ምንሊክ ሳልሳዊ
የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ካልታገዱ ለታቀደው ፕራይቬታይዜሽን ትልቅ አደጋ አለው ። የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ ስራ ላይ እንዳይሰማሩ ጥብቅ ህግ መውጣት አለበት። ፕራይቬታይዜሽን ጠቃሚ ነው፣ ግን ጎን ለጎን መንግስት ሙስና ላይ ዘመቻ መክፈት አለበት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ከንግድ ስር መውጣት አለባቸው፣ የተዘረፉ ሃብቶች እንዲመለሱ ያስፈልጋል ።
ሕወሓት የኢኮኖሚ የበላይነቱንና የስለላ መስመሩን ለማጠናከር በግል ኢንቨስትመት ስም አየር መንገድንና ቴሌን በመቆጣጠር ለዘረፋ ተዘጋጅቷል ።አሁን በተያዘው የሕዝብ የለውጥ መስመር ለመዝረፍ ለሕወሓት የማይቻል ሲሆን ምእራባውያን ደጓሚዎችም በሚፈጥሩት ጫና ተቋማቱ በከፊል ወደ ግል ዞረዋል በሚል ሽፋን ራሱ ሕወሓት በንግድ ድርጅቶቹና ወኪሎቹ ከእጁ እንዳይወጣ ያደርጋል ። አየር መንገድንና ቴሌን በመዝረፍ አክስሮ ከገበያ ውጪ ማድረግ እና ንብረቶችን በመውረስ ማሸሽ ሌላኛው የሕወሓት ግብ ነው። ብስለት ይጠበቅብናል ፤ በተገኘው በተነበበ መግለጫ ሁሉ ሀገር ለዘራፊዎች ሀገር ለአደጋ ተላልፋ ስትሰጥ እንደማየት አስከፊነት የለም ። ፕራይቬታይዜሽን ጠቃሚ ነው፣ ግን ጎን ለጎን መንግስት ሙስና ላይ ዘመቻ መክፈት አለበት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ከንግድ ስር መውጣት አለባቸው፣ የተዘረፉ ሃብቶች እንዲመለሱ ያስፈልጋል።
አየር መንገድንና ቴሌን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት አክስዮን ለመሸጥ መታሰቡ ሕወሓት በሌላ የዝርፊያ መንገድ መምጣቱ በቂ ማሳያ ነው ። እነዚህ ድርጅቶችን ለመቀራመት ከማቀድ በፊት የግል ባለሐብቶች በቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ እንዲሠማሩ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቀድ ይገባል ። ሕወሓት የኢኮኖሚ የበላይነቱንና የስለላ መስመሩን ለማጠናከር አየር መንገድና ቴሌን መሰል ተቋሞቹን ተቆጣጥሮ የፖለቲካ የበላይነቱን ኦሕዴድ እንዲይዝ በስፋት እየሰራ ነው ። አየር መንገድንና ቴሌን በተለያየ መንገድ በመዝረፍ ለኪሳራ በመዳረግ ከገበያ ውጪ ማድረግ ሌላኛው የሕወሓት እቅድ ነው ። ይህ ለሐገርም ለሕዝቡም የማይጠቅም እኩይ መንግስታዊ ሽብር ነው ። የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ ስራ ላይ እንዳይሰማሩ ጥብቅ ህግ መውጣት አለበት።
የባድመ ለኤርትራ መመለስም ቢሆን መስዋትነት እስከተከፈለበት ድረስ የኢትዮጵያን ጥቅም ያገናዘበ ሊሆን ይገባዋል ። የረዥም አመታት ችግሮችን ተሸክሞ ለመኖር የፈቀደ አገዛዝ የወልቃይት ጉዳይ አላላውስ ሲለው የሻእቢያ ጉያ ስር ለመወሸቅ የሚራወጠው የሕዝብንና የአገርን ብሔራዊ ጥቅም ወደ ጉድጉዋድ በመጨመር ነው። የሀገር ውስጥ ትኩሳት አጣብቂኝ ውስጥ ሲከተው ስልጣኑን ላለማጣት የሐገርን ጥቅም አሳልፎ ይሸጣል ። ነገ ከባድና ሊፈታ የሚያስቸግር አደጋ ከፊታችን እየጠበቀን እንደሆነ መዘንጋት የለብንም።
የባድመም መመለስ ሆነ የካሳ ክፍያው ውሳኔ ያገኘው በ17 ቀን ስብሰባቸው ነው ይህ የውሳኔ ዝርዝር አቡዳቢ ላይ ለኢሳያሳ ቀርቦለት ተቀብሎ በተግባራዊነቱ ላይ ተሰርቶበት ነው አሁን ይፋ ያደረጉት ገና አሰብ ወደብን እንጠቀም በሚል ሰበብ ሀገር ይራቆታል ፤ ይህ አሁን የመጣው ጉዳይ በተደጋጋሚ የተነገረ ሲሆን ከዚ በላይም አዳዲስ ነገር ይፈጠራል ፤ ወያኔ ቃላቶችን አጣፍጦና አሳምሮ ስላቀረበ የተጠቀምን የሚመስላቸው በርካቶች እውነታውን ለመፈለግ አይሹም ፤ የወያኔና ሻእቢያ ፖለቲካ በፍጹም ቅንነት የጎደለው ነው።
በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ኤርትራ ተወስኖላት የነበረው ውሳኔ በኢትዮጵያ መንግስት ምክንያት ተግባራዊ ሳይደረግ እስካሁን በመቆየቱ በቢሊየን የሚቆጠር ካሳ ሊሰጠኝ ይገባል ማለቷ አይቀርም ። እኛም በበኩላችን በአሰብ ወደብ የተወረሱ ንብረቶችን ካሳ ልንጠይቅ እንችል ይሆናል ። ነገር ግን ኤርትራ ልትጠይቀው ከምትችለው ካሳ አንፃር እኛ ልናገኝ የምንችለው ኢምንት ነው ።
Minilik Salsawi