ኢትዮጵያዊነት እንዲያገግምና እንዲለመልም “የጎሣ ፌደራሊዝም” እንደ በርሊን ግንብ ይፍረስልን!

የበርሊን ግንብ ለሁለት ከፍሎ የነበርው ምስራቅንና ምዕራብ ጀርመንን ብቻ አልነበረም:: የለያየው ጀርመኖችን ከጀርመኖችም ነበር:: የእንግሊዝ ጠ/ሚ ማርግሬት ታቸር ስለ በርሊን ግንብ ሲገልፁ “እያንዳንዱ ድንጋይ ለተንሰራፋው የህብረተሰብ የሞራል ዝቅጠት ምስክር ነው” ብለው ነበር

የበርሊን ግንብ (Berlin Wall) ሲፈርስም መጀመሪያ የተገናኙት ጀርመኖች ከጀርመኖች እንጂ ምስራቅንና ምዕራብ ጀርመንም አልነበሩም:: ይህ ክፍፍልና መለያየት የተከሠተው በሂትለርና በናዚዎች ርዕዮት ሣቢያና መዘዝም ነው::

በእኛም ሃገር የኢትዮጵያን ህዝብ በጎሣ ከፋፍሎ እንደ ጀርመን ግንብ የለያየው አፖርታይዳዊውና ወያኔ ጠንሣሹና ሠራሹ “የጎሣ ፌደራሊዝም” ስርዐትና “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮተ-ዓለማዊ ግንብ ነው:: ይህ ስርዐትና ርዕዮት ልክ እንደ በርሊን ግንብ ‘የሞራል ዝቅጠት’ ምልክት ነው:: ጎሣን ከጎሣ አናክሶ አብሮነትን የሚገድብ እሾካማ መርዝ ነው:: ወያኔና ጨቋኝ ስርዐቱ የሚናደው ልክ እንደ ናዚዝም ይህ እንሠሣዊና “የጎሣ ፌደራሊዝም” የተሰኘው ስርዐትና አብዮታዊም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮቱ ሲናድና ሲፈርስ ብቻ ነው::

ጠ/ሚ አቢይ አህመድ!
ይህ በቅን ልቦና የቀረበ ጥያቄ ነው::

ያወደሱትን ኢትዮጵያዊነት እንዲታደስና እንዲያንሰራፋ አስፈላጊውን ግብዐት ይመግቡት:: የአሜሪካን ፕሬዝደንት የነበሩት ሮናልድ ሬገን እ.አ.አ. በጁን 12/1987 በበርሊን ግንብ ፊት ለፊት ቆመው ለቀድሞ የሶቪየት ህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ጎርቫቾቭ “ይህንን ግንብ አሁኑኑ ይናዱት” ብለዋቸው ነበር:: ጎርቫቾቭም ናዱት:: እኛም ጠ/ሚ አቢይን ይህን “የጎሣ ፌደራሊዝም” ግንብ አሁኑኑ ይናዱልን እያልን እንደ ሮናልድ ሬገን እንጠይቃለን:: እርስዎም ልክ እንደ ጎርቫቾብ ይገርስሱልን::

“የጎሣ ፌደራሊዝም” የሚመጥነው እንሠሦችን እንጂ የሠው ልጆችን አይደለም::

==++==

Let “Ethnic Federalism” be perished first if we all honestly & desperately need the resurrection & triumph of Ethiopiawinet.

The Berlin Wall didn’t only have divided the German nation into East & West blocks; but also disconnected Germans from fellow Germans. Margaret Thatcher, about German wall, once said “Every stone bears witness to the moral bankruptcy of the society it encloses”.

During the toppling down of Berlin Wall, it wasn’t the two German nations blocked by wall first united but the two Germans disjointed by a man made barrier. All divisions made as a result of horrifying actions of Adolf Hitler & his Nazi party.

Shifting to our Ethiopian current political situation, it’s the “Ethnic Federalism” that is detaching Ethiopians from fellow Ethiopians just like the Berlin Wall. “Ethnic Federalism”, as Nazism, is a sign of moral bankruptcy. TPLF’S social order named “Ethnic Federalism” together with its ideology “Revolutionary Democracy”, that’s best fitting a fundamental animality, should be dismantled like that of Nazism & the German wall as well.

Prime Minister Abeiy!
This is an earnest entreating.

Please arm your of Ethiopiawinet narrative’s with the tools vital to its rejuvenation.

American president Ronald Reagan, in his speech in front of Berlin Wall on June 12/1987, said “Mr. Gorbachev, tear down this wall!”.
Prime Minister Abeiy, we also kindly ask you, as Reagan asked Gorbachev, to tear down “Ethnic Federalism”. Just tear it & do what Gorbachev did it & it’s heroic.

“Ethnic Federalism” best serves animals than humans.
#PrimeMinisterAbeiyAhmed