የአገራችን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች እና ቢሆኑዎች፦

ወደ ዝርዝር ጉዳዩ ከመግባታችን በፊት «ወቅታዊ» ፣ «ተጨባጭ» ፣ «ሁኔታዎች» እና «ቢሆኑዎች» የሚሉትን ቃሎች በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ መገንዘቡ የመረጥነው ርዕስ ተፈላጊውን ግንዛቤ ለመጨበጥ ይረዳል።

– «ተጨባጭ» ስንል፣ በዓይን የሚታዩ፣ በእጅ የሚዳሰሱ ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች እና ግጭቶች ማለታችን ነው።
– «ሁኔታዎች» ስንል በአገራችን በመከናወን ላይ ያሉ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክስተቶች፣ ድርጊቶች፣ ክንውኖች፣ የኃይልና የቡድኖች አሰላለፍ ዝግጅቶች ማለታችን ነው።
– «ቢሆኑዎች» ስንል ማኅበራዊ ሣይንስ እንደ ተፈጥሮ ሳይንስ ቋሚ ገዥ ሕግ የሌለው በመሆኑ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚከናወኑትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ጉዳዮች፣ አንድነትና ልዩነት፣ ቁርኝትና ግፊት፣ ተዛምዶና ተቃርኖ በማየት ሊከተል የሚችለውን

ውጤት ይህ ሊሆን ይችላል፣ ይህ ካልሆነ ይኸ ይሆናል በማለት፤ ሊሆን ይችላል የሚባሉ ጉዳዮችን አስቀድሞ የማሳየት ነው። ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉት ቢሆኑዎች ደግሞ ከመረጃዎቹ ጥንካሬ አንፃር በመነሳት በቅደም ተከተል የሚተነበዩ ናቸው። ባንድ ቃል ቢሆን ማለት ወደፊ የሚሆን፣ የሚከሰት ሁኔታ ማለት ነው። የቢሆን ትንበያዎች ዕውን መሆን የሚችሉት፣ እንዲሆን የሚፈለገው ነገር እንዲሆን፣ በሚሠሩት ኃይሎችና ቡድኖች ሁለንተናዊ ጥንካሬ ላይ በመመሥረት ሊሆን ይችላል የተባለውን ጉዳይ የማስፈጸም አቅም መጎልበትን ይጠይቃል።
1 የኢትዮጵያ ተጫባጭ ሁኔታ፦

(1.1) ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት አገራችን ለውጥ አዋላጅና ለውጥ አጨናጋፊ የሆኑ ኃይሎች ፊት ለፊት የተፋጠጡበት ወቅት ነው።ለውጥ አጨናጋፊው የፈለገውን ያህል የለውጡ ደንቃራ የመሆኑ ጉዳይ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ለውጡ ግን አይቀሬ መሆኑን የሚያመላክቱ ጠናካራ ነባራዊ ሁኔታዎች ያሳያሉ። የጠንካራው ነባራዊ ሁኔታ ማሳያዎቹ ሕዝባዊ ዕንቢተኝነቱ እና ተቃውሞው ከአገሪቱ መሀል እስከ ጠረፍ ድረስ በተቃውሞ ሰልፎች በመናጥ ላይ መሆኗ አንዱ ነው። ባጭሩ፣ ወቅቱ አገራችን መሠረታዊ የሆነ ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት ምጥ የተያዘችበት እና ለውጡ ጤነኛና ለኢትዮጵያውያን ኅልውና ዕውን መሆን ጥበበኛ አዋላጅ ኃይል የምትሻበትና፣ የሚወለደው የአዲስ ሥራዓት ተጠሪ የሚሆነው ኃይል ሳይወለድ እንዲጨነግፍ በሚሻው የትግሬ ወያኔ ቡድን መካከል ፍጥጫ የገባችበት ወቅት ነው።

(1.2) ወቅቱ ዕውነተኛ መሠረታዊ የሆነ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ለውጥ ዕውን እንዲሆን የቆሙ ኃይሎችና ለውጡ በጥገናዊ ለውጥ ታጅቦ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተባባሪ የሆኑ ኃይሎች፣ ሌላ ተጨማሪ የመከራ አገዛዛቸውን በሕዝባችን ላይ አስፍነው ለመቀጠል የሚሹ ኃይሎች ፊት ለፉት የተፋጠጡበት ጊዜ ነው። ….. (Read more)