የኢህአደግ  ማእከላይ ኮሚቴ ስራ አሰፈጻሚ  የሀገራችን ሉኡላዊ መሬት ለሸአብያ አሳልፎ  በመስጠቱ ህዝብ የሀገራችን የባህር በር መብታችን እንዲረጋገጥልን እየጠበቀ  እያለ ፣ይባስ ብሎ  የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ በተለይ ደግሞ ከሸራሮ እስከ ቡሩሬ የተዘረጋ  ከ1000 ከሎ  ሜትር  ጠረፍ የሚገኜው የትግራይ የባድመ ፣ሸራሮ ፣እገላ ፣ጉሎ መከዳ ፣ክልተ ኢሮብ ፣ባዳ ፣ቡሬ ወዘተ አካባቢዎች እና  ህዝቦች መሬታቸው ለሸአብያ በመሰጠቱ  ከባድ ቁጣ አድርሶ እንዳለ ሁሉ ዜጋ ያውቀዋል ። ለዚሁ ፈላጭ ቆራጭ  የኢህአደግ  ስራ አሰፈጻሚ የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት ፓርላማ  ህገመንግስት መብት የጣሰ ግብታዊ ውሳኔ መወሰኑ  ፣ምንም እንእንኳ  የህወሓት   ፣ ኢህአደግ ህዝቡ መብቱ ለማስጠበቅ  አደባባይ ወጥቶ እንዳይ  አንዳይ ወጣ  እንቅፋት እየፈጠሩለት ቢሆን ፣እኖሆ  የተቃውሞ ቁጣ  በኢሮብና በባድመ ተጀምረዋል ። የተቃውሞ ሰልፉ በአዲግራት በ07 /10 2010 ዓ ም  በ 09  /10 /2010 ሰልፊ ሊወጣ ነው ።ሌሎች ዞኖችና ወረዳዎችም የተቃውሞ ቁጣቸው ለማሰማት በዝግጅት ላይ ናቸው ።

በተለይ የአዲግራትና የመቀለ የተቃውሞ ሰልፍ ለመካዬድ አስተባባሪ ኮሚቴዎች  ይዘውት ያሉ የተቃውሞ ሰልፍ ይሳካ ዘንዳ ለአገር ውስጥ የግልና የመንግስት ፣ኤፍኤሞች ሚዲያዎች ፣እንዲሁም የውጭ ሙዲያዎች ለአመሪካ ፣የጀርመን ሬድዮ ጣብያዎች ፣እንዲሁም ማህበራዊ ሚድያዎች ፣ዌቭ ሳይቶች ተለብዥን ፣ሬድዮኖች ፣ሰልፉን በማስታወቅ ግዳጃቹ  ትወጡ ዘንድ ጥሪያችን እነቀርባለን  ይላሉ ።

በሌሎች ክልሎችም  በሰሜን ሀገራችን ያለው ሉኧሏዊ መሬታችንና ህዝባችን  በኢትየኤርትራ ከ70 000 የህዝብ ልጆች የተቀሰፉበት በ100 000 የሚቆጠሩ ልጆቻችን የቀሰሉበት እጅግ ቡዙ የትግራይ አርሶ አደሮች ፣ምልሻዎች ያለቁበት መሬታችና ህዝባችን ፣የለጆቻችን የተቀበሩበት  በካሀዲው የህወሓት ኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተውሰነው በመቃወም ሉአላዊ መሬታችን  እንዳይቆረስ በአደባባይ ወጥታችሁ ተቃውሞችሁ ለመግለጽ  የተለመደው ኢትየጱያዊ ሓላፍነታችሁ ተወጡ  ዘንዳ ህዝብ የድረሱልን ጥሪን ያስተላልፋለ ።

ማሳሰብያ ለኢህአደግ ፈላጭ ቆራጭ መንግስት በተለይ ደግሞ የህወሓት  አማራር ፈላጭ  ቆራጭ  ቡዱን በናንተ የተባላሸ አሰራር፣ ድንቁርና ፣የተደፈርንና  ከሸአብያ ጋር ተሻርካችሁ ለአላውነታችን ያሰደፈራችሁን አልበቃም ብሏችሁ ። አሁንደግሞ የኢትየጱያ ህዝብ ባላመነበት ኢፍትሀዊ ወሳኔ  ለምናደርገው የተቃውሞ ሰልፍ እንቅፋት ለመፍጠርና ብሎም ለማክሸፍ ፣በሰላዮቻችሁ ፣በከድሬዎች ፣በቀበሌ እና ወረዳ አሰተዳዳሪዎች የምታደርጉት ያላቹህ የሰልፉን ማስተጓጎል አቁማችሁ ttከሰልፎኞች  ወድሞች እህቶቻችሁ ጎን ተሰልፋችሁ ሀገራዊ ግዳጃችሁ  ብተወጡ ለራሳችሁ ጥቅም እና ታሪክ ግንባታ ፣ለልጆቻቹህ ኩራት ክብር ይሆናል ።ካልሆነ  በሂደት የመጥፎ ታሪክ ጥቁር ካባ ትከናነቡ አሏችሁ !!!!!!!!!
ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
መቀለ
09 /10  / 2010