‘የምር ተኳሹን እኛ ስናውቀው
ድንጉጡንባንዳ ማን ደባለቀው::’
ግን ይህ ለምን ትዝ አለኝ? እንጃ!
አቶ ኤፍሬም ሌጄቦ ማናቸው?
አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ሌጄቦን በልጅነቴ አውቃቸዋለሁ:: የአቶ ሌጄቦ ማዴቦ ልጅም ናቸው:: በደርግ ዘመን ‘ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሬቮሉሽናሪ ድርጅት- ማሌሬድ’ የሚባለው አቶ ተስፋዬ በተሰኙ የትግራይ ተወላጅ ተመስርቶ ከወታደራዊው ደርግ ጎን ተሰልፎ ይሰራ የነበረ ድርጅት አባልና በአቢዮት ጥበቃነትና ገራፊነት ከአጎታቸው ልጅ ደጉ ማዴቦ ጋር በአዋሣ ከተማ ይሰሩም ነበር:: በታጠቁትና ‘ፓፓሽ’ የተሰኘ ጠመንጃ ባርቆባቸው የአጎታቸው ልጅ የሆኑትን አቶ መኮንን ባቲሶን እግር ስለመቱ ግለሰቡ እስከሞቱበት ቀን ድረስ አንድ እግራቸው አርተፊሻል እንደነበርም አውቃለሁ::
ከዚህ በፊት አቶ ኤፍሬም በአፄ ሚኒሊክ ላይ እና ‘የመግዛት ተራው የደቡቦች ነው’ ብለው የሰጡት አስተያየት እሣት ጭሮ ነበር:: ዛሬ ደግሞ በአማራ አደረጃጀት ላይ ጦርነት ከፍተዋል።
አቶ ኤፍሬምና የአማራ መደራጀት!
አቶ ኤፍሬም በጁን 10/2018 የቲዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፁህፍ ” አማራ ብቻ ሣይሆን ማንኛውም በጎሣ ላይ መሠረት ያደረገ ብሔረተኝነት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ አንድነት ስጋት ነው:: ትዊት ከተደረገው ውጪ አዎ ለኢትዮጵያ ስጋት የሆነ ለአርበኞች ግንቦት 7ም ስጋት ነው:: እንደ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ፍላጎት ያልሆነ የኛም ፍላጎት አይደለም” በማለት ፅፈዋል::
ይህ የአቶ ኤፍሬም ፁህፍ የግል አመለካከታቸው ወይም የድርጅታቸው ዕይታና አቋም ስለመሆን አላውቅም:: ለአስተያየታቸው መንስኤ ግን ሰሞኑን የተደራጀውና ህጋዊ እውቅናን ከክልሉ ያገኘውን ‘የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ-አብን’ ይፋ መሆኑ ያበሣጫቸው መሆኑን እረዳለሁ::
ይህን ላስታውሳቸው እወዳለሁ::
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጎሣ አደረጃጀት ምክንያት ወያኔያዊው “የጎሣ ፌደራሊዝም” ስርዐትና የሚያራምደው “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮት ነው:: “የጎሣ ፌደራሊዝም” ለብሔራዊ አንድነትና ማንነት እንቅፋት እንደሆነ እረዳለሁ:: ለኢትዮጵያ አንድነትም ስጋት መሆኑን አሣምሬ አውቃለሁ:: ልክ እርስዎ ያገለገሉት የደርግ የሶሻሊዝም ስርዐትና አይዲዮሎጂው ማርክሲዝም-ሌኒንዚም የኢትዮጵያ አንድነት ስጋት ጥንስስ እንደነበረው::
ቅዱስ አምብሮስ “ሮም ስትኖር ሮማውያንን መስለህ ኑር:: ከሮማ ውጭ ባለ ሌላ ቦታ ስትኖርም እዛ የሚኖሩትን መስለህ ኑር” ይላል (“When in Rome, live as the Romans do; when elsewhere, live as they live elsewhere.” (Saint Ambrose)። ይህ ምክር ‘ሰው አካባቢውን ይመስላል’ የሚለውን ያጠናክራል:: እንደ አቶ ኤፍሬም ደምፍላት ኢትዮጵያ ውስጥ በጎሣ ብሔረተኝነት መደራጀት የጀመረው አማራ አይደለም:: ይልቁንስ የዚህ ስርዐትና አደረጃጀት ተጠቂውና በጠላትነት የተፈረጀው አማራ ነው:: ከ80 በላይ ጎሣዎች ባሏት ኢትዮጵያ ቢያንስ የወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት የሌለውም አማራ ነው:: ለአማራውም የኢትዮጵያዊነትን ጥቅም የሚያስረዱት እርስዎ አይደሉም:: ኢትዮጵያዊነት ማንነቱም ነው:: መጠየቅ የሚገባዎት ጥያቄም አማራ በብሔረተኝነት መደራጀት ለምን አስፈለገው ብቻ ነው:: ባጭሩ የህልውናና የማንነት ጥቃት (existential threat) ሣቢያ ኢላማ ተደርጎ በተደጋጋሚ የሚፈፀምበትን የዘር ማፅዳትና ጭፍጨፋ የወለደው ህይወት አድን ምከታ (self-defense) ነው:: አማራ ብሔር ነው:: ብሔርም ህብረ-ብሔራዊ ነው:: ሊጠየቅ የሚገባው ይህ የአደረጃጀቱ ባህርይና የእሣቤው መሠረት የጎሣ ወይስ የሲቪል ብሔረተኝነትን መንገድ ይከተላል ወይ ነው:: እንደሚገባኝ ሊመጥነው የሚችለው ከሊብራል ርዕዮት ጋር የተቆራኘው ‘የሲቪል ብሔረተኛነት’ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ:: አማራው በብሔር ለመደራጀት ያበቃውን ምክንያቶች ከላይ ካሳየሁ ለመደራጀት ያበቃው ነባራዊው እውነታን ከጨበጡ አማራው ለመደራጀት የእርስዎን ፈቃድ መጠየቅ ያለበትም አይመስለኝም:: ላለፉት 27 ዓመታትም ድርጅት አልነበረውም:: ይልቁንም በምን መልኩ ይደራጅ የሚለው ላይ ማተኮሩና አብሮ (ልክ ከነኦነግ፣ ሲዓን ወ.ዘ.ተ.) ለመስራት መሞከርና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማምጣት ብልህነት ነው። ለአደረጃጀቱ ግብዐት ማቅረብ ነው ኢትዮጵያዊነት የምለው።
አቶ ኤፍሬም ይህን ይጠየቁ::
በርስዎ ድርጅት ዙሪያ የተሰባሰቡት ድርጅቶች ሁሉ የጎሣ ድርጅቶች ናቸው:: እንደውም አንዱ በአማራ ስም የተደራጀ ነው:: ኢትዮጵያ ሃገራችን አይደለችም ከሚሉት እንዱ ኦዴግ እዛው ነበር:: ለኢትዮጵያ አንድነት ስጋት የሆኑ ድርጅቶችን ታቅፈው ከኢትዮጵያ በተገነጠለችው ሃገር ተቀምጠው “የአማራው መደራጀት ለኢትዮጵያና ለድርጅቴ ስጋት ነው” እያሉ ሲከሱ እኔ በእርስዎ አፍሬያለሁ:: ሃገሬ ‘መሪ አይውጣልሽ’ ተብላ የተረገመችም መስሎኛል:: አቶ ኤፍሬም ተመሳሳይ ሁኔታዎችን የሚያዩበት የተለያየ የመርህ አተገባበር (Double Standard) አላቸው:: እስከዛሬም ሌሎቹን የጎሣ ድርጅቶች ‘ለምን በጎሣ ትደራጃላችሁ? የኢትዮጵያና የድርጅቴ ስጋት ናችሁ’ ብለው አያውቁም:: ለነዚህ ድርጅት እውቅና እየሰጡ አማራን “አይደራጅ ለኢትዮጵያና ለድርጅቴ ስጋት ነው” ሲሉ ሁለት ተፃራሪ እምነቶችን (Doublethink) እያራመዱም ነው:: ይህም በግብዝነትና ገለልተኛነትን (hypocrisy & neutrality) አብጠው በህሊናዎ የሚጋጩ አስተሳሰቦችን መያዞ ሊያሳየኝ የቻለው የእርስዎን የአስተሳሰብ ደካማነትን ብቻ ሣይሆን ውስንነትም (cognitive dissonance) ነው::
የሚያምርብዎ በዘር ማፅዳትና ችፍጨፋ ስለሆኑትና ለ27 ዓመታት በጠላትነት ተፈርጀው የሚጠቁትን በሃገራቸው ባዕድ ስለሆኑት አማሮች ነው። ሊቃውሙም የሚገባዎት የአማራ ድርጅት በመስረቱ ሣይሆን ይህ የአማራ ድርጅት ወደ ተግባር ሲገባ የሚኖረው ግድፈት ካለ እዛ ላይ ነው። ማንኛውም መደምደሚያ ላይ ከመደረሱ በፊት ጥልቅ ስሌትና ዳሰሳ ማድረጉ ይመረጣክ።
የርስዎ ነገር ሁለት ሃገር በቀል ብሂሎችን አስታወሰኝ። ይህም “ወጡ ሣይወጠወጥ ወስከምባው ቂጢጥ እና ከኛ ወዲያ ስካር ለአሣር ነው” የተሰኙትን።
ይልቁንም ይህን ቅዠትና ወገዛ ከሚያራግቡ ልምዶን በመጠቀም በዚህ የተሳሳተ ግንዛቤዎ ላይ
“ቀይ ሽብር” ያፋፍሙበት:: አይጠቅምዎትም::
