አጼ ሚኒሊኪ

ዛሬ ገዳን ያገኘንው በሚኒሊክ ምክነያት ነው፡፡  የኢትዮጵያው ታላቅ መሪ አፄ ሚኒሊክ ለኦሮሞ ሕዝብ ልዩ ክብርና ቦታ ነበራቸው ስንል ከምንም ተነስተን አደለም፡፡ ምንም እንኳን አገሪቱን በመሩበት ዘመን ሁሉ በመንግስታቸው ዛሬ ኦሮሞ እየተባለ የሚጠራው ሕዝብ ልጆች በበላይነት የተሳተፉበት እንደሆነ ታሪክ ቢሟገተንም ያ ታሪክ እውነት ባይሆን ትልቅ ምኞታቸው የሆነ በሚኒሊክ ላይ ትልቅ ጥላቻ ያላቸው ዛሬ የሚኖሩ ኦሮሞውች ብዙ ናቸው፡፡ ሚኒሊክ ማንንም ሕዝብ በማንነቱ አልበደሉም፡፡ ለኦሮሞ ግን ልዩ ሥፍራ ስላላቸው የመንግስታቸውን ሥልጣን በአብዛኛው ያስያዙት ከዚሁ ሕዝብ በወጡ ልጆች ነው፡፡ በመጨረሻም አልጋ ወራሻቸው ያደረጉት ከኦሮሞ የሚወለደውን ኢያሱን ነው፡፡ ይህ ሁሉ እውነት እያለ ዛሬ ብዙዎች በገዳዮቻቸው በተሰበገላቸው ወሬ እውነቱን ክደዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ እስኪ አንድ ተጨማሪ እውነት የሚከተለውን ሊንክ ላይ ያለውን እውነት ያድምጡ፡፡ ሚኒሊክ የገዳ ሥርዓት ቆይቶ ዛሬ እንድናየው ዋና ባለውለታ እንደሆኑ፡፡ ይህን እውነት የሚመሰክሩት የገዳን ሥርዓት በጥልቀት ያጠኑት ኤርትራዊው አስመሮም ናቸው፡፡ ቃለ መጠይቁን ያደረገላቸው የፊንፊኔ ራዲዮ ነው፡፡ ለአድማጭ እንዲቀል ሚኒሊክ ገዳን እንዴት ከመጥፋት እንዳዳኑት የሚነጋሩበትን ቦታ ብቻ ቆርጬ ነው ሊንኩን የምጋብዛችሁ፡፡ ጊዜ ከአላችሁ ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ብታደምጡ ብዙ እውነቶችን ትሰሙበታለችሁ፡፡ እሱንም ከታች ትቼላችኋለሁ፡፡  ትንሽ ከኋላ መነሻውን እንድትሰሙት ሰፋ አድርጌ ነው የቆረጥኩት፡፡

ሙሉው ቃለ መጠይቅ ከዚህ በታች፡፡ በዚህ ቃለ መጠይቅ ሌላ ብዙ ኦሮሞዎች በተሳሳተ ወሬ ስለ ታሪከ ጸሀፊው አባ ባህሬ ያላቸውን አመለካከትም እራሳቸውን እንዲጠይቁ ያደርጋል

https://www.youtube.com/watch?v=1ZqDFvRMVmc

ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!