ህወሃት የሚፈልገው “የጎሣ ፌደራሊዝም” ስርዐቱንና “የአቢዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮቱን የሚሸከምለት የጋማ ከብት እንጂ ይህን ርዕዮቱን የሚቀርፅለት ኦነጋዊ መሃንዲስ አይደለም::

በቀለ ገርባ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አልተሣሣቱም:: በማር የተለወሠውን ድብቁን አጀንዳ ይፋ ነው ያደረጉት:: ዋሺንግተንም “የኢትዮጵያ ባንዲራ አያጅበኝም” ነው ያሉት:: ፀረ-ኢትዮጵያነታቸውን ነው ያሣወቁት:: የማይገባቸውን ክብር ሰተንና እስር ቤት ውስጥ ስላሥካኩ የዴሞክራሲ፣ የነፃነትና የሕግ የበላይነት እንቁላል እንዲጥሉ ፈለግን:: የተሣሣትነው እኛ ነን::

ከመስከረም 8/2027 ጀምሮ በኦነግና ጭንብሉን በለበሱ ኩባንያዎቹ ማለትም ኦህዴድ: ኦዴግና ኦፌኮ መካከል ያለውን የግብ ዓላማ አንድነት (strategic alliance) አቅርበናል:: ችግሩ መፃፍ እንጂ ማንበብና ማገናዘብ የማይፈልጉ የፌስ ቡክ አርበኞች እጀ ሠባራ አደረጉን እንጂ::

ይህን እናስተውል!!

1. እየተዋጋንና እየወጋን ያለውየወያኔን። አፖርታይዳዊና እንሠሣዊ “የጎሣ ፌደራሊዝም” ስርዐትና “አቢዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮቱን ወይስ ግለሰቦችን? ግለሰቦችን ከሆነ አሁንም ተሣስተናል:: ጠላታችን ስርዐቱ ነው:: እነ በቀለ ገርባም የዚህ ስርዐት ህይወት-አድን (life savors) ናቸው::

2. ይህ “የጎሣ ፌደራሊዝም” ወያኔ ከእንክርዳድ የጠመቀው መርዝ ሲሆን “አተገባበሩ እንጂ ስርዐቱ ሸጋ ነው” በማለት ኦነግና ጭንብል ድርጅቶቹ (ኦህዴድ፣ ኦዴግና ኦፌኮ) አረጋግጠዋል:: “የመግዛት ተራው የኛ ነው” ሲሉም አቅራርተዋል:: ፕ/ር መረራም “ኦሮሞ በቁመቱ ልክ ሥልጣን ያስፈልገዋል” በማለት አጠናክረውታል:: ህዝብን ከፋፍሎ ለሚገዛው ወያኔ ሰራሽ ስርዐት እውቅና ሰጥተዋል:: ስለዚህ በወያኔና ኦነጋውያን (ኦህዴድ፣ ኦዴግና ኦፌኮ) ያለውን ርዕዮተዓለማዊ አንድነት ተነግሮናል:: ስለዚህም በወያኔና ኦነጋውያን አንድም ሁለትም ናቸው:: ልንፋለማቸውም ይገባል::

3. ኦነጋውያን (ኦህዴድ፣ ኦዴግና ኦፌኮ) እንደ እርጉዝ ኢትዮጵያን መመልከት ያቅለሸልሻቸዋል:: እንደ እርጉዝም ያማራቸው ነፃነትና ዴሞክራሲ ሣይሆን “በቁመታቸው ልክ” የፖለቲካ ሥልጣን ነው:: ያማራቸው ወያኔን መሆን ነው::

4. በቀለ ገርባም ይሁን ሌሎቹ ኦነጋውያን መዳረሻቸው ኦሮሚያን “መገንጠል” ነው:: ለዚህም ነው ወያኔን ጥለን “እኛ የምንመራው “የጎሣ ፌደራሊዝም” ካልተቀበላችሁ ኢትዮጵያ ትፈርሣለች” እያሉ ደንብረው ሊያደናብሩን የሚሞክሩት::

5. ያሠፈሰፉትም ከኛ ኢትዮጵያን፤ ህዝባዊ ውክልና ያልሰጣቸውን ኦሮሞን ኢትዮጵያዊነቱን በፈጠራ ተረታቸው ከውስጡ ለመንጠቅ ነው::

የፈሪ ዱላቸው መዘዝ አለው:: ይህንን ይወቁ:-

ሀ). ቅዠታቸው ቢሳካ እንኩዋን ስልጣንን ብቻ ሣይሆን ሃገርንም በቁመታችን ልክ እንደምንካፈል

ለ). በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አግባብ በእኩልነትና በነፃነት አብረን መኖር ካልቻልን ህዝብን ለእልቂት የሚጋብዝ የእርስ በርስ ግጭትና ጦርነትንና መዘዙን አሁኑኑ ማጤንና ማንም አሸናፊ እንደማይሆን መገንዘብ ጥሩ ነው::

ሐ). ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ንብረት መሆኑን ማስተዋል

መ). የመግዛት ተራ የሕግ የበላይነት እንጂ የአንድ ወይም ሌላ ጎሣ አለመሆኑን

ሠ). ኢትዮጵያ ከእንግዲህ የምትተዳደረው አብላጫ ቁጥር ባለው ጎሣ ሣይሆን የዴሞክራሲያዊ አብላጫ ድምፅን በምርጫ በሚያገኝ ስርዐት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል::

ረ). “የጎሣ ፌደራሊዝም” እንሠሣዊና ህዝብን የሚያናክስ እንደ ላቲን ፊደል መጋዘን መግባት ያለበት ኢ-ዲሞክራሲያዊም በመሆኑ በሊብራል ዴሞክራሲ ፍልስፍና ለመመራትና ለመተካት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል::

የኦነግና ኩባንያው ጥንካሬ ከህወሃት ጋር ባለው የአላማና የርዕዮት አንድነት የሚደረግበት ግፊትና ጫና ማነስ እንጂ ህዝባዊ መሠረቱም አይደለም:: +50 ዓመታት ያልተፈታን ቅዠት እንደ ኳስ ከማንከባለል ፍትሃዊና ወቅታዊ መስመርን ማራመዱ ይበጃል:: ህወሃት ሠራሹ ስዕል ላይ የሚገነባ የካርታ እሣቤ እድሜው የህወሃትና የስርዐቱ “የጎሣ ፌደራሊዝም” እንደሆነ ሣይረፍድ ማወራረድ ይመከራል::
‘ይሆናልን ትተን አይሆንምን ማሠቡ መልካም ነው።

ሞት “ለጎሣ ፌደራሊዝም”!