
ጋሽ በቀለን ከ2007 ጀምሮ አውቀዋለው በአንድ ከተማ በመኖራችን ብዙ የመገናኘት እድል ነበረን ከዛም አልፎ አዩ ሆቴል ተዝናንተን ዋርካ ኪዳነምህረት ስጋ ቤት ብዙ ግዜ ምሳ በልተን ስለ ሀገራችን ፓለቲካ ብዙ አውርደን ጥለናል ። በድጋሚ ሲታሰርም በተደጋጋሚ ቃሊቲ ወርጄ ጠይቄዋለው ። ሲፈታም ከአዲስ አበባ ይዘነው ልንመጣ ከአዳማ መንገድ ስንጀምር ሞጆ ላይ ተገናኝተን አጅበነው እልል እያልን እቤቱ አስገብቼዋለው ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን የታገለው ለህዝብ ነው ከሚል እሳቤ ብቻ ነው ።
ጋሽ በቀለ ጋር ይበልጥ የተግባባነው ኦሮምኛ ስለማወራ ነው አንድ ቀን ስለ ሚኒሊክ ሲወራ አማራ ኦሮሞን ይቅርታ መጠየቅ አለበት የሚል ወሬ ተነሳ ከዛ አሁን በስደት ካናዳ ያለ ፍቃድ ግርማ እሚባል ልጅ በቄ ዘውዳችን እኮ አማራ ነው አለው ጋሽ በቄም በቃ አንተን እኛ ሞጋሳ እንወስድሀለን አልያም የሸዋ ኦሮሞ እንድርሀለን ብሎ ነገሩ በሳቅ አለፈ ።
ከዛ ግዜ ጀምሮ በቄ የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኛ መሆኑን ተረድቻለው ፣ ቀጠለና ሆን ብሎ ባንዲራውን ተጠይፎ ከእስክንድር ጋር አሜሪካ ላለማሄድ ውሀ እማይቃጥር ምክንያት ሲያነሳ ፈገግ ብያለው ዛሬ ደግሞ የተናገረውን ደጋግሜ ስሰማው ኦነግ ቁጥር 2 ሆነው ብቅ ያሉ መሰለኝ ጋሽ በቄ ምንም አክራሪ ብሔርተኛ ቢሆንም ይህን ንግግር ይናገራም ብዬ አስቤው አላውቅም የአቶ አንዳርጋቸው መፈታት እንዴት ያንጨረጭራል ፣ የእኛ የሆነ ሰው ቢመጣም ምንም ጠብ አላለልንም ማለት እኛ ብቻ እንዝረፍ ነው ለኔ (ህውሓትን የጠላነው ለምን ሆነና) ትግላችን ተጠልፎ ሌላ ሰው ነው በድሉ እየተጠቀመ ያለው ብሎ ለመናገር የሚያደርስ ነገር ምን ተገኝቶ ነው ማንስ ምን ተጠቀመ ደግሞስ የቱ ድል ነው ? ጋሽ በቄ የታገለው ለንዋይ አልያም ለስልጣን ነው ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል ፣ በመጨረሻም እኛ ማናማስለው ከሆነ ሀገር ይበተናል ብሎ አስፈራርቷል እሱ ባለው እሚሆን ከሆነ ይሞክሩት ሌላ ምን ይባላል ህውሓት እንካን መሳሪያ ታጥቆ ሀገር ለማፍረስ ቢጥርም አልቻለም ከተሳካ መንገድን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብለናል ፣ ግን ይህን ንግግር ጋሽ በቄ ያደረገው አክራሪ ብሔርተኝነትን ለመቀስቀስ አስቦ እንደሆነ እረዳለው ። ዛሬ ትላንት አይደለም ሀገር እናፈርሳለን ስላሉ እሚለማመጥ ልቡ እሚቀልጥ ሰው ብዙ ይኖራል ብዬ አላስብም ስለዚህ ያልተበላበት የፓለቲካ ካርድ ቢመዙ የተሻለ ይሆናል ።
ለጋሽ በቄ እንረስ ካላችሁ
ተባብረን እንረስ
አይሆንም ካላችሁ
ተውት ዳዋ ይልበስ ።



