በኢትዮጵያ አዲሱ አብይ ወደ ሥልጣን ከመጣ በየቀኑ ብዙ የምንደሰትባቸው ነገሮች እየሰማን ነው፡፡ ሰሞኑንም ብዙ አሉ፡፡ ከሰሞኑ ከሰማናቸው አንዳንዶቹ ግን ምን ያህል ተጠንቶባቸው እንደሆነ አላውቅም፡፡ ከነዚህ የሰሞኑ ዜናዎች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ትልልቅ የመንግስት (የሕዝብ) ተቋማት ለግል ነጋዴዎች በከፊል ሊሸጡ መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ ስህተት እንዳይሰራ ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ የመንግስተ የንግድ ተቋማት በከፊል ሆን በሙሉ ለባለሀብቶች መሸጥ የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ተቋማት ግን በመንግስት እጅ መቆየት ግድ የሚላቸው ይኖራሉ፡፡

ያም ሆኖ በመጀመሪያ የተቋማቱ አሁን ያሉበት አደረጃጀትና አስተዳደራችን መፈተሽ ከሽያጭ ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ይመስለኛል፡፡ ተቋማቱ በከፊል አክሲዮን ሸጡም አልሸጡም ቅድሚያ  የእነዚህ ተቋማት መዋቅርና አስተዳደራቸውን ማሻሻል ይገባል ባይ ነኝ፡፡ በሌሎቹ ተቋማት ምን ያህል እንደሆነ ባላውቅም ከተጠቆሙት ተቋማት በተለይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለ እፍረት ትግሬ ወያኔዎች እንዲሰገሰጉበት ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክነያት ብዙዎች ብቃት ያለቸው ሰራተኞች ትግሬ ስላልሆኑ ከተቋሙ እንዲወጡ ሲደረግ በምትካቸው ያለ ብቃትና ችሎታ በትግሬነት በሚመደቡ ተወረዋል፡፡ የአየር መንገዱ ብቻም ሳይሆን ከአየርመንገዱ ጋር የተያያዙ የጉምሩክና ኢሚግሬሽን ድርጅቶችም በትግሬ ተሞልተዋል፡፡ ይህ ነበር ኢትዮጵያን በመጨረሻ  ወደ አደጋ እየከተታት የነበረው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት አልፈልግም፡፡ ከእንግዲህ ግን ኢትዮጵያውያን በተለይ በቦሌ አየር ማረፊያ ትግሬ የሙሉባቸውን ተርሚናሎች ማይት አይፈልግም፡፡ ይህ ቅድሚያ ሊታሰብበት የሚገባ ነው፡፡ ከላይ እስከታች ያለው አስተዳደርም እንደዛው ነው፡፡ ግን ዜጎችን ለመሰለልና ችግር ለመፍጠር የተቀጠሩ የወያኔ ሰላዮች ዛሬውኑ ከዛ ቦታ መጽዳት አለባቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰውም ሌሎች ተቋማትም ኢትዮጵያን ክደው ሁሉም እናፈረሳታለን እያለ ሲፎክር አየር መንገዱ ብቸኛው ለአገሩ ታማኝ የሆነ ተቋም ነው፡፡ ይህ ሰዎች ሳያስተውሉት አየር መንገዱ (አውሮፐላኖቹ) ኢትዮጵያዊነትን ሲሰብኩ ኖረዋል፡፡ አስተውሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮከብ የሌለበት ባንዲራ ይዞ በአለም ሁሉ ይዞራል፡፡ አንበሳውም ከፊት እንዳለ ነው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ንጉሰ ነገስቱ ለአየር መንገዱ በአደራ የሰጡት ይመስላል፡፡ እሱም አደራውን ጠብቆ ይሄው ዛሬም አለ፡፡  በዚህ የኢትዮጵያ አይር መንገድ ከሌሎች ተቋማት የተለየ ነው፡፡ ሥሙና ክብሩም እዚሁ አደራን መተበቁ ላይ ነው፡፡ የቱንም ያህል ወሮበሎች ቢገቡበትም የኢትዮያ ነኝ ብሎ በአቋሙ የጸና ብቸኛ ተቋም ነው፡፡ በእርግጥ በሥራውም ኢትዮጵያውያን በሌሎች ዘንድ እንድትከበር የሚያደርግ ነው፡፡

ስለሌሎቹ አላውቅም ይህ ተቋም ግን ከኢትዮጵያዊያን(ሕዝብ/መንግስት) ውጪ ምንም አይነት ሌላ ባለሀብት ባለቤት ባይሆንበት እላለሁ፡፡ ይህን ተቋም ለማስፋፋትም ሆነ ለማዘመን ቢፈለግም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚሳተፉበት ልዩ አሰራር እንዲኖረውና አቅሙን ማሳደግ እንጂ ለግል ባለሀብት መሸጥ ኢትዮጵያዊነትን እንደመሸጥ ይሰማኛል፡፡ ስለዚህ ይን ተቋም መንግስት (ሕዝብ) የራሱ ብቻ ሊያደርገው ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በኋላ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ትርፍ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን በአለም መድረክ ከፍ እንዲሉ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ከኪሳቸውም አውጥተው ቢሆን ተቋሙን ለአገሪቱና ለሕዝቦቿ እንደ ልዩ የክብር ሀብት ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያውያን ልዩ እሴት ሆኖ መቀተል አለበት፡፡ ተቋሙ የገንዘብ ትርፍ የሚያመጣ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ግን ለዜጎች እንደ ልዩ እሴት ሆኖ በመንግስት እጅ ይቆይ ባይ ነኝ፡፡ እናንተስ ምን ትላላችሁ?

ሰሞኑን የባድሜ ጉዳይ ዋና ወሬ ነው፡፡ ስለባድሜ ብዙም ስሜት የለኝም፡፡ ይልቁንም በባድሜ ስም ኢሳያስና መለስ ለሰሩት ድራማ እንደ ግብዓት የተጠቀሟቸውን በመቶ ሺዎች ዜጎች ያለቁበትን ሳስብ እበሳጫለሁ፡፡ በተለይ ኢሳያስንና አሰብን ሊይዝ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሆን ተብሎ ነው እንዲያልቅ የተደረገው፡፡ ዛሬ በድሜ እያሉ ሊያደናግሩን ይፈልጋሉ፡፡ ባድሜን ሥሟን እንኳን አናውቃትም ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ሌላ ሊታሰብበት የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ አለ፡፡ አብይ ይህን ጉዳይ ይረዳው አይረዳው አልገባኝም፡፡ ግን በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሰራዊት ከኤርትራ ድንበር መልቀቅ የለበትም ባይ ነኝ፡፡ እንደውም ከወያኔ አዛዦች የጸዳ ልዩ ኃይል በሥፍራው ሊቆይ ያስፈልጋል፡፡ ከ40 ዓመት በላይ ሲወጠን የኖረ ትልቅ ሴራ እንዳለ ነው የሚገባኝ፡፡ ባድሜን እንደፈለጋቸው ያድርጉ፡፡ የኤርትራ ሕዝብ ራሱ ጠላን እንጂ እኛ ድሮም ምንም አላደረግነውም፡፡ ኢትዮጵያ ኤርትራውያንን ብልዩ ሁኔታ ነበር ስትንከባከባች የነበረው፡፡ ዛሬም እኛ ቂም አልያዝንም፡፡ ከኢትዮጵያ መገንጠል ሲንጋፖርን ያደርገናል ብለው ነው የሄዱት፡፡ወያኔ ስትገባ ቤተመንግስቱና የኢምባሲ መስራቤቶች ሳይቅር በኤርትራውያን ነበር በዋነኝነት የተሞሉት፡፡  ለማንኛውም የመለስና የኢሳያስ ሴራ ብዙ ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ትንሽ ኢትዮጵያዊነት የነበራቸውን ብዙ ወያኔ ትግሬዎችም በኤርትራ ጉዳይ ባላቸው አቋም እስከወዲያኛው ነው ዝም እንዲሉ የተደረገው፡፡ እዚህ ላይ ክንፈ ገ/መድህንንና ኃያሎም አርዓያን እንደምሳሌ ማቅረብ ጥሩ ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ለምን እንደተገደሉ ሚስጢሩን የሚያውቅ አለ? ዛሬ በሕይወት ያሉ ወያኔ ትግሬዎች አሳምረው ያውቃሉ ግን እነሱ የሴራው ተባባሪ ስለሆኑ ሚስጢሩ እንዲታወቅ አይፈልጉም ይመስለኛል፡፡

ወዳጆቼ እና ጉዳዩ የባድሜ ሳይሆን አሁንም ሻቢያና ወያኔ መካከል ልዩ ቁርኝት እንዳለ መዘንጋት ሞኝነት ነው፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በሌሎችም ሊደገፍ እንደሚችል ማሰብ ጥሩ ነው፡፡ የወያኔና ሻቢያ የነፍስ አባት የሆነው አሜሪካዊው ሄርማን ኮኸን በቅርብ ቲዊት ያደረገውን ጉዳይ ብዙዎች ያያችሁት መሰለኝ፡፡ በተለይ ኢንግሊዝና አሜሪካ ለእኛ ጥሩ እንዳልሆኑ  ግን ሁሌም መዘናጋት ኤገባም፡፡ ለ27 ዓመት ወሮበሎችን እየደገፉ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ግፍ እንደ ጥቁር ታሪክ የምናስታውሰው እውነት ነው፡፡ ልብ በሉ እንደነ ጃፓን፣ ጀርመን የመሳሰሉ አገሮች ኢትዮጵያን በታወቀ የልማት ሥራ ነው የሚደግፉት የአሜሪካና ኢንግሊዝ ግን አንድም ቦታ በዚህ መልክ የለም፡፡ ገንዘቡ ወይ በኤንጂኦ ወይም በወሮበላ ታማኞቻቸው በኩል ነው የሚሰጠው፡፡ ለማንኛውም አሜሪካዊው የወያኔና የሻቢያ ነፍስ አባት አሁንም እንዲህ እያለን ነው፡፡

እና ወገኖቼ በሁሉም አቅጣጫ ምንቃት ያስፈልገናል፡፡

አመሰግናለሁ!

ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!