የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ?ኤጆሌ ቢያ አካም ጂርተን! ወደፊት ኦሮምኛ እንግዲህ ሌላው የፌደራል ቋንቋ መሆኑም አደለ ትንሽ ትሽ እንማራ  (ጢቆ ጢቆ/ጢኖ ጢኖ ሀበረኑካ)፡፡ ሰሞኑን ትንሽ ነገሮች የተደበላለቁ መሰለኝ፡፡ እስካሁን እነለማ ድራማ እየሰሩ ነው የሚሉ ብዙዎች ነበሩ፡፡ እንደሚመስለኝ እነለማ እያደረጉ ያለውን ሳያዩ ቀርተው ሳይሆን ሥራቸው ባይሳካ ስለሚመኙ ይመስላል፡፡ ከቀን ወደ ቀን ግን እነለማ አብይ ያሰቡትን ይበልጥ እያጎሉት ሲመጣ እንዴ እነዚህ ሰዎች የምር ሊሳካላቸው ነው እንዴ የሚል ሥሜት ያደረባቸው ግራ ገብቷቸዋል፡፡ አቦ ማል ወያ (አቦ ምን ይሻላል)?

እስኪ ወደ ቁም ነገሬ፡፡ ወገኖቼ ይህን የምናገረው ከልብ ኢትዮጵያዊነት ለሚሰማችሁ ነው፡፡ ዛሬ ለመተቸትም ሆነ ለማመስገን የበቃንበት ክስተት ብዙዎች ሕይወታቸውን ያጡበትን፣ ብዙዎች ከሞት ያልተናነሰ መከራና ስቃይ የተቀበሉበትን እጅግ መራራ የሆነ ጊዜ አልፎ(ሁሉም አለፈ ባልልም) ነው፡፡ አሁንም ሙሉ በሙሉ የተቋጨ ነገር ባይሆንም ግን ድል ወደ እኛ መዝናለች፡፡ በምንም መልኩ አሳልፈን ለሌሎች መስጠት የለብንም፡፡

የሆነው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንጂ ሰዎች ስለፈለጉም አይደለምና ወደኋላ የሚመለስ ነገር የለም፡፡ አሁን የምናየውን እውነት በቅርቡ ከመስከረም በፊት እንኳን ይሆናል ብሎ መገመት ይቅርና ማለምም አይቻልም ነበር፡፡ እጅግ ክፉ የሆኑ ሰውኛ ፍጡሮች የዚህን ያህል እድል እንዲኖራቸው ሳናውቀው ተዘናግተንላቸው ነው የሆነው ሁሉ የሆነው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በጎንደር የነበረው የሰላማዊ ሰልፍ የፈጠረው የኢትዮጵያዊነት ጥሪ ሲደወል ነው ነገሩ ሁሉ የተገለጠው፡፡ እስከዚያ ድረስ እውነቱን ብናውቀውም አዚም ስለተደረገብን ፈዘን ነበር፡፡ ጎነደሮች የደወሉት ደወል ምላሹ ከአዳማ ሲሰጥ ነበር በምን ያህል አገርን በማፍረስና ሕዝብን በማለያየት 40 ዓመት ሲያሴር የኖረ ቡድን ስንት ዓመት የለፋሁበት ሴራዬ ሊናድ ነው  ብሎ በድንጋጤ ሲያብድ ያየንው፡፡

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ለአገርህና ሕዝብህ ዘብ ቁም፡፡ ከተነዳው አትነዳ፡፡ በውዥንብር አንታመስ፡፡ እየተስተዋለ፡፡ አሁን እንኳን በኖርዝ አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ አብይ ለመገኘት ጥያቄ አቀረበ ተብሎ ሕዝብን ለመሰለልና በውዥንበር ለማደናገር ድራማ ሲሰሩ የነበሩትን አስተውል፡፡ አብይ ልምጣም ብሎ አልጠየቀም፡፡ ቁማሩን ሲጫወቱ የነበሩት በአሜሪካ የወያኔው ኢምባሲና ራሱ የስፖርቱ አዘጋጅ ቦርድ ተብዬው ነበር፡፡ በኋላም የሕዝብ አስተያየት በሚል ድምጽ መሰባሰብ ጀመሩ፡፡ የድምጹን ውጤት አይታችኋል፡፡ እሱም የቁማሩ አንድ አካል ነበርና፡፡ ከዛም ውድቅ አደረግን የሚል ወሬ ማናፈስ ጀመሩ፡፡ ልብ በሉ ጠ/ሚኒስቴሩ እንኳንስ ሊጠይቅ ምን እየሆነ ስለዚህ ጉዳይ ሊሰማም የሚችልበት እድል የለም፡፡ እንደኛው ከፌስቡክ ከአየው እንጂ፡፡ የወያኔ ኢመባሲ የኢትዮጵያ ጠላት ወሮበሎች የሙሉበት እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ለእነዚህ ሥርዓትም ነውርም የላቸውም፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ተመልከቱ 65 ለ35 የደጋፊ ድምጽ እያለ ውሳኔውን ከሕዝብ ድምጽ በተቃራኒው ሆነ ብለው ሌላ ውዥንብር የሚነዙ ተነሱ፡፡ ከአላማዎቹ አንዱ አስቀድሞም ይሄ ነበርና፡፡ እንጂማ አብይ እንደማይመጣ ቀድሞውንም እነሱ ያውቁት ነበር፡፡ አብይ እንደወያኔ ባለስልጣን በፌስቡክ በሚሰጥ ፍላጎትና አስተያየት አደልም የሚመራው በራሱ እቅድ እንጂ፡፡  የእኛ መጀመሪያ እራሱ አቅዶ ከሆነስ በሚል ነበር፡፡ ያም ቢሆን አብይ እንዲመጣ ስላልፈለግን ይህን የተቃወምንው፡፡ ምን አልባት አብይን ለሌላ ሴራ እንዳይጠቀሙ ከሚል ማለት ነው፡፡ ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ግን እባካችሁ ሁላችሁም ከስሜት ሰከን ብላችሁ ወያኔና ደጋፊዎቻቸው የሚሰሩትን ደራማ በትኩረት እየተከታተላችሁ አፋቸውን አስዘጉ፡፡ እድል አትስጧቸው፡፡ አሁን እየሆነ ያለው በጣ ብስለትን እየጠየቀ ያለ አካሄድ ነው፡፡ ለዛ ሁላችም በአለንበት ወያኔ ለ27 ዓመት የዘረጋችውን የሴራ ድር መበጣጠስ አለብን፡፡ መሰለል አለብን፡፡ ጥሩና ለስላሳ ነገር እያወሩ ውስጣቸው መርዝ የሚረጭ ብዙዎች ናቸው፡፡ በቅርቡ ግንቦት 20 በሚል በመቀሌ የተደረገውን ስብሰባና ንግግሮችን አድምጣችኋል፡፡ ለብዙው ኢትዮጵያውያን ወያኔ እንደዚያ የሚያስብ ሰው መሰል ፍጡራን እንደሆኑ ባለማወቃቸው ገርሟቸዋል ግን እኮ ብዙዎች በየአለንበት ይሄን መሰል አስተሳሰብ ይዘው ነው ከእኛ ጋር ሰው መስለው የሚኖሩት፡፡ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘመቻዊ አካሄድ ራስን ጠብቅ፡፡

ሳምንቱ አንዳርጋቸው የተለቀቀበት በመሆኑ ብዙ ሌላ አስገራሚ ነገሮች አይተናል፡፡ ወያኔ ትግሬዎች እንዴት ቪዛ የሌለው ሰው አገር ውስጥ ይቆያል አሉ፡፡ እንዴ ዛሬም ለራሳቸው እንኳን ቢያስቡ ጥሩ ነበር፡፡ አገሩ የእኛ እነሱን ሲጀምር የሚያገባቸው የለም፡፡ ትግሬ ወያኔ ወንበዴ የኢትዮጵያ ጠላት እንጂ ኢትዮጵያዊ አደለም፡፡ ከጅምሩ እኮ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ሲዋጉ የኖሩት፡፡ አሁን ሳስበው የደርጉ ጊዜ ጦርነት አንኳን ሳናውቅ ነው ባድሜ ተያዘች ብሎ በኢትዮጵያዊነት ሥም ያለቀውን ወገናችንን ሳስብ እበሳጫለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ከየአለበት ባድሜ ተወረረች ብሎ ሲዘምት የትግራይ ወጣት ለኮምፒተር ስልጠና ሲመለመል ነበር፡፡ ከዛም ኢትዮጵያንውያንን ለመሰለል በመረጃ መረብ ደህንነት ውስጥ በመሰግሰግ፡፡ በአገር ጉዳይ የአለውን አንድነት የተመለከተው ማቹ የወያኔውን ቡድን መሪ መለስን ከዛ ጦርነት በኋላ ያደረጋቸውን አስተውሉ፡፡ የሕዝቡ በአገር ጉዳይ ያለው ስሜት አስደንግጦት ነበር፡፡ አይምሰላችሁ ብዙ ተሸውደናል፡፡ ሲጀምር ያን የሚያህል ጦርነት ድራማ መሆኑ ሳይገባን ነው፡፡ ብዜ ዜጋችን አለቀ፡፡ ከዛ በኋላ ግን የሆነውን አስተውሉ፡፡ በዛ ጦርነት ብዙ ሥራ የሰሩ የተሾሙ መሰላችሁ፡፡ የሕዝቡ አንድነትና የአገር ወዳድነት ስሜቱ ያስደነገጠው ወያኔ ከዛ በኋላ በወታደራዊ እዝ ሰንሰለት ውስጥ ከትግሬ ወያኔ ውጭ በመሪነት እንዳይኖር ከማድረጉም ሌላ ወሳኝ የተባሉ የደህንነት መዋቅሮችንና የገንዘብ መስመሮችን ሁሉ በትግሬ ሞላው፡፡ አስተውሉ ከባድሜ በኋላ የሆነውን ሁሉ፡፡ በእርግጥም የባድሜው ጦርነት የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር ከፋፍለንዋል ብለው አስበው ስለነበር መከፋፈል አለመከፋፈሉን ለማረጋገጥ ነበር፡፡ ግን እንዳሰቡት አልሆነም፡፡ ይህ ድራማ ዛሬም ያልገባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ በኤርትራ በኩል ለኢትዮጵያ ነጻነት እንታገላለን የሚሉ ቡድኖች ተሸውዳችሁ ከሆን አሁን ስሙኝ አውቃችህ የሴራው አካል ለመሆን ፈቅዳችሁ ከሆን ግን ምርጫችሁ ስለሆነ ግፉበት፡፡ ግን መቼም ቢሆን ከዚህ በኋላ እድል እንደማንሰጣችሁ አወቁ፡፡ ወያኔና ሻቢያ አንድ ናቸው ስንል ለሰሚው ሁሉ ቀልድ ይመስለዋል፡፡ ሰዎቹ ወንበዴዎች እንጂ እንደ መንግስት ለሕዝብና አገር ጉዳያቸው አደለም፡፡ ኢሳያስን የኢትዮጵያ ሰራዊት እንዳይዝ መለስ መከልከል ብቻም ሳይሆን ሰራዊቱ እንዲያልቅ ልዩ ሴራ ነበር የሰራው፡፡ ኢሳያስ በኤርትራ እስከዛሬ ኖረ የአለቀው በኤርትራ በኩል ሕዝብ ነው በእኛ በኩል ከሕዝብም ትግሬ ያልሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ልብ በሉ ጦርነቱ የተጋሄደው ግን በትግራይ ክልል ነው፡፡ የአንዳርጋቸው መያዝ ዝም ብሎ  አጋጣሚ አልነበረም፡፡ እንዴት በአለ ሁኔታ ነው አንድ የሌላ አገር ዜጋ በሌላ አገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ ሊያዝ የሚችለው፡፡ ኤርትራ ውስጥ እንዳይያዝ የተፈለገው ድራማው እንዳይነቃ ነበር እንጂ መሪ ተውኔቱ የተደረገው በኤርትራ በኩል ነው፡፡ ይህ ድራማ ግልጽ ሆኖ መውጣት አለበት፡፡ አንዳርጋቸውም የሚጠረጥራቸውንና ያለፈባቸውን ሁኔታዎች በግልጽ ለሕዝብ ማሳወቅ አለበት፡፡ ለአንዳርጋቸው መፈታት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ዜጋዬ ያለችው ኢንግሊዝ ራሷ የነበራት አስተዋጽኦ ሊያውም ከአለ ኢምንት ነው፡፡ በአጠቃላይ አንዳርጋቸውም ሆነ ሌሎች እየተፈቱ ያሉት የአውሬው ጉሮሮ በሕዝብ ክንድ ስለታነቀ ነው፡፡

ዲያስፖራው የትግሬ ወያኔ በሚያቀርቡለት ውዥንበር መወናበድ የለበትም ይልቁንም ከዚህ በኋላ ዋነኛ ሥራው  መሆን ያለበት ከትግሬ ወያኔ የፀዳ ኢምባሲ በየሚኖርበት አገር እንዲኖረው ጥነክሮ መስራት ነው፡፡ በሚኖርበት ሁሉ ለአገሩና ሕዝቡ ቁርጠኛ ሆኖ መቆም ነው፡፡ ሴረኞችን ከመሰለል እስከ ማገት የደረሰ ሥራ ላይ ሊሰማራ ይገባዋል፡፡ በትግሬ ወያኔ የወንበዴ ቡድን ሴራ ውስጥ ብዙዎች አሉ፡፡ እነ አብይን እንዳናምናቸው ብዙ ነገር የሚነዙት እንደውም በቀጥታ ትግሬ ሳይሆኑ በትግሬ ወያኔው ቡድን የተቀጠሩ ናቸው፡፡ እስካሁን አንዳንዱ መስሎት ነው በሚል ዝም ብለናል ከዚህ በኋላ ግን በሴራው ድራማ የሚቀጥሉ በግልጽ የኢትዮጵያና ሕዝቦቿን መነሳት የማይፈልጉ ወይም በኢትዮጵያውያን እልቂት ኑሮአቸውን የገነቡ ናቸው፡፡

አብይ 60 ቀን ሆነው በእርግጥም የሠራው ሥራ በ6 ዓመትም ይሆን ያልመሰለን ነው፡፡ እርግጥ ነው ሥራው የተጀመረው ቀደም ብሎ ነው፡፡ አሁን አብይ እየሰራ ያለው ቀድሞ የተጀመረውን ማፋጠን ነው፡፡ ዛሬ አብይ በመሪነት እየሰራውና በአዳዲስ ሀሳቦች እያደመቀው ያለው የኢትዮጵያዊነት ትንሳዔ ዘመቻ ችቦውን ያቀጣጠለው ለማ ነው፡፡ አይምሰላችሁ ለማ በባሕር ዳር ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ስላለ አደለም፡፡ ነገሩ ከመጀመሪያውም ስለገባውና ቀን እየጠበቀለት የነበረው ሕልሙን የኦሮሚያ ፕሬዘደንት ሲሆን ከውስጡ አውጥቶ ወሮበሎቹ ኢትዮጵያዊነቱን አስጥለት ለነበረው ወገኑ ሁሉ ልብ ውስጥ አሰራጨው እንጂ፡፡ ለማ ይህ ሲያደርግ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ ከጎኑ ዛሬ መላው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት መሆኑ አጋጣሚው እንዲጠቀም አገዘው እንጂ ፈተናው ግን ቀላል አልነበረም፡፡ በአጭሩ ለማ የአባቶቹን አገር ከጥፋት ታደጋት! አስታውሱ አራቱ ቡድኖች ስብሰባ በነበረበት ወቅት የነበረውን፡፡ ለማ ብቻውን አገሬን በእኔ መቃብር ላይ ታፈርሷታላችሁ የሚል ግልጽ መልዕክት ነበር ያስተላለፈው፡፡ ያን ወቅት ለማ እንኳን እሱ ሕጻናጽ ልጆቹ ሳይቀሩ ኢላማ ተደርገው ነበር፡፡ ለማ ዛሬ ከጥፋት ለተረፈቸው ኢትዮጵያ አንድ ልጇ ብቻ አደለም! ሰሞኑን ለማ የአመቱ በጎ ሰው በሚል ሊሸለም እንደሆነ ሰማን! ያዓቅማቸውን ለማሰብ የሞከሩ መልካም አደረጉ ግን ይህ ሰው ያንስበታል፡፡ ሌላው ሰሞኑን ለማ እኛ ነጻ አወጣናችሁ በማለት ተቃዋሚዎችንና ዲያስፖራ በተለይም ኦሮሞ ነን የሚሉትን ዘልፏል በሚል መቼም ማፈር የለምና ሊተቹት ሞከሩ፡፡ ነገርናችሁ አገሪቱም ሆነ ሕዝቧ እናንተ አፈራረሳችኋታል አሁን ያለችው አገር ለማ ከተበታተነችበት ሰብስቦ የገጣጠማት ናት፡፡ ትንሽም ቢሆን በሥራ አሳይተናል ነው ለማ ያለው፡፡ ትንሽ አደለም አገርንና ሕዝብን ማዳንን የሚበልጥ ምንም ነገር የለ፡፡ ብዙዎችን ፍጹም ከአልነበራቸው ተስፋ ወደ ሕይወት መመለስ ትንሽ አደለም፡፡ የተግባርም አይነት አለው፡፡ እርግጥ ነው ለማም ቢሆን በራሱ ሊመካ አይስፈልገውም ይህ ሥራው ከልዑል አምላክ እግዚአብሔር የተሰጠው ስለሆነ፡፡ ስታስተውሉም የመጣንባቸው ሂደቶች እውን እውንም የማይመስሉ ናቸው! አው እግዚአብሔር ያለበት ሥራ እንዲህ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሥራ የተመረጡ ለማን ጨምሮ ሌሎች አብይ ገዱም በየተሰማሩበትና በየመጡበት ለሥራው ሥኬት ከልባቸው እንጂ ለማስመሰል ስላልሆነ ነው፡፡ እስካሁንም ፈተናዎች አልቆሙም ድል የተደረገው አውሬው ቡድን አሁንም አልሞተምና፡፡ በወዲያ በኩል ያለውን ገዱን ረስቼው አደለም፡፡ በመጀመሪያ ለማ ስል በአጠቃላይ ከእሱ ጋር የቆሙትን ሁሉ ነው፡፡ ገዱም አንደዛው ነው፡፡ ገዱና ለማ ተመሳሳይ አቋም ላይ ያሉ መሪዎቻችን ሲሆኑ አሁን ለተፈጠሩት ተስፋ ሰጭ እድሎች ግን ለማ መሪ ተዋናዩ ነበር፡፡ የሁለቱ መሪዎች ጥምረት ብቻም ሳይሆን የአቋም ፅናት ግን ግድ ነበር፡፡ እናመሰግናለን

የአብይ ወደጠቅላይ ሚኒስቴርነት መምጣት ደግሞ ለዚህ ቦታ አብይ ስላስፈለገ ነው፡፡ እርግጥም እየሆነ ያለውን ላይ የሚገርም ሂደት ነው፡፡ አብይ በልበሙሉነትና በደስታ ኢትዮጵያዊነትን እየዘመረ ነው መሪ እየሆነ ያለው፡፡ ወገኖቼ አንኳንስ በሕይወት አጥንታቸውም በሰው አገር አይቀር የሚል ሀሳብ እንዲኖረው ነው ከላይ ወደታች የሚፈስለት ሀሳቡ፡፡ በጎ ነገር ስታስብ ከመልካምም በላይ የሆነው መልካምነት ይገለጣል፡፡ አብይ በሊቢያ የታረዱ ወገኖችን ወደ አገር ቤት አጽማቸውን የመለሰ ዕለት ታላላቅ ሚዲያዎች ላይቪ እንደሚቀርጹ ጠብቁ፡፡ ይህ የሆነ እለት አለም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ምን አይነት ሕዝቦች ናቸው በሚል ይደመማል፡፡ ያኔ የናፈቅነው የኢትዮጵያ ታላቅነት ትንሳዔ መጀመሩን ሁሉም አምኖ ይቀበላል፡፡ ይህን ሀሳብ ከእራሱ ያፈለቀው አይመሰልኝም፡፡ አንድምታው ጥልቅና እጅግ ታላቅ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ሲሆን በልዩ ዝግጅት እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ እነዚህ ዜጎቻችን የአሳለፍውን ክፉ ዘመን ሁሉ ምልክት እንዲሆኑ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ተስሎ እንዲኖር በታላቅ አደባባይ ወይም ልዩ ሥፋራ ሀውልታቸው ይቆማል፡፡ ከዛች ዕለት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ወደአገራቸው ይሰበሰባሉ፡፡ ትንቢት አደለም፡፡ በአብይ የመጣውን ሀሳብ እንጂ፡፡

እንግዲህ አብይ እስካሁን ኢትዮጵያውያንን ማረጋጋት ነበር ዋነኛ ተግባሩ፡፡ አፋጣኝ እርዳታ ለሚፈልጉትም መድረስ፡፡ ለቀሩት ይቀጥላል አሁን ግን ወደዋናው ጉዳይ ይገባል፡፡ ዛሬ አስቸኳ የተባለው ሕገወጡ የሽብር አዋጅ እንዲነሳ ተወስኗል፡፡ ሌሎች በዚኅ አሁን ልገልጻቸው የማልፈልጋቸውን እርምጃዎችም ሊወስድ እንዳሰበ የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡ ለወሮበሎቹ ብዙ ድንጋጤ ነው! ኢትዮጵያ የራሷ ሰራዊት ከ27 ዓመት በኋላ እንደሚኖራትም አብይ ፍንጭ ሰጥቶናል፡፡ እስከደርግ መውደቅ የኢትዮጵያ ሰራዊት ነበር ከዛ በኋላ ግን የወሮበላው ቡድን ተቀጣሪ ነፍሰ ገዳዮች ነበሩ አገሪቱ ሰራዊት አልነበራትም፡፡ ይህ ቀልድ ይመስላል ግን የሆነው እውነት ይሄና ይሄ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ ሁሉ በያላችሁበት አላስፈላጊ ውዥንበር ውስጥ ገብቶ የጣላት መጠቀሚያ ከመሆን ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ለአገርንና ሕዝብ ራሳችሁን ዘብ አቁሙ፡፡ ድጋፍ አድርጉ፡፡ በአጭበርባሪዎች ድራማ አብይ ንግግር ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ የሚሏችሁን ሳይሆን እራሳችን በክብር በምናዘጋጀው መድረክ አብይ ለዜጎቹ በአሜሪካም ይሁን በሌሎች አገሮች ተገኝቶ ሀሳቡን ሊያጋራን እኛም ሀሳባችንን እንድናገራው እናስብ፡፡ አገር መሪ አንደ ተራ ምናምን በወሮበሎች ፍላጎት አይመራም፡፡ የረሱ ዕቅድ አለው፡፡ ለዛ ጊዜ ሰጥተን በታቀደ ወቅት እኛው እናደርገዋለን፡፡

በመጨረሻም ሀሳብ በሚቀጥለው ምርጫ እነለማ አብይ ገዱ የመሳሰሉትን ሰዎች በምንም ተዓምር ልናጣቸው አንፈልግም፡፡ ስለዚህም አንድ የአሉበት ቡድን ከወያኔ ትግሬ የጸዳ እንዲሆን ሁለት በፓርላማ የሚመረጥ ጠ/ሚኒስቴር ሳይሆን በቀጥታ በሕዝብ የሚመረጥ እንዲሆን፡፡ ሶስት ኢጆሌ ቢያ (የአገሬ ልጆች) ወይም አገሬ ኢትዮጵያ (ኢትዮጵያ ቢያኮ)  የሚል ፓርቲ አቋቁመው ለብቻቸው ጽድት ብለው እንዲወዳደሩ፡፡

ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ! አሜን!