቴ ጥያቄያቸዉን ለፌዴሬሽን ምክርቤት ለሁለተኛ ጊዜ ማስገባታቸዉን ተከትሎ የወልቃይት አጀንዳ ዳግም አገርሽቷል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአማራ ክልል መንግስት የሰጠዉ አስተያደት የለም።
ፋሽሽቱ የትግሬ ወያኔ አቶ አዳነ መኮነን የገደለው ከወልቃይት ወደ ጎንደር ሲጓዝበት በነበረት ወቅት በ9 ጥይት ተኩሶ መሆኑን ለማቀቅ ተችሏል።
በአዲ ረመጥ ከተማ ፌስቡክ ላይ ጽፋችሁዋል የተባሉ ወጣቶች ታሰሩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የኮማንድ ፖስት አባላት ነን ያሉ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች በወልቃይት ወረዳ አዲ ረመጥ ከተማ ነዋሪ የሆነውን ወጣት ፈቃዴ አሰፋን ይዘው በማሰር፣ ለብሶት የነበረውን የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ማሊያን አስወልቀው በቅደድና በእግራቸው በመርገጥ በመጨረሻም ወደ እስር ቤት ልከውታል። ወጣቱ፣ የወልቃይትን ጉዳይ አንስቶ በድፍረት እንደሚጽፍ፣ በሚጽፋቸው ጽሁፎች እንደማይጸጸትና ይቅርታ እንደማይጠይቅ መናገሩን አብሮት ተይዞ የነበረው በንግድ ስራ የሚተዳደረው ማማዬ የተባለው ሰው ተናግሯል።
ቢራ የማከፋፈል ስራ የሚሰራው ማማዬ ፣ የመከላከያ አዛዦቹ ድግሳቸውን ስፖርንሰር እንዲያደርግላቸው እንደጠየቁት፣ እርሱም ከአንድ ወይም ከሁለት ሳጥን በላይ ስፖንሰር ማድረግ እንደማይችል እንደገለጸላቸው፣ ኮ/ል ደመቀ ሲፈቱ ግን እስከ 15 ሳጥን ስፖንሰር እንዳደረገ በመገልጽ፣ በኮሎኔል ደመቀና በእርሱ ላይ ጸያፍ የሆኑ ስድቦችን እንደተሳደቡና ከ2 ሰዓታት ከ40 ደቂቃ እገታ በሁዋላ እንደፈቱት ተናግሯል።