የዓዲግራት ከተማ የኢሮብ ብሄረሰብ ነዋሪዎች ትልቁና ታሪካዊ ስብሰባ ኣደረጉ። የስብሰባው ዋና ዓላማ በቅርቡ የኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ የኣልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሉን በመቃወም ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ስምምነት ተቀብሎ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ የኢሮብ ህዝብ በሁለት ይከፍላል፤ በሁለት የተከፈለ እንደሆነ ብሄረሰቡ እንደ ብሄረሰብ መቀጠል ኣይችልም።
ሰለዚህ በስብሰባ የተወሰነ ውሳኔ፦

– የኣልጀርስ ስምምነት ብሄረሰቡን የሚያጠፋ በመሆኑ የኢሮብ ህዝብ ኣይቀበሎውም
– በማንኛውም ታርክ ዘመን የኢሮብ ህዝብ የኤርትራ ኣካል ሆኖ ኣያውቅም
– ኢትዮጵያዊ ዜግነት ኢሮብ ህዝብ በደሙና በተፈጥሮ ያገኘው እንጂ በፖሊቲካ ውሳኔ ኣይደለም፤ በመሆኑ የኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ የውሳኔውን እንደገና ማየት እንዳለበት ኣሳስቧል
– በከተማ ደረጃ 9 ኣባላት ያለው ኣስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም ሰብስበው ተጠናቀቀ