ነጋ ደሌ

ነጋ ደሌ መውጫ መግቢያው የማይታወቅ፣ በዚህ መጣ በዚህ ገባ እየተባለ የመንግስት ጦር የሚፈራው አርበኛ ነበር። በዚህም ምክንያት የጨለማው ጭስ ይሉታል። መውጫ መግቢያው የማይታወቅ! በእስረኛው ዘንድ “ጭሱ” ተብሎ ይጠራል!

ነጋ ከጎንደር ማረሚያ ቤት አምልጦ ያመነው ሰው እንዳስያዘው ይነገራል። በተያዘበት ወቅት ሊገድሉት እንደነበር አጫውቶኛል።

ሆኖም ሌላ ቦታ የነበር የፌደራል ፖሊስ ከያዙት መካከል ለአንዱ ደውሎ “ነጋን ያዛችሁት የሚባለው እውነት ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል። በስልክ! የተደወለለት ፌደራል ፖሊስ አባልም “እንደያዝነው ታውቋልኮ! ማን ተናገረ?” ብሎ ጓደኞቹን ያፋጥጣል። ፌደራል ፖሊሶችም እንደያዝነው ታውቋል ብለው ሳይገድሉት ይቀረሉ።

ነጋን ጎንደር ማረሚያ ቤት “ይጠፋብኛል!” ብሎ ወደማዕከላዊ ይልከዋል። ማዕከላዊ ታስሮ ያመልጣል እያሉ ይሰጉ ነበር፣ ቂሊንጦም እንደዚሁ!

ነጋ ደሌ ያስቸገረው የመንግስት ጦር ከጠበኞቹ ጋር ሆኖ 13 የቤተሰብ አባላቱን በሩምታ ገድሎበታል!

በነጋ ደሌ ክስ መዝገብ የተከሰሱት ክሳቸው ተነስቷል! የእሱም ክስ ከተነሳ በኋላ አቃቤ ሕግ በጓዳ አስፈርዶበታል። ነጋ 7 አመት ተፈርዶበት ዝዋይ ይገኛል!