‹‹ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አፈፃፀም አራምባና ቆቦ!!! በመንግሥት ውስጥ መንግሥት!!! (A State within a State) ››

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማቆቆም ያስፈልጋል!!!

{I} የኤክስፖርትና ኢንፖርት የንግድ ሚዛን አፈፃፀም

{1} የአንደኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የውጪ ንግድን ከ10.5 በመቶ ወደ 31.2 በመቶ የአመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት ጋር ማድረስ የሚል ነበር፤ በ2006 በጀት ዓመት 3.2 ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር የኤክስፖርት ገቢ ተገኝቶል፡፡} {በዕቅዱ የመነሻ የመነሻ አመት(በ2002) 2 ቢሊዩን ዶላር የነበረው የሸቀጣ ሸቀጥ የኤክስፖርት ገቢ በ2007 መጨረሻ ከ5-8 ቢሊዩን ዶላር ለማድረግ ግብ ተቀምጦ ሲሰራ ቆይቶል፡፡} {የሸቀጦች የውጪ ንግድ ሚዛን ክፍተት እየጠበበ እንዲሄድ ማድረግ ለዘላቂ ዕድገቱ ወሳኝ በመሆኑ የዕቃዎች ኤክስፖርትን እና ቱሪዝምን እና የአየር ትራንስፖርት የመሳሰሉትን አገልግሎቶች በከፍተኛ መጠን ማስፋፋት ይገባል፡፡ የኤክስፖርት መስፋፋት፡- አስተማማኝ የውጪ ምንዛሪ ግኝት በማረጋገጥ በአገር ውስጥ የማይመረቱ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችና ዕቃዎች ከውጪ በማስመጣት ፈጣን ዕድገቱን ለማስቀጠል፣ ከውጭ ብድርና እርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ፣ የኢኮኖሚውን ተወዳዳሪነት በቀጣይነት ለማረጋገጥና፣ እና በአገር ውስጥ ገበያ ብቻ ያልታጠረ ስፊ ገበያ ለማግኘት ያስችላል፡፡} { አምስቱ አመታት ውስጥ የሃገሪቱ አመታዊ የኤክስፖርት ገቢያችን በአማካይ 29 በመቶ እንዲያድግ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡}{የማኑፋክቸሪንግ ዉጤቶች በኤክስፖርት ንግዱ ውስጥ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ በተለይም ቆዳ፣ጫማና ሌሎች የቆዳ ውጤቶች፣እና ስካüር ትኩረት ተሰጥቶቸው እንዲስፋፉና ዋናዋና የኤክስፖርት ምርቶች እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡}{ከአየር ትራንስፖርትና አገራችን ከፍተኛ እምቅ አቅም እንዳላት ከሚነገርላት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ለማስገኘት ጥረት ይደረጋል፡፡}{የኤክስፖርትን የማስፋፋትና ስብጥሩን ለመቀየር ስትራቴጂ ለማሳካት፣ የውጪ ምንዛሪ ተመኑን በቅርብ መከታተል፣ የኤክስፖርት ማምረት ለማበረታታት የሎጂስቲክስና ትራንስፖርት አገልግሎት፣የኤሌትሪክ አገልግሎት፣የመሬት አቅርቦት፣እና የንግድና የጉምሩክ ፋሲሊቴሽን ይረጋገጣል፡፡}{በኤክስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በውጪ ምንዛሪ አቅርቦትና በብድር አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዚሁ ቅድሚያ  ትኩረት አግኝተው በፍጥነት እንዲስተናገዱ ይደረጋል፡፡} {ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በዕቅዱ የመነሻ የመነሻ አመት(በ2006) 3.2 ቢሊዩን ዶላር ለማድረግ ግብ ተቀምጦል፡፡}

{2} የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (2008-2012)፣ {በአጠቃላይ የውጪ ንግድ ከጠቅላላው የሃገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ 11.8 ድርሻ እንዲኖረው ውጥን ተይዞል፡፡}{በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከግብርና ምርቶች የውጪ ንግድ 7.7 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡} {በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከኢንዱስትሪ ምርቶች የውጪ ንግድ 4.6 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡} {በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት (የውጪ ንግድ) 636 ሚሊዩን  ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡} {በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከማእድን ዘርፍ ኤክስፖርት (የውጪ ንግድ) 2.1ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡ በአንደኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከዘርፉ 508 ሚሊዩን  ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡} {በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የውጪ ንግድ 1 ቢሊዩን  ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡} {በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የውጪ ንግድ 800 ሚሊዩን  ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል፡፡} { የውጭ ንግድ ገቢ እቅድ በ2007 ዓ/ም (3,019.3 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2008 ዓ/ም (4,884.6 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2009 ዓ/ም (6,780.3 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2010 ዓ/ም (8,747.8 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2011 ዓ/ም (11,035.6 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2012 ዓ/ም (13,909.1 ቢሊዩን ዶላር) ሆኖም ከ2008 እስከ 2009 ዓ/ም የእቅዱ አፈፃፀም 3 ቢሊዩን ዶላር በታች ነው፡፡}

የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ የገቢና ውጪ ንግድ እቅድና አፈፃፀም፡- በ2010 መንፈቅ አመት እቅድና አፈፃፀም የኢትዮጵያ በውጭ ንግድ ገቢ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ አፈፃፀሙ 1.35 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ተገልፆል እንዲሁም የዘጠኝ ወር በውጭ ንግድ ገቢ አፈፃፀም 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መሆኑ ተገልፃል፡፡ የ2009 ዓ/ም በጀት ዓመት የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ የገቢ ንግድ ወጪ እየጨመረ መሄድና የወጪ ንግድ ገቢ እየቀነሰ መሄድ በእቅድና አፈፃፀም ሪፖርት መሠረት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል፡፡ ከ2009 ዓ/ም ጠቅላላ የውጪ ንግድ ገቢ ከተያዘው ዕቅድ፣ አፈፃፀም 42.8 በመቶ  ማሽቆልቆሉን መንግስት ካወጣው እቅድና አፈፃፀመ መረዳት ይቻላል፡፡

  • በ2007ዓ/ም ከውጪ ንግድ ዘርፍ 2,995,321 ቢሊዩን ዶላር የነበረ ሲሆን ዕቅዱ 3019.3 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙ የዕቅዱን 99.2 በመቶ መሆኑን ያሳያል፡፡
  • በ2008ዓ/ም ከውጪ ንግድ ዘርፍ 2,856,000 ቢሊዩን ዶላር፣በአጠቃላይ ዕቅዱ 4.884.6 ቢሊዩን ዶላር፣ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው 2.8 ቢሊዩን ዶላር ብቻ ነው፡፡ አፈፃፀሙ የዕቅዱን 58.5 በመቶ መሆኑን ያሳያል፡፡
  • በ2009ዓ/ም ከውጭ ንግድ ዘርፍ 2.9 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ይታወቃል፡፡በ2016/17እኤአ ጠቅለላ የውጭ ንግድ ገቢ ዕቅድ 6780.3 የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙ ከግማሽ በታች 2.9 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ይስተዋላል፡፡ አፈፃፀሙ የዕቅዱን 42.8 በመቶ መሆኑን ያሳያል፡፡ በ2009ዓ/ም የገቢ ንግድ ውጪ 15.8 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በበጀት ዓመቱ 12.9 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ሚዛን ጉድለት ተመዝግቦ ነበር፡፡
  • በ2010ዓ/ም ከውጭ ንግድ ዘርፍ የዘጠኝ ወር 2.1 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ይታወቃል፡፡በ2017/18 እኤአ ጠቅለላ የውጭ ንግድ ገቢ ዕቅድ 8747.8 የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙ አንድ አራተኛ በታች መሆኑ ይስተዋላል፡፡ የ2010ዓ/ም ሲጠናቀቅ አፈፃፀሙ የዕቅዱን በመቶ እናሰላለን፡፡
  • በ2011ዓ/ም የውጪ ንግድ ገቢ ዕቅድ 11,6 ብር፣ በ2012ዓ/ም የውጪ ንግድ ገቢ ዕቅድ  13,909.1 ብር ምናባዊ ዕቅድ በማውጣት የውጪ ንግድ ገቢ ዕቅድ ከአፈፃፀሙ ጋር ሲነፃፀር በጥናት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
  • በሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የሚካሄዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ 2.2998 ትሪሊን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 1.3133 ትሪሊን ብር የሚሆነው ለካፒታል ወጪዎች የሚያስፈልግ ሲሆን ከአደጉ አገራቶች የሚገኘው የፋይናንስ ድጋፍ (ኦፊሻል ዴቨሎፕመንት አሲስታንስ) እየቀነሰ በመምጣቱ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያ የገቢ ምርት ውጪ ለነዳጅ ያወጣችው በ2007ዓ/ም 2 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በ2008 ዓ/ም 1.33 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በ2009ዓ/ም 1.8 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡

የዓለም ዓቀፍ ህብረተሰብና በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትጵያውያን ዜጎች መንግስት  በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ እንቢተኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ተሸጋግሮ፣ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ተሸመድምዶል፡፡ በህወሓት አንባገነናዊ አገዛዝ የተነሳ፣ የልማት አጋሮች እርዳታና ድጋፍ መቀነስና መቆረጥ፣ የባህር ማዶ ዲያስፖራ ወገኖቻቸው ላይ በሚደርስ ግድያና እስራት የተነሳ የውጭ የሃዋላ የገንዘብ መላክ አድማ ወያኔን ኢኮኖሚ ድባቅ መቶታል፡፡ የወያኔ ባለሥልታናት የሚያደርጉት ካፒታል ፍላይት(ወደ ውጭ ሀገራት የካፒታል/ የገንዘብ ሽሽት) በሃገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት የተነሳ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ የካፒታልና የውጭ ምንዛሪ ኩብለላ ከፍተኛ ሆኖል፡፡ የውጭ ሃገር ኢንቨስትመንት መቀነስ፣የሃገር ጎብኝዎች (የቱሪስት)ቁጥር መቀነስ፣ እንዲም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣይነት የውጭ ብድር አቅርቦት ማጣት፣የውጭ ብድር ክፍያ ዶላር እጦት፣ለሜጋ ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ካፒታል ጉድስ ግዥ ለምሳሌ ማሽነሪዎች፣ ጀነሬተሮች፣ ተርባይኖች፣ወዘተ ግዥ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪ ችግር የተነሳ የሜጋ ፕሮጀክቶቹ ሥራ ተስተጎጉሎል፡፡ በአጠቃላይ አማካይ አመታዊ የሃገር ውስጥ ምርት መቀነስ (ጂዲፒ)፣ የሃገር ውስጥ የግብር ገቢ መቀነስ፣ኢንፍሌሽን /የዋጋ መናር/ በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ፣ተከስቶል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የመልካም አስተዳደር ችግርና በሙስና መዘፈቅ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በጥቂት ዘውጌ ባለኃብቶች ቁጥጥር ስር እንዲሆን ዳርጎታል፡፡ከሃገሪቱ አንጡራ ኃብት በህገወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድን ምርት፣በተለያዩ ክልሎች በድንበር በኩል ወደ፣ሱዳን፣ሱማሊያ፣ ኬንያና፣ጅቡቲ በኩል ከአገር እንደሚወጡና በከፍተኛ ዋጋ በውጪ ምንዛሪ ይሸጣሉ፡፡ የውጪ ምንዛሪ የአንዱ ዶላር በ33 ብር መመንዘር የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ቀውስ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡ የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የውጭ ገቢ ንግድ ገቢ መቀነስ ብሎም ድንበር ዘለል የህገወጥ ንግድ መስፋፋት፣ ሃገሪቱ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶች የካቲታል ጉድስ እቃ ግዥ አስፈላጊነት መጨመር አንዱ ሳያልቅ ሌላ መገንባት የመማሰፈፀም አቅም ሳይኖር ለሙስና መዳረግ፣ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የ2010 ዓ/ም የመንፈቅ ዓመት የኢትዮጵያ በውጭ ንግድ ገቢ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ አፈፃፀሙ 1.35 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ተገልፆል፡፡አፈፃፀሙ 61 መቶ የእቅድን እንደሆነ ያሳያል፡፡ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም የተጠቃለለ ሰነድ ሲሆን ዝርዝሩን ከጋዜጣው አንብበው በመረዳት እቅዱ ከአፈፃፀሙ አንፃር አራንባና ቆቦ በመሆኑ እንደ ከሸፈ መረዳት አያዳግትም፡፡

{II} የፊስካል ፖሊሲና የመንግስት ገቢና ወጪ ፋይናንስ አፈፃፀም፤ (የአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢ)

{1} አንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ ጠቅላላ የታክስ ገቢ በ2002 ከነበረበት 43 ቢሊዩን ብር በ2006 መጨረሻ ወደ 133 ቢሊዩን ብር ከፍ ያለ ሲሆን የታክስ ገቢው ባለፍት አራት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ በ33 በመቶ አድጎል፡፡ የተሰበሰበው ገቢ በራሳችን አቅም ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማካሄድ አስችሎናል፡፡} {በ2007 በጀት ዓመት የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት ያለውን ድርሻ ወደ 15 በመቶ ለማድረስ የታቀደ ቢሆንም በ2006 የበጀት ዓመት የተሰበሰበው የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 12.7 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት አማካይ አፈፃፀም 15 በመቶ ነው፡፡} {ከመንግስት ጠቅላላ የወጪ በጀት ውስጥ ወደ 60 በመቶው የሚጠጋው ለካፒታል ኢንቨስትመንት ሲደለደል የቆየ ሲሆን፣ ቀሪው 40 በመቶ ገደማ ብቻ የመደበኛ ወጪ ለመሸፈን ሲመደብ ቆይቶል፡፡ } {በዕቅድ ዘመኑ የተሰበሰበው የመንግስት ገቢ በመደልደል የበጀት ጉድለቱ ከ3 በመቶ እንዳይበልጥ በማድረግ ጥብቅ የፊስካል ፖሊሲ ተግባራዊ ተደርጎል፡፡}

በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (2003-2007 እኢአ) ፣ በአምስት አመታት ውስጥ የአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢ፣441.1 ቢሊዩን ብር መሆኑን ተገልፆል፡፡ በእቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 10.12 በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ ተችሎል፡፡ በሃገሪቱ በ2008 እስከ 2009 ዓ/ም በተቀሰቀሳ ሕዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ምክንያት የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት ከህዝብ፣ ከግብርና እና ታክስ የሚሰበስበው ገቢ በጣም ቀንሶል፡፡ በ2008ዓ/ም 133 ቢሊዩን ብር ከህዝብ በግብር ሰበሰቡ፤ ወያኔ በ2009ዓ/ም የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 173.19 ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 113.56 ቢሊዩን ብር ብቻ በመሰብሰቡ የጎደለውን 59.63 ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ በመገደዱ ከህብረተሰቡ ተጨማሪ ግብር ለመሰብሰብ አስቸኮይ የስራ ዘመቻ የከፈተው ነበር፡፡ አሁን ህዝብ ላይ የተጫነው ግብር ዋናው ምክንያት ለ‹‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ›› በኮማንድ ፖስቱ እየወጣ ያለው የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር፣ ልዩ ኃይል፣ ወዘተ የደሞዝ፣ የቀን አበል ያልተጠበቀና በበጀት ያልተያዘ ወጪ ሥርአቱን አናግቶት ነበር፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ መንግስት የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከጅምሩ አክስሞ አጨንግፎት ነበር፡፡

{2} ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ የታክስ ገቢው ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 17 በመቶ ለማሳደግ ከፍተኛ የታክስ አስተዳደር ጥረት ለማረጋገጥ ታቅዶል፡፡ የመንግስት የወጪ ዕድገትን የካፒታል ክምችትን በሚያሳድጉ የካፒታል ኢንቨስትመንቶች እንዲውሉ ማድረገረ፣የመንግስት ገቢና ወጪን በማመጣጠንና በጀት ጉድለቱ የዋጋ ግሽበትን በማያስከትል ብድር እንዲሸፍን ማድረግ፣ የተረጋጋና ዝቅተኛ የዋጋ እድገት ማረጋገጥ፣ የውጭ የምንዛሪ ተመን ፖሊሲ፣ የተረጋጋ የብር ምንዛሪ ተመንና የውጪ ንግድን የሚያበረታታ ማድረግ፣ የውጭ የምንዛሪ ክምችትን ማጠናከር፣ የአገሪቱ የፋይናንስና የባንክ ኢንዱስትሪው ልማቱ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የማቅረብ ብቃት፣ በቀጣዩ የተያዘውን ሰፊ የመሠረተ ለማት ዝርጋታ፣ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪና ዘመናዊ ግብርና ልማትና የኤክስፖርት ልማት ዕቅድ በወሳኝነት መደገፍ ብቃት ማጠናከር፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (2008-2012እኢአ) ፣ በአምስት አመታት ውስጥ የአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢ፣አንድ ትሪሊዩን ሦስት ቢሊዩን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ህወኃት /ኢህአዴግ በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ዶሴው ላይ ገልፆል፡፡ በእቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 17 በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶል፡፡

‹‹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ የብር ዶላርን የመግዛት ዋጋን በ15 በመቶ ዝቅ ያደረገ ሲሆን፣ አንድ ዶላር ይመነዘር የነበረው 23.41 ብር ወደ 26.93 ብር ከፍ ብሎል፡፡ ይህም ለአገር ውስጥ ምርቶች የገበያ እድል እንደሚከፍትና የውጭ ባለሃብቶችን ወደ አገር ውስጥ በመሳብ ለማልማት እንደሚያበረታታ ይናገራሉ፡፡››2

አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ የኢትዮጵ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ‹‹ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የአገሪቱ ምርቶች በዓለም ዓቀፍ ገበያ ዋጋቸው እየቀነሰ መምጣቱ ለውጪ ንግድ መቀዝቀዝ ምክንያት በመሆኑ በወጪና ገቢ ንግድ መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብና የውጪ ንግድን ለማሳደግ የምንዛሪ ለውጥ መደረጉን አስረድተዋል፡፡››

አቶ ፍሬህወት ሀንዳም፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር በፊስካል ፖሊሲ ዳይሬክቶሬት የፊስካል ፖሊሲ ጥናት ቡድን መሪ እንደሚሉት ‹‹በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች መታየት ያለባቸው አጠቃላይ ፋይዳቸው ሲሆን፣ ብር ዶላርን የመግዛት ዋጋው በ15 በመቶ እንዲወርድ መደረጉ ባለፉት አምስት አመታት የተዳከመውን የውጪ ንግድ የሚያነቃቃበት ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ አገሪቱ እያስፋፋችው በምትገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የውጭ ባለሃብቶች እንዲገቡና የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲበረታታ ያደርጋል፡፡ ይህም ለወጣቱ ሰፊ የሥራ እድል ይፈጥራል፤ ጎብኚዎች ጥቂት ዶላር ይዘው መግባት እንዲችሉ ስለሚያደርግ ቱሪዝሙን ከመደገፍ አኮያም የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡››

ዶክተር ተክኤ አለሙ፣ በአዲስ አበባ ኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ‹‹ የአገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ የሚቀንሰውና የሚጨምረው የብር መንዛሪ ዋጋን በመቀነስ ብቻ አይደለም፡፡ ከዶላር መንዛሪ አንፃር የብር ዋጋ መውረድ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ዋጋ በመጨመር የሰው ፍላጎት እንዲቀንስና በአገር ውስጥ ምርት እንዲጠቀም ቢያደርግም የውጪ ንግዱን ለማሻሻል ግን ብቸኛ አማራጭ አየደለም፡፡ ውጤቱም በአጭር ጊዜ የሚታወቅ አይደለም፡፡ በመሆኑም የውጭ ንግዱን ለማሻሻል ከምንዛሪ ዋጋ መጨመር ባሻገር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በብዛት ማምረትና ጥራታቸውን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ የውጪ ንግዱ እንዲቀዛቀዝ ካደረጉ ምክንቶች ውስጥ ምርቱ በዓል ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን በተሸለ ጥራት መላክ አለመቻሉና እሴት ያልተጨመረበት መሆኑ ነው፡፡ ይህም መዳረሻ አገራትን ለማስፋት እንቅፋት  ፈጥሮል፡፡ ለአብነት ወደ አውሮፓ አገራት ለመላክየተሸለ ጥራት ያለው ምርት ሆኖ መገኘት አለበት፡፡ ይህ መሆን ካልቻለ የምንዛሪ ለውጡ ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ መሰረታዊ አይሆንም፡፡››2 ብለዋል፡፡ እንደ ባለሙያዎቹ ማብራሪያ፤ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ከምንዛሪ ማሳደግ ባሻገር በምርት ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ፣ እሴት የተጨመረበትና በቂ የሆነ ምርት ለዓለም ገበያ ማቅረብ፣ በአገር ውስጥ ምርቶች መጠቀም፣ የምርቶችን ስብጥር ማብዛት እንዲሁም መዳረሻ አገራትን ማስፋት ያስፈልጋል፡፡

ዶክተር አብርሃም ተከስተ፣ ‹‹የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥትን የ2010 ዓ/ም የበጀት ሰነዶችን በመገምገም በየመሥሪያ ቤቱ ከተመደበው በጀት ወጪ እንዲቀነስና የበጀት ሽግሽግ እንዲደረግ ከወሰነ ከ41 ቀናት በኃላ ከ80 መሥሪያ ቤቶች 560 ሚሊዮን ብር እንደተቀነሰ ሰሞኑን ይፋ ተደርጎል፡፡….  የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም፣ ‹‹ 2009 ኣ/ም ከታክስ ገቢ 170 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ቢታቀድም ፣የተሰበሰበው 130 ቢሊዮን ብር መሆኑን ያስታውሱና፤40 ቢሊዮን ብር ሳይሰበሰብ ቀርቶ በጀቱን ማስተዳደር አለመቻሉን ይናገራሉ፡፡ በ2010 ዓ/ም 196 ቢሊዮን ብር ከታክስ ለመሰብሰብ መታቀዱን በማንሳትም፤ሥራው ከፍተኛ ጥረት ይጠይቃል፡፡የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን 54 ቢሊዮን ብር ድረስ ብድር ይወስዳል ነው የሚሉት፡፡››

የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም ተግዳሮቶች፣ በተከሰተው የህዝብ አልገዛም ባይነትና ህዝባዊ ተጋድሎ  እቅዱ ሊጨናገፍ ችሎል፡፡ የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ችግሮች መኃል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፤

{1} ውጭ ምንዛሪ ድርቅ መመታት፣ በበ2003ዓ/ም በጀት አመት 55.5 ሚሊዩን ብር የነበረ ሲሆን፤ በ2004ዓ/ም 39.8 ሚሊዩን ብር፣ በ2005ዓ/ም 45.6 ቢሊዩን ዶላር፣ በ2006ዓ/ም 56.1 ሚሊዩን ብር፣ በ2007ዓ/ም 37.5 ሚሊዩን ብር ፣ 2009ዓ/ም የኣለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ኃብት 3.2 ቢሊዩን ዶላር፣ ሃረሪቱ ለውጭ ንግድ በሁለት ወራት ውስጥ ከምታወጣው ያነሰ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በ2016/17 እኤአ የዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ቀሪ ገንዘብ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ለአንድ ዓመት ለወራቶች ብቻ የሚበቃ የውጪ ግዥ ለመፈፀም (ኢንፖርት ወጪ) ለመሸፈን የሚውል መጠባበቂያ  ገንዘብ እንደሆነ አይኤፍ ኤም ገልፆል፡፡

{2} የገቢ ንግድ ነጋዴችዎ/ኢንፖርተሮች፣ በሃገሪቱ አምስት ሽህ የገቢ ንግድ ላይ ተሰማሩ ካንፓኒዎች ይገኛሉ፣ አብዛኛዎቹ በወያኔ/ኢፈርት፣ በብአዴን /ጥረት የፓርቲ የንግድ ድርጅቶ ኃብት የሆኑ ኮንፓኒዎች ናቸው፡፡ በአብዛኛው የወያኔ ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ጥረት ካንፓኒዎች ወደ ሃገር ውስጥ የፍጆታ እቃዎች በማስገባት ፍቃድ በመውስድ ዘይት፣ ዱቄት፣ ስኮር፣ ማዳበሪያ፣ ወዘተ በማስገባት የውጭ ምንዛሪው ዋነኛ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በግሉ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንፖርት አድራጊ ነጋዴዎች በው ምንዛሪ እጦት የተነሳ ለሁለት አስርት በላይ ከንግዱ ጨዋታው ውጪ ሆነው ቆይተዋል፡፡ የህወሓት የፖለቲካ ድርጅት በውንብድና ንግድ ተሰማርተው የሃገሪቱ የግል ዘርፍ ሥራ በመውሰድ የንግድ ሥርዓቱን ተቆጣጥረው በመያዝ ህዝቡን በመበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ ልማት ባንክና የግል ባንኮች ለእነዚህ 5000 ኢንፖርተሮች የሰጡት የውጭ ምንዛሪ አድሎዊ አሰራር አንድ ቀን ተጋልጦ ይወጣል፡፡ ኢንፖርተሮቹ  ያስገቡትን ሽቀጣ ሸቀጥ ሶስትና አራት መቶ እጥፍ ያለ አንዳች የትርፍ ህዳግ ሲሸጡ ብሄራዊ ባንክ ሌሎች መንግሥታዊ ዘርፍ ድርጅቶች የትርፍ ህዳግ ሳያደርጉ ህብረተሰቡን ሲያዘርፉት አመታት ተቆጥሮል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተቀማጭ ገንዘብ መቀነስ ዋና ምክንያት በህወሓት/ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች የተዘረፈ የህዝብ ኃብት ነው፡፡ ለወያኔ/ኢፈርት አንድ መቶ አንድ የመኪና አስመጭና ሻጭ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ካንፓኒዎች በሃገሪቱ ውስጥና በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ አዳዲስ መኪኖች በውጭ ምንዛሪ እያስመጡ በመሸጥ ገበያውን በቁጥጥር ሥር ካደረጉት አመታት ተቆጥሮል፡፡ የወያኔ መንግሥት ለህዝብ መድሃኒት መግዣ የሚሆን የውጭ ምንዛሪ የለንም እያለ ይቀልዳል፡፡በተመሳሳይ የወያኔ በባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ ውስጥ የወጋጋን ባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ የአንበሳ ባንክ፣ የእናት ባንክ ና ዳሎል ባንክ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ በመቆጣጠር፣ አንጡራ ኃብታችንንና የኢኮኖሚ የደም ስር ይዘው ይዘርፋሉ፡፡ ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም የምንለው፡፡

{3} የእንዱስትሪው ዘርፍ፣ የጥሬ ዕቃዎች ግብዓቶች 75 በመቶ ከውጪ ሃገር ስለሚገቡ የውጪ ምንዛሪ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ የሚያስገኙት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ዝቅተኛ ነው፡፡  ከባህር ማዶ የሚመጣ የጥሬ ዕቃዎች ግብዓቶች ውስጥ  ኬሚካሎች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች ለቀለም ፋብሪካዎች፣ ለጎማ ፋብሪካዎች፣ ለወረቀት ፋብሪካዎች፣ ለእምነበረድና ቴራዞ አምራቶች ፋብሪካዎች፣ ለጠርሙስና ብርጭቆ ፋብሪካዎች፣ ለአልሙኒየም ሰልፌትና ሰልፊክ አሲድ፣ የጅብሰም ቦርድ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የጥሬ ዕቃዎች ግብዓቶች በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ በመሆኑ አዋጭና ዘለቄታዊ ቀጣይነት ያላቸው ያልሆኑ ጥገኛ ፋብሪካዎች መሆናቸው የኢንዱስትሪ ዘርፉና አስር ቢሊዮን ዶላር ወጪ የወጣበት አስር የኢንዱስትሪል ፓርኮች ዝቅተኛ የማምረት አቅም የጠነሳ ያስገኛሉ የተባለው የውጭ ምንዛሪ ውሃ በልቶታል፡፡ በተለይ በኢንዱስትሪል ፓርኮች ውስጥ የተገጠሙ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የቻይና፣ ቱርክ፣ አረብ አገራቶች ማሽኖች ከአገር ውስጥ ባንክ ለግብዓታው የውጭ ምንዛሪ በመጠየቅ የተገነቡ ሲሆን  ምርታቸውም በዓለም ዓቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ ሆነው ዶላርና ፓውንድ ሊያስገኙ አልቻለም፡፡

{4} የኮንትሮባንድ ንግድ፣ በህወሓት/ኢፈርትና ሜቴክ አባላቶች በኮንትሮባንድ የውጭ ምንዛሪ የማሸሽ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሎል ወያኔ አንዳቻውንም ስም ሲገልፅና ለፍርድ ሲያቀርብ አልታየም፡፡ በዚህ ላይ ከሃገሪቱ አንዴ ግማሽ ሚሊዩን ፣ አንዴ 1.8 ሚሊዩን ዶላር በድንበር በኩል ይሾልካል፤ በቦሌ ኤርፖረት በኩል የቻይና ባለሃብት 350 ሽህ እንዲሁም ከአንድ ኢትዩጵያዊ 28.6 ሽህ ዶላር መያዙን አስታውቀዋል፡፡ በአጠቃላይ በ2016 እኤአ 4 ሚሊዩን ዶላር በቦሌ ኤርፖርት በኩል ሊወጣ ሲል ተይዞል ብለዋል፡፡ በግንቦት ወር 2010ዓ/ም 1.2 ሚሊዮን ዶላር በድንበር በኩል መያዙን  ተገልፆል፡፡ በድንበርና በቦሌ በኩል  ሳይይዝ የወጣው የወያኔ ዶላር ብዛቱ የትየ ለሌ ለመሆኑ ጥርጥር የለንም፡፡ ሃገራችን ባለቤት በሌላት የወንበዴዎች መንግሥት  እስከተመራን ድረስ ዘረፋው በየፈርጁ ይቀጥላል፡፡ የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘረፋውን ህጋዊ ላድርግላችሁ እያለ መመሪያ አውጥቶል፡፡

{5} የዋናው ኦዲተር ቢሮ፣ የኢህአዴግ ገዥው አውራ ፓርቲ  በኢኮኖሚ ግምገማ በማድረግ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስና በሙስና ላይ እርምጃ ለመውስድ  ቁርጠኝነት ያስፈልጋል፡፡ የዋናው ኦዲተር ቢሮ ኃላፊ አቶ ገመቹ ዱቢሶ የሚመራ በሃገሪቱ ውስጥ የተከሠተውን የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት የሙስና መረብ አጣርተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርገዋል፡፡ የዋናው ኦዲተር ቢሮ ሠራተኞች፣ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም ዙሪያ በሃገሪቱ የተከናወነውን ዘርፈ ብዙ የሙስና ሌብነት በማጋለጥ ፣የስኳር ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቶችን፣ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሌብነትን፣ ዮኒቨርሲቲዎችን፣ የተለያዩ  የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ህገወጥ አሠራር በማጋለጥ ለፓርላማ በማቅረብ ታሪክ የማይረሳው አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ የሜድሮክን የወርቅ ዘረፋ፣  የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዩጵያ ቴሌኮም፣ የኢትዩጵያ መብራት ኃይል፣ የኢትዩጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዩጵያ መንገዶች ሥራ ድርጅት፣ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክና ኢንሹራንስ፣ የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት፣ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ኢንሳ፣ የመሳሰሉ ድርጅቶችን በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም በሙስናና ሌብነት እንደተጠናቀቀ በዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት ተረጋግጦል እንላለን፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በሙስና የተሸጡ የህዝብ ንብረቶቸ፣ የሪል ስቴት ድርጅቶች የከተማ መሬት ዘረፋ፣ የገጠር የመሬት ወረራ፣ የፋይናንስ ዘርፉን የባንክና ኢንሸሹራንስ ድርጅቶችን የሙስና አሰራር ነቅሰው በማውጣት፣ አይነኬ የህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ህገወጥ የንግድ ሥራ በመርማሪ ኮሚሽን እንዲመረመሩ ማድረግና ሹማምንቶቹ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የጦር መኮንኖች ያፈሩት ሃብት እንዲመረመር በማድረግ፣ ለዘለቄታዊ የመንግስት ሹሞች ግልፅና ሃቀኛ አሰራርን ይፈነጥቃል፡፡ በሃገራችን ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣ ሚዛናዊ የክልሎች የተመጣጠነ እድገት፣ ፍትሃዊ የባጀት ክፍፍል፣ የሥራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚያችን ዘመናዊ ማድረግ ለሃገራችን መፍትሄና መግባባት ይፈጥራል፡፡ ኢኮኖሚ የብሄራዊ ዳቦ ጥያቄ ነው፡፡ የሃገሪቱ ብሄራዊ የሃብት ክፍፍል ፍህታዊ ካልሆነ ሰላም የለም!!! የዋናው ኦዲተር ቢሮ በስኳር ኮርፖሬሽን 77 ቢሊዩን ብር ስርቆት፣   በሌሎች መንግሥታዊ ተቆማቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወዘተ ያደረጉትን ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት በተደጋጋሚ የቀረቡትን  የኦዲት ሪፖርቶች  የሸረሪት ድር አድርቶባቸዋል፡፡ በሙስና የተዘፈቁ የህወሓት/ ኢህአዴግ ሹማምንቶች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ጀነራል መኮንኖች፣ ቱጃር ነጋዴዎችና ኮንትሮባንዲስቶች የኦዲት ሪፖርቱ ተግባራዊ እንዳይሆን፣ የዋናው ኦዲተር ቢሮ ሠራተኞችን ኃላፊዎች በህገ መንግስቱ የተሠጣቸው ሥልጣንና ተግባር ጥርስ የሌለው አንበሳ እንዲሆን አድርጎቸዋል፡፡ በዚህም የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም የተኮላሸ ለመሆን ችሎል፡፡

በመንግሥት ውስጥ መንግሥት!!! (A State Within a State፣ አንድ አገር ብሄራዊ ኢኮኖሚዋን ለመገንባት መሠረተ ልማቶን ለማፋጠን የውጭ ምንዛሪ የሚስገኙ የግብርና ምርቶችና የማእድን ዘርፎች የሚወጡበት አካባቢ በቅድሚያ መንገዶች፣ የባቡር መስመሮችና ኤርፖርቶች ማስፋፋት አለባት፡፡ በዚህም መሰረት የኦሮሚያ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች የቡና፣ ሠሊጥ፣ የቦለቄ፣ የአበባ፣ የጫት፣ የወርቅ ወዘተ ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ ሦስት አራተኛውን የሃገሪቱን የውጭ መንዛሪ ስለሚያስገኙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ የምጣኔ ኃብት ጠበብቶች፡፡ የወያኔ መሠረተ ልማት በጠባብ ብሄርተኛነትና በአድሎ ላይ የተመሰረተ ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሪ አስተዋፅዖ በማያደርጉ ከልሎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ለውጭ ዕዳ ሃገሪቱን ዳርጎል፣ በዚህም ምክንያት በክልሎች ያልተመጣጠነ እድገት በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ የሃገሪቱ ብሄራዊ ኢኮኖሚ በክልላዊ ኢኮኖሚ በመተካቱ በመንግስት ውስጥ ስውር መንግስት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የሃገሪቱ ብድርና የዕዳ ጫና የተከሰተው በዚህ ምክንያት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡ በዚህም የተነሳ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም ተዘርፎ ከንቱ ሆኖ ወድቆል፡፡

የኮንትሮባንድ የደም ገንዘብ!!!‹‹የንግድ ሚኒስቴር የ2009 ዓ/ም የውጪ ንግድ አፈጻፀም የሚያሳየው ሪፖርት፣ወርቅ ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ የማዕድን ዘርፍ የተገኘው ወጪ ንግድ ገቢ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ በ2009 በጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፎች አንደሚገኝ ታቅዶ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ገቢ መጠን 718.6 ሚሊዮን ዶላር ቢሆነም፣ በተጨባጭ የተገኘው ግን 231 ሚሊዩን ዶላር ብቻ እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት አስፍሮል፡፡›› የቀድሞው የማእድን ሚኒስቴር የአሁኑ የማእድን፣የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር አቶ ሞቱማ መቃሳ  በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለቀረባላው ጥያቄ ‹‹ የወርቅ ኮንትሮንድ ንግድ እና በድንበር አካባቢ የሚወጣ ሕገወጥ የማዕድናት ዝውውር መስፋፋት አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ከፍተና ጥቅም እያሳጣት መሆኑን በቅርቡ ተገልፆል፤ ይሄን ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄዎች እተወሰዱ ነው›› ሲመልሱ ‹‹አገሪቱ ከምታመርተው አጠቃላይ የወርቅ ሀብት 60 በመቶ የሚመረተው በባህላዊ አምራቾች በኩል ነው፡፡ አሁንና በባህላዊ መንገድ የተመረተወ ወርቅ በአግባቡ ወደ ብሄራዊ ባንክ እየቀረበ አይደለም፡፡ ምርቱ ቢኖርም በኮንትሮባንድ ንግድ እየወጣ ነው፡፡የባህላዊ ምርቱ የሚከናወንባቸው አምስት ክልሎች ኦሮሚ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ እና ጋምቤላ ናቸው፡፡ ወርቅ በብዛት የሚገኘውና የሚመረተው ጠረፍ በሆኑ አካባቢዎች ነው፡፡ ከእዚህ ጋር ተያይዞ የተመረተውን ምርት ወደ ባንክ ከማቅረብ ይልቅ ወደ ውጪ በኮንትሮባንድ የመሸጥ ሁኔታ ይታያል፡፡ በኮንትሮባንድ ንግድ የቁም እንሰሳት፣ ሰሊጥ፣ ቡና፣ ቦለቄ፣ ጫት፣ ወዘተ በወያኔ ኢፈርት ድንበር ጥሰው ወደ ጎረቤት ሃገራቶ ወጥተው በዶላር ይሸጣሉ፡፡  አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጪ ምንዛሪ ሳታገኝ በህገወት መንገድ ወደ ውጭ የሚሄድበት ገንዘብ ከፍተኛ ነው፡፡ የብሄራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው ከዓለም አቀፍ ዋጋ አምስት በመቶ ጭማሪ በማድረግ ሆኖ እያለ እንኮን ወርቁ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቆርጦ መሸጡ ነጋዴዎቹ በጎረቤት ሃገራት ዶላር ለማሸሽና ማስቀመጥ ሲረዳቸው የሃገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ገቢን በመቀነስ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በማደናቀፍና የህዝቡን ጉሮሮ በመዝጋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በሰሜን ከኤርትር፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምስራቅ ጅቡቲና ሶማሊያ፣ በሰሜን ምዕራብ ሱዳንና በስተ ደቡብ ምዕራብ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ያዋሰኖታል፡፡ የህወሃት ጦር አበጋዞች መንግሥት፣ መከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች በዚህ ህገወጥ የድንበር የወርቅ ማዕድን ንግድ ግንባር ቀደሙን ሥራ በመስራት ወርቁን በዶላር በመሸጥ ዘረፋ ያከናውናሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የጀቱ ገንዘብ ተዘርፎ ተጠናቆል፡፡

 

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃ ነት የለም!!!

የሙስናው ቀይ መሥመር ተጣሰ፣ ህግ የለም ፍትህ የለም!!

የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››