በተለይ በአሁኑ ሰዓት የአማራ ጉዳይ ይገደናል ያገባኛል ብለው በአማራ ስም የተደራጁ በርካታ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ድርጅቶች አሉ፡፡
ለመሆኑ እነኝህ ድርጅቶች ሥራቸውን፣ ኃላፊነታቸውንና ግዴታቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ ወይ???
እኔ አንድ እንኳ ለመኖሩ በእጅጉ እጠራጠራለሁ!!! ምን ለማለት ፈልጌ ነው በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የማፈናቀል የመግደልና ሌሎች ግፍ የተሞላባቸው በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ፈጽሞ የማይጠበቁ አረመኔያዊ የግፍ እርምጃዎችን ጥቃቱ በተፈጸመ ቁጥር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ክፍል፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለምዕራባውያን መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሳይሰለቹ ሳይታክቱ ሥራየ ብለው ክስ እና አቤቱታ ያቀርባሉ ወይ??? አይመስለኝም! ይሄ መሆኑም በእጅጉ ያሳዝናል!!! ይሄንን ቢያደርጉና ለዚህ ቢተጉ ኖሮ እነኝህ ዓለም አቀፍ አካላት ማፈናቀሉን መግደሉንና ሌላውንም አረመኔያዊ ግፍ መግለጫ እያወጡ ሲያወግዙ እንሰማ ነበረ፡፡
በተለይ ደግሞ ከአማራ አብራክ የወጡ ምሁራንን እንዴት አድርጌ ብረግማቸው የልቤ እንደሚደርስ አላውቅም! የኦሮሞን፣ የትግሬንና የሌሎችን ምሁራን ተመልከቱ ለየወገናቸው ምን ያህል ተቆርቋሪ፣ ተሟጋች፣ ፈጥኖ ደራሽና አሳቢ እንደሆኑ ታያላቹህ፡፡ ወገናችን ለሚሉት ጥቃቅን ነገር እያነሡ፣ አግባብ ያልሆነ ጥቅም እየፈለጉ ምን ያህል ለየወገናቸው እንደቆሙና እንደሚሟገቱ እየታዘባቹህ ነው፡፡
የአማራ ምሁራንን ደግሞ ተመልከቱ እንኳን እንደሌሎቹ ለጥቃቅን ነገርና ለማይገባ ጥቅም ሊሟገቱ ይቅርና በዚህች ሀገር በማንም ብሔረሰብ ላይ ደርሶ የማያውቅ የዘር ማጥፋት ጥቃት ለ27 ዓመታት ያለማባራት ሲፈጸም እኔ እንዴት እንደማይሰማቸውና እንደማይገዳቸው አላውቅም ጭራሽ መርፌ እንኳ የጠፋባቸው አይመስሉም፡፡ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሲንጎራደዱ ትመለከቷቸዋላቹህ፡፡ ጭራሽም አራጆቻችንን ሲያገለግሉ ታገኟቸዋላቹህ፡፡ እነኝህ ታዲያ እርግማን ይበዛባቸዋል እንዴ ታዲያ???
ይሄኔ ይሄ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት ጥቃት በመላ ሀገሪቱ ታውጆ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው በኦሮሞ ወይም በትግሬ ወይም በሌላ ብሔረሰብ ላይ ቢሆን ምሁራኖቻቸው ምን ያህል ዓለምን ያለ እረፍት ሊቀውጧት እንደሚችሉ ይታዩዋቹሀል???
አየ ወገኔ ከቶ ምን ላድርግህ??? ወዴት አባቴ ሸሽጌ ላስጥልህ??? መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይድረስልሀ ሌላ ምን ላደርግህ እችላለሁ???
ድል ለአሳረኛው አማራ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
