የኦሕዴድ ሊቀመንበር ዶ/ር (ሊ.ማ.) ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ለማ መገርሳ በወያኔ ተደርሶ የተሰጣቸውን ድራማ (ትውንተ ኩነት) በመሪ ገጸባሕርይ በሚተውኑት ትወና ሕዝቡን ማጃጃል ችለው ጥቂት በማይባለው ሕዝብ ዘንድ እንደለውጥ ሐዋርያት መቆጠራቸው እና እያፈናቀሉት፣ እያስገደሉት ላለው አማራ ትኩረት መነፈጉ የልብ ልብ ሰጣቸው መሰለኝ “ኦሮሚያን ከአማራ እና ከአማርኛ እናጸዳለን!” ብለው የተነሡበትን ዘመቻ ቀጥለውበት ሰሞኑን አማራን ማፈናቀሉን አጠናክረው ተያይዘውታል፡፡ ለምሳሌ ያህልም መሰንበቻውን ከተለያየ ሥፍራ ያፈናቀሏቸውን ትተን ይሄንን ሁለት ሦስት ቀን ከቄሌም እና ከደዴሳ የተፈናቀለውን በርካታ ወገን መጥቀስ ይቻላል፡፡
የአንዱን ሥፍራ ብቻ በዝርዝር ለመመልከት ያህል፦
በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ ሶቦ ቀበሌ ለረጅም ዓመታት ከኖሩበት “ለቃችሁ ካልወጣችሁ!” በሚል በቀደም ግንቦት 22 ቀን 2010ዓ.ም. ዐሥራ አንድ አባወራዎች ታስረዋል። የታሰሩት ከነሚስቶቻቸው ቢሆንም በማግስቱ ሴቶቹ ተለቀዋል። አርሶ አደሮቹ ከዚህ በፊት 45 ሄክታር (ቃዳ) የሚጠጋ መሬት የተቀሙ ሲሆን አሁን የታሰሩት ቀሪውን መሬት አርሰው እና አዘጋጅተው ለመዝራት እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት እንደሆነ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት አርሶ አደር አባወራዎች፦
1.አበባው ከበደ
2.ጌታነህ ግዛው
3.ግርማ አባተ
4.ሃብታሙ ባፍሎ
5.ዓለሙ ግሩም
6.ተመስገን ምሕረት
7.የዓለምዘውድ በላይ
8.አስቻለው አበባው
9.ካሳሁን በላዬ
10.ሁነኛው ወርቄ
11.ታደሰ…..ሲሆኑ አቶ አበባው ከበደ ከዚህ በፊት ሞዴል አርሶ አደር ተብሎ መሸለሙን ያለው መረጃ ያረጋግጣል።
ትናንትና ደግሞ ወለጋ በርካታ አማሮች ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ሰዎቹ እራሳቸውን ለማዳን ሸሽተው ጫካ ገብተው የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ እንዴት እንደሆኑም የታወቀ ነገር የለም!
በዐቢይንና በለማን ትወና እን ልፈፋ ተጃጅለህ እነሱን እንደ የለውጥ ሐዋርያት እና ለፍትሕ ለዕኩልነት የቆሙ ቆራጥ መሪዎች አድርገህ የምታስበው ቂል መንጋ ሆይ!፦
* ለመሆኑ የኦሕዴድ ሊቀመንበር ዶ/ር (ሊ.ማ.) ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ የለውጥ ሐዋርያ ናቸው እየተባሉ አሥተዳደራቸው ግን አማራን ማፈናቀል ማሳደዱን መቀጠሉ ለስማቸው መልካም አለመሆኑ የማያስጨንቃቸው ለምን ይመስላቹሀል???
* ዐቢይ እና ለማ አሥተዳደራቸው እንዲህ ዓይነቱን ግፍ መፈጸሙን ቀጥሎ እያለስ ምን ዓይነት ዓይነአውጣና የወጣላቸው እፍረተቢሶች ቢሆኑ ነው እንደ ለውጥ ሐዋርያት እንዲታዩ የሚፈልጉት???
* ዐቢይንና ለማን እንደለውጥ ሐዋርያት፣ ለፍትሕና ለዕኩልነት የቆሙ አድርገህ የምትቆጥሩ ቂል መንጋዎች ሆይ! በዐቢይ እና በለማ አሥተዳደር የአማራ ገበሬዎች ከኦሮሞ ገበሬዎች ጋር ዕኩል የመታየት መብት ተነፍጓቸውና እንደመጤ እንደ የሌላ ሀገር ዜጋ ታይተው በአድልኦ ለአንድ አማራ አባወራ “ሁለት ሄክታር ብቻ!” እያለ እንዲሁም ከነአካቴውም ለቀው እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ እያደረገ እያሳደደ በዓይናቹህ እያያቹህ በጆሯቹህ እየሰማቹህ ዐቢይንና ለማን እንደ የለውጥ ሐዋርያት፣ እንደ ለፍትሕና ለዕኩልነት የቆሙ ቅራጥ መሪዎች አድርጋቹህ የምትቆጥሯቸው ምን ያህል ማገናዘብ፣ ማሰብ ማሰላሰል የተሳናቹህ ዘገምተኛ ብትሆኑ ነው???
ወገን ሆይ! ተው ጨክን??? ተው ቁረጥ??? ተው ተነሥ??? ይሄ ነገር በየተራ ተለቅመህ ለማለቅ ካልሆነ በስተቀር በማስታመም የሚሆን ነገር አይደለም!!! ሞት ካልቀረ ጠላትን ይዞ መሞትም እኮ አንድ ቁምነገር ነው!!!
ድል ለአሳረኛው ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
