‹‹በሃገሪቱ የተፈጠሩ የእኩል ተጠቃሚነት እና የመልካም አስተደደር እጥረት ፅንፍ ያለው የከረረ ብሄረተኝነት ስስት ውስጥ አስገብቷል ››
በባህርዳር ከተማ ከ400 በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት ምክንያታዊ የወጣቶች የክርክር መድረክ ላይ ወጣቶች ያነሱት ሃሳብ ነው ።
ባሕርዳር፡ግንቦት 26/2010 ዓ/ም (አብመድ)ወጣቶቹ ባነሱት ሃሳብ አማራው በሃገሪቱ የፓለቲካ ተሳትፎ ተፅዕኖ ፈጣሪነቱ አናሳ ነው ።በትምህርቱ መስክ የሚገኙ ምሁራን በዩኒቨርሲቲዎቻቸው የሚያሳዩት ባህሪ ጥላቻን በማባባስ የብሶት መገለጫ እንዲሆኑ የሚገፋፉ ናቸው ።
አቅም ያለው አመራር ያለመኖር የስንፍና ባህል በማስፈን ወጣቱን ከሱስ ማውጣት አልቻለም ።የአማራ ወጣት በገዛ መሬቱ መኖሪያ መሬት ይሰጥሀል እየተባለ በጉጉት ውስጥ እየማቀቀ ነው ።
በወጣቱና በድርጅቱ መካከል ሰፊ ርቀት ተፈጥሯል ። የወጣቱን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ካልተቻለ ግለኝነትንና ለሌሎች ክብር የሌለው ዜጋ ይፈጠራል ።
በሃገሪቱ እየታየ ያለ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አካሄድ በመጠራጠር ላይ የተመሰረተ፣ የከረረ ብሔርተኝነት ማሳያ በመሆኑ የጋራ መግባባት ሊፈጠር ይገባል ።
የከረረ ብሔርተኝነትን ወደህዝብ የሚያስገቡት ከፍተኛ አመራሮች ናቸው የሚሉ ሃሳቦችም ተነስተዋል ።

መድረኩ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
Amhara Mass Media Agency
በግርማ ተጫነ
