በሃራጅ ሊሸጥ ገዥ እየተፈለገለት ያለው የኢትዮጵያ የአየር መንገድ

(ሚኪ አማራ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉድና ለምን በሃራጅ እንደሚሸጥ (ET is in deep trouble too)
—————————
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምናልባትም በአለም ካሉት የኮርፖሬት ካምፓኒዎች ጥያቄ የጠየቁ ሰራተኞችን የሚቀጣበት የምድር እስርቤት ያለዉ ብቸኛዉ ካምፓኒ ሳያደርገዉ አይቀርም፡፡ በአየር መንገዱ አሰራር ላይ ጥያቄ ያነሳ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አንጋር አካባቢ ወደ ሚገኘዉ ቀዝቃዛ እስር ቤት ለሳምንታት ወይም ለወራት ልትታሰር ትችላለህ፡፡ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ በዚህ እስር ቤት ጠባቂዎች የመደፈር ጉዳይ አለ፡፡ ብዙ ሰዉ ይህ ድርጅት አትራፊ ነዉ ለምን ይሸጣል ይላል፡፡ በርግጥ በአመት 50 ወይም 100 እስከ 200 ሚሊየን ዶላር አትርፎ ያዉቃል፡፡ ነገር ግን ከአሜሪካ ባንኮች፤ ከቻይና አግዚም ባንክና እና ከህንድ ባንክ የተበደረዉ ብድር የትእየለሌ ነዉ፡፡ ለራሱ ለድርጅቱ ብቻ ሳይሆን መንግስት በዚህ ድርጅት ሰበብ ለራሱ ይበደርበታል፡፡ አሁን ላይ በየአመቱ መንግስት ከሚከፍለዉ የብድር እዳ 60% የአየር መንገዱን እዳ ይሸፍናል፡፡እስኪ ከብዙ ችግሮች ዉስጥ አንዱን ለምሳሌ ላንሳዉ፡፡

የአምስቱ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የማኔጅመንቱ ድብቅ ቁማር
ANA (All Nippon Airways) በመባል የሚታወቀው የጃፖኑ አየር መንገድ ከቦይንግ ካዘዛቸው በርካታ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ውስጥ ቀድመው ተመርተው የነበሩት B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በነበራቸው የምርት ጥራት ችግር የዲዛይን ደረጃቸውን ስለማያሞሉ እና በዚሁም ምክንያት አውሮፕላኖቹ ምንም ሳይጭኑ ከባድ በመሆናቸው እና የጭነት መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና አጭር ርቀት ብቻ መብረር በመቻላቸው በመሳሰሉ ትክክለኛ ምክንያቶች ከቦይንግ አልወስድም ብሎ ስለተዋቸው ፈላጊ አተው ለበርካታ አመታት ቆመው ነበር። የኢት ማኔጅመንት ግን እኒህን 5 አዉሮፕላኖች በጥቅም ተደልሎ ተቀብሏቸዋል፡፡

በቦይንግ አሰራር መሰረት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለአየር መንገዶች ብቻ እንደሚሸጥ ይታወቃል። በዚህም መሰረት South America አካባቢ የሚገኝ አውሮፕላን ገዝቶ በማከራየት የሚታወቅ አንድ ካምፖኒ እነዚህን አውሮፕላኖች ከመግዛቱ በፊት በዚህ standard ማንም እንደማይከራየው ስለሚያውቅ እና በቀጥታ ቦይንግ ስለማይሸጥለት በድርድር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያንዳንዱን 90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ከቦይንግ እንዲገዛው ካደረገ በሆላ ይሄው ካምፖኒ ገንዘብ ጨምሮ ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መልሶ በመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ25 አመታት በላይ አውሮፕላኑ እስኪያረጅ ድረስ ተከራይቶ እንዲያበርለት የሚያስገድድ ውል ከማኔጅመንቱ ጋር ይፈራረማል፡፡ይሄው ዛሬም ተዋረዱ ሲላቸው ከጅምሩ ጀምሮ በፋን ብሌድ ዝገት፣ በሞተር ዘይት መፍሰስ በመሳሰሉ አወዛጋቢ ችግሮች ሲገጥመው በቆየው የተገጠመለት Trent 1000 Rolls Royce ሞተር ችግር ምክንያት ፓርቱ እስኪገኝ ድረስ አራቱ አውሮፕላኖች እዳቸው እየተከፈለ ላልታወቀ ረጅም ጊዜ እንዳይበሩ ተደርገዋል። የዚህ አውሮፕላን የሊዝ ክፍያ በዶላር በወር 800,000 እስከ 1.25 ሚሊየን USD ድረስ ነው (በዚህች በደሀ ሀገር ላይ ይሄ ዶላር ምን ያህል ቁም ነገር ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ነው) ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ B787 ድሪም ላይነሮች የነዚህ የተበላሹ አውሮፕላኖች መስመርን ለመሸፈን ሲባል ለጥገና መግባት ከነበረባቸው ሰአት በላይ ሴፍቲን በሚፃረር ሁኔታ እየበረሩ ይገኛሉ። እነዚህን አውሮፕላኖች ጨምሮ Trent 1000 Rolls Royce ሞተር የተገጠመላቸው አውሮፕላኖች ሁሉ ሞተራቸው ላይ ያለው ችግር ያለበት ፖርት እስኪቀየር ድረስ አውሮፕላኖቹ በገናናዎቹ የአየር ደህንነት ተቆጣጣሪዎች እንዳይበሩ መታገዳቸው ይታወቃል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ቀድሞ መፈረም የነበረበት ወረቀት CEO አቶ ተወልደ ቢሮ ሳይፈረም ሲገላበጥ ቆይቶ የሚፈለገው መለዋወጫ በጊዜ ሳይገዛ በመቅረቱ እና ሌሎች አየር መንገዶች ቀድመው ጠራርገው በመውሰዳቸው ፖርቱ መገኘት አልቻለም። ኪሳራውም በቀን 110,000 ዶላር በላይ ይገመታል ። በዚህም ምክንያት የአውሮፕላኖቹ መቆም የፈጠረው መዘዝ እና ንትርክ ምክንያት የአውሮፕላኖቹ የሽያጭ እና ሊዝ ሚስጢር ሊታወቅ ችሏል፡፡ይሄም ያለ ጥናት ችግራቸው እየታወቀ በ CEO ትእዛዝ በመገዛታቸው በቀጥታ የአየር መንገዱን CEO ተጠያቂ አድርጎቸዋል። በዚህ ንትርክ ዉስጥ ከአየር መንገዱ የሴኪዉሪቲ ቢሮ ፊት ለፊት የሆነዉ የአቶ መስፍን (COO) ቢሮ ተሰብሮ የእነዚህን አዉሮፕላን የቴክኒክ ጉዳዮች እና ሌሎች መረጃወችን እንዲሁም የሰዉየዉን ላፕቶፕ ተሰርቋል፡፡ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት አቶ መስፍን እኒህን ዶክመንቶች በጥንቃቄ የያዘ ሲሆን አቶ ተወልደ ችግሩን ለማዳፈንና የቴክኒካል ጉዳዮችን ያማከረኝ አቶ መስፍን ናቸዉ ለማለት እንደሆነ ይገመታል፡፡ከዚህም በላይ አየር መንገዱ ለዉጭ አብራሪዎች የሚከፍለዉ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላኛዉ ወጪዉ ነዉ፡፡ ስለዚህም በአመት 100 ሚሊየን ዶላር ቢያተርፍም አየር መንገዱ ያለበት በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር እዳ መንግስት ከሚሸከመዉ አቅም በላይ ሁኖበታል፡፡

በ2010 ገደማ የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን መንግስት የአየር መንገዱንና የኢትዮ ቴሌኮምን በጀትና የብድር መጠን እንዲያሳዉ በተደጋጋሚ እንደጠየቀ ዊክሊክስ ላይ የተለቀቀዉ የኢ-ሜል መረጃ ያሳያል፡፡ በጊዜዉ የንግድ ሚኒስቴር የነበረዉን መኮነን ማንያዘዋልን ኤምባሲዉ ድረስ ጠርተዉ በአየር መንገዱ የብድር መጠን ላይ ጥርጣሬ ስላለን በጀቱን እንዲሰጣቸዉ ቢጠየቅም፡፡ የአየር መንገድ የፋይናንስ ጉዳይ ማንም አያዉቅም ስለዚህም መረጃ የለኝም የሚል መልስ እንደሰጣቸዉ ኤምባሲዉ ለስቴት ዲፓርትምንት የላከዉ ኢ-ሜል ያሳያል፡፡ የአሜሪካ መንግስት በአይ ኤም ኤፍና አለምባንክ በኩል ለኢትዮጵያ በሚሰጠዉ እርዳታ መንግስት የነዚህን ድርጅት በጀት ካላሳወቀ እንዲያዝ እንደሚያደርግ ገልጾ ነበር፡፡

**************************

The History of Aviation in Ethiopia

History of aviation in Ethiopia goes back to 1929 when French made airplane, Potez 25 flown by a French pilot Andre Milet landed in the western side of Addis Ababa enrooted from Djibouti. This was 26 years after the first attempted flight by the Wright brothers and two years after the famous flight across the Atlantic by Captain Lind burg. Although Millet piloted the first aircraft which marked the history of aviation in the country, soon came with his successors with other types of airplane after one month time- in the month of September.

In 1930 five sweater airplane like Farman-192 and others were purchased by the government for postal, security and government services between the towns of Dire Dawa, Djibouti, Debremarkos and Gondar. The dream that Ethiopian they would pilot the airplane was not long in coming true. In 1930 Gaston Vidal, a French Instructor, established the first pilot training Scholl in the town of Jigjiga which produced Mishka babichief and Asfaw Ali who were certified to be the first Ethiopian pilots. Mishka made his first solo flight on sept. 1, 1930 followed by Asfaw Ali only after thirteen days. Very soon Bahiru Kaba and Tesfamikael Haile were also added to the number. What is remarkable of that time was that W/ro Mulumebet Emrru also turned out to be one of the first Ethiopian female pilots. The school at Jigjiga was not only limited to the pilot training, but also added aircraft maintenance. Maintenance work was also began at Jenmeda (Addis Ababa) and Dessie. From 1926-1936 new domestic routes were opened to Gefersa, Bishoftu, Janmeda and Akaki, and the country had also acquired twenty airplanes until the occupation of Italy.

The aircraft technology did also cross a new frontier in Ethiopia with the assembling of the first aircraft named ETHIOPIAN ONE or TSEHAY by Land wing Weber, German national and engineer-in-charge. But During the Italian occupation the Ethiopian patriots camouflaged ETHIOPIA ONE in a forest with the idea that it would escape the Italian loot. But all their effort was in vain since the Italians got access to the hidden aircraft which today is kept in a museum in a naval force near Rome.

The first Aircraft manufactured in Ethiopia known as “Tsehay”

In 1930 the first maintenance technicians and flying school established in jigjiga, eastern Ethiopia and our forerunners were graduated in 1931. In 1944 the Ethiopian government was invited by the United States of America to attend the Chicago conference of December 7, 1944. This made Ethiopia one of the few African nations to sign the convention of the International Civil Aviation Organization. This same year another major step was taken by the Government of Ethiopia and the Civil Aviation Authority was founded. One year later in 1945 Ethiopian Airlines was founded with six-second world surplus DC-3/c-47 airplanes. In 1951 through the technical assistance provided by the International Civil Aviation Organization aviation school was opened in Addis Ababa. The first 60 trainees of the school were trained in Communication, Navigation, Aircraft, Metrology, and Radio operation and maintenance.

Source: http://www.ecaa.gov.et/History.aspx

 

ሌሎች በሃራጅ ሊሸጡ ገዥ እየተፈለገላቸው ያሉ የኢትዮጵያ አንጡራ ሀብቶች (ዘመዱሁን በቀለ እንደጻፈው)

– የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን በእምዬ ሚኒሊክ ተመሠረተ። – የኢትዮጵያ ቴሌኮሚንኬሽን በህውሓት ተሸጠ።

– የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመሠረተ። – የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህውሓት ተሸጠ።

– የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን በጃንሆይ ተመሠረተ።  – የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን በህውሓት ተሸጠ

– የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በአጼ ካሌብ መሠረቱ ተጥሎ በአጼ ኃይለ ሥላሴ በዘመናዊ መልኩ ተመሠረተ። – የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በህውሓት ፈረሰ።

– የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት በአጼ ኃይለሥላሴ ተመሠረተ።  – የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት በህውሓት ፈረሰ።

– የኢትዮጵያ ባቡር ድርጅት በእምዬ ሚኒሊክ ተመሠረተ።   – የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት በህውሓት ተሸጠ

– ራሷ ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ተፈጠረች።   –   ራሷ ኢትዮጵያ በህውሓት ተሸጠች።