ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ሲሆንበአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛው ነው። ጣና የአካባቢው ነዋሪ የህልውናመሰረት የሆነ በአገር አቀፍ ደረጃደግሞ ታሪካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ  ባህላዊእንዲሁም ሃይማኖታዊ ቅርስከመሆኑም በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ UNESCO የብዙ አእዋፍ፣ ኣሳዎችእንዲሁም እፅዋት ምንጭ ( biodiversity) እውቅና ያገኘ ሐይቅ ነው።

ሃይቁን የአካባቢው ሕዝብ ለማጓጓዣ፤ ለአሣምርት፤ለመጠጥ፤ለመዝናኛ፤ለእርሻ(ግብርና)፤ለቱሪዝም እንዲሁምለግንባታ(አሽዋ) የሚያገለግል ነዉ። በሃይማኖት በኩል በብዙዎች ደሴቶችየሚገኙት ገዳማት እና ቤ/ክርስቲያናት ለክርስትና እምነት ታላቅ ድርሻሲያባረክቱ ቆይተዋል;፡

ክ2012 (እኤአ) ጀምሮ ጣና Water hyacinth (እምቦጭ) በተባለ ባዕድ አረምበመወረሩ የአካባቢው ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ውጭ በመጡ አገር ወዳድኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውንና ጎልበታቸውን መስዋዕት ባደረጉ ወግኖች አረሙሲወገድ ቆይቷል። በቅርቡ ደግሞ በዉጭ አገር በሚኖሩ  ኢትዮጵያዉያን በብዙ ጥናት አፈላልገዉ ይህን አረም የሚይስወግድ መሳሪይ ተግዝቶ ተልኮበቦታው ደርሷል። ለዚህ ግንባር ቀደም አራያነት ስራቸዉ ከፍ ያለ ምስጋናችን እናቀርባለን።

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ደግሞ ጣናን ለመታደግ ይረዳ ዘንድክዚህ በታች የሚታየውን መሳሪያ (Aquamarine H5-200 Harvester) በስጦታ ለክልሉ የደን ፤የዱር እንስሳትና፤የአካባቢ ጥበቃ አስተዳደርለማበርከት ግዢውን አጠናቖ ጨርሷል።በተጨማሪም  የእምቦጭ የአረም ማስወገጃ የዚህ አይነት  መሳሪያ እሰከ ሰባት እንደሚያስፈልግ ከሃላፊወ ማወቅ ችለናል።

በመጨረሻም፤ ይህ ጥረታችን እምቦጮ እስኪወገድ ድረስ የሚቻለዉን ሁሉ ለማድረፍ የጎሕ አመራር እና አባላት በሙሉ ከህዝባችን ጎን ምንጊዜም እንደማንለይ እናሳዉቃለን ።  እንዲሁም ጣና ሃይቅ አደጋ ላይ መሁኑ ያሳሰባችሁ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንድትተባበሩ ጥሪያችን በአክብሮት እናስተላልፋለን።

ጎንድር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት