ሰሞኑን ኤፍሬም ማንዴቦ የአማራ ብሐየራዊ ንቅናቄ ምስረታን ተንተርሰው መመስረት አልነበረበትም አይነት ቅሬታ ያዘለ መልዕክት በማስተላለፋቸው አንዳንዶች መልስ ሲሰጧቸው ተመልክቻለሁ፡፡ አቶ ኤፍሬም ብሔርን መሠረት ያደረገ ፓርቲን አያስፈልግም ባይ ናቸው፡፡ ለሰው ጆሮ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከልብ ይሄ እምነት እንዳላቸው በጣም እጠራጠራለሁ፡፡ በእኔ እምነት ግንቦት 7 በአጠቃላይ የራሱ ልዩ አጀንዳ ያለው እንጂ ከሕዝብና አገር ፍላጎት ጋር አደለም ባይ ነኝ፡፡ የባሰ ደግሞ ይሄው ግንቦት 7 ዋነኛ ደጋፊ ሊያደርግ የሚሞክረውና እንቀሳቀስበታለሁ የሚለው ማህበረሰብ ዛሬ አማራ በተባለው ማህበረሰብ ሆኖ የውስጥ አሰራሩ ግን ይህን ማሕበረሰብ ጨቋኝ በሚል የመደበ ነው፡፡ እንዲህ ያለ ቁማር የት እንዲሚያደርስ ባይገባኝም ግንቦት 7 አማራውን እንደግብዓት እየተጠቀመ ሌሎችን ለማስደሰት በሚል ይሁን ሌላ ባይገባኝም አማራውን በጨቋኝነት መድቦ ስኬታማ ለመሆን የሚሞክር ድርጅት ይመሰለኛል፡፡

በብሔር የተደራጁ ቡድኖች ሁሉ አማራን በጨቋኝነት መድቦ ስለአማራው ጥላቻን መስበክ ነው ዋና ስልት ያደረጉት፡፡ ይህን 27 ዓመት ስንታዘብ ቆይተናል፡፡ አማራን የማይጠላ ቡድን የነጻነት ቡድን ሊሆን አይችልም የተባለ ነው የሚመስለው፡፡ በብብሔር የተደራጁትስ በእርግጥም ወና የሀሳብ ምንጫቸው ወያኔ ስለሆነ ቀዳሚ መስፈርታቸው አማራን መጥላት ነው፡፡ ይህን የተመለከቱት ፕሮፌሰር አስራት መላው አማራ ድርጅትን አቋቁመው ነበር፡፡ የሆነውን ሁሉ እናውቃለን፡፡

ዛሬ ለተፈጠረው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ግን እኔ እንደሚገባኝ ግንቦት 7 ራሱ ምክነያት ነው፡፡ ምክነያቱም የግንቦት 7 በአማራው መሕበረሰብ በአንድነት ሥም ሊጠቀም አስቦ ነው፡፡ የእሰከአሁኑም የግ7 የአማራ ድርጅትን መቃወም ምክነያት እንጀራዬን ያሳጣኛል ከሚል እንጂ የብሔር ጉዳይ የኢትዮጵያን አንድነት ይጎዳዋል ከሚል አደለም፡፡ ቢያንስ ትግሬና አማራ በመፈራረቅ ሲገዙ ኖረዋል አሁን ተራው የኦሮሞ፣ ሱማሌው አና ሌሎች ደበብ ሕዝቦች ነው የሚል ሀሰባ ከግ7 ባልተሰማ ነበር፡፡ ኦሮሞን የቀላቀለው አሁንም ለንግድ እንዲመቸው እንጂ በገዥነት በተለይ በኢትዮጵያ የቅርብ ታሪክ ኦሮሞ ቀዳሚነቱን ይይዛል፡፡ ግን ወያኔ አንተ ተገዥ እንጂ ገዥ አደለህም ስላለቸው አምኖ ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሌላ ምክነያት የኦሮሞ አክራሪዎች ናቸው፡፡አብዛኛው  የኦሮሞ ፖለቲካ ከሁሉም የከፋ መንገድ የተከተለ በዋነኝነት በአማራ ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ወያኔ እየገደለችው ዛሬም ነጻ እናወጣዋለን የሚሉት ከአማራ አገዛዝ ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር ለማንና አጋሮቹን በአያስነሳ  የኦሮሞ አክራሪዎች ፖለቲካ ሌላውን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ አገሪቱንም ለአደጋ ዳርጎ በዋናነት ግን ራሱን ክፉኛ ሊጥል ተቃረቦ ነበር፡፡ ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ፣ የሚኒሊክ ሰፋሪዎች ከኦሮሚያ ተለቃቅመው መውጣት አለባቸው የሚለው የመጨረሻው አካባቢ የአክራሪዎቹ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ በዚህም ምክነያት እስከዛሬም ከኦሮምያ የአማራው ማህበረሰብ መፈናቀል ወሬ የእለት ከእለት ዜና ሆኗል፡፡ ከዚህ በከፋ ግን ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ የሚለው አክራሪ ቡድን (የቡድን ስብስብ ቢባል ይሻላል) አላማው የሕዝቦችን አብሮ መኖር ማደፍረስ እንጂ ኦሮሞ ራሱ የዚህ አክራሪነት ተጠቂ እንደሆነ ሊያስብ አይፈልግም፡፡ በመሆኑም ዛሬ ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጋ ኦሮሞ በአገሩ ተሰዳጅ ሆነ፡፡ አብዲ ኢሌን ለማውገዝ እነዚህ አክራሪዎች ምን ሞራል እንደሚኖራቸው አላውቅም፡፡  እነለማ በከፍተኛ ትግስትና ብስለት ብዙውን በአክራሪዎች የተበከለውን አእምሮ ወደራሱ እንዲመለስና ማሰብ እንዲችል ቢያደርጉትም አሁንም ግን ቀላል የማይባል አክራሪ ኦሮሞ አንዳለ እናያለን፡፡ አንዳንዶቹም አሁን ጆሮ ስለአጡ መመሳሰልን መርጠው ነው፡፡ በተለይ ተማርኩ የሚለው እጅግ የሚያስፈራ ዘረኝነት የተጠናወተው ነው፡፡ አመክንሐዮ የተማረ ሰው ይሻል ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን አደለም፡፡ ለዛሬው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ተብዬው መመስረት የኦሮሞ አክራሪዎች አንድ ምክነያት ናቸው፡፡ የሚከተለውን ሊንክ አስተውሉ፡፡ ይሄ ነበር አገርንም ሕዝብንም ያዋረደ ዘረኝነት በመጨረሻ በሚሊየን የሚቆጠር ኦሮሞንም በገዛ አገሩ ስደተኛ ያረገው፡፡ ለትውስታ እንጂ ዛሬ ተሰብረዋል፡፡ ለዚህ መስፍን ፈይሳ ሮቢ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡

https://www.facebook.com/MegenagnaTube/videos/1796933567011537/?hc_ref=ARSHrUpIyIkKJ-ioKkSfNh-eVX5HvG3Saqjs4HJU3a3RsAx0oINWrfaEGQPbI4xxJjo

እኔ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስለተባለው ቡድን መመስረት ከማይደግፉት ነኝ፡፡ እሰከዛሬ የደረሰበት ግፍ ቢደርስበትም አማራው በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አማራም እንደኦሮሞ ከኢትዮጵያዊነት እየተራገፈ ይመስላል፡፡ ኦሮሞን ገና በጠዋቱ ነው ኦነግና ወያኔ ከኢትዮጵያዊነት አራግፈው አገር አልባ ያደረጉት፡፡ እነለማ ከ27ዓመት ገኋላ ይሄው ኦሮሞን ወደኢትዮጵያዊነት ለመሰብሰብ መከራ እያዩ ነው፡፡ በተራው ደግሞ አማራ ከኢትዮጵያዊነት በብዛት እየተራገፈ ነው፡፡ በአጠቃላይ የብሔር ፖለቲካ ቡድን መሠረቱ ከሕዝብና አገር ጋር ሳይሆን ሌላውን በጋራ ለመጥላት የሚደረግ ትብብር ቢባል ይሻላል፡፡ ብሔረተኝነት ሌላ ምንም ትርጉም አይሰጠውም ዘረኝነት ነው፡፡ ስለዚህ የዛሬው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለመከላከል ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ አሁን አገራችን ወደ ተሻለ አስተሳሰብ እየወሰዷት ያሉ መሪዎች ተነስተውላታል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አጋጣሚውን ተጠቀመበት እንጂ ለአማራው ጉዳት ምንም ፋይዳ እንደማይኖረው ነው የሚገባኝ፡፡ ጥቂት ጊዜ ችግሮች ቢቀጥሉም በአገራችን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንደሚቀር እንረዳለን፡፡ እስከዛሬም በወሮበሎች ሴራ ነው እንጂ ሕዝቡ ለሕብረቱ ራሱ ዋና ተዋናይ ነው፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ የክልሉ መንግስት ወሰደ የተባለው እርምጃ አንድ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ የሚሉትን አክራሪዎች ፊት ለፊት መዋጋት ግድ ነው፡፡ አብዲ ኢሌም ሱማሌ የሱማሌዎች ነው ብሎ ነው በሕዝብ ላይ ጦርነት የከፈተው፡፡ በእርግጥ የየክልሎች ሕገመንግስት በይፋ ይሄንኑ ይናገራል፡፡ ቢያንስ ለማን የኦሮሚያን ሕገመንግስት በአስቸኳይ እንዲቀይርና ምሳሌ እንዲሆን አመክራለሁ፡፡ ይህ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ሰሞኑን የባድሜ ነገር ሌላው ጉዳይ ነው፡፡ መቀሌ ላይ ስብሰባ አለ ተባለ፡፡ ግን ይህን ስብሰባ ተከትሎ የሚወጡ ውዥንብሮች ይገርማሉ፡፡ ሕወሀት ለሶሰት ተከፈለ የተለመደ ውዥንብር ነው፡፡ ይሄን ቁማር ድሮ ሲጫወተው የነበረው የኢሳቱ ኤርምያስ ለገሰ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከየት እንደመጣ አላውቅም፡፡ ውላችንም እናስተውል፡፡ እውነታው ከመቼውም ጊዜ በላይ ሁሉም አንድ ሆነው ነው እየሰሩ ያሉት ለሰው ይምሰል ነው ልክ እርስ በእርስ የሚቃረኑ የሚመስሉት፡፡ ባድሜ በፊት የትግራይ ነው ሲሉ የነበሩት ዛሬ የኢሮቦች ብቻ ሆኖ ነው ያየንው፡፡ ስለባድሜ ሚስኪኖቹ ኢሮቦች ናቸው የጮሁት፡፡ ሌሎቹ ለማስመሰል እንጂ የአልጀርሱን ስምምነት ይፈልጉታል፡፡ ለመሆኑ መለስ ዜናዊ የአልጀርሱን ስምምነት መፈረሙ ሳያንስ በነጋሪት ጋዜጣ ማፅደቅ፣ ባድሜ ወደኤርትራ እንድትሆን ካርታ ሰርቶ መሥጠት ምን ሊሉን ይሆን፡፡ ለነገሩ የባድሜ ጉዳይ እንዲህ ቀላል አደለም፡፡ እንደገባኝ አብይ ሁሉንም አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው መሠለኝ፡፡ ኤርትራም በመለስ ጊዜ አንጂ አሁን ላይ ባድሜን ለመፈለጓ እንጃ፡፡ ጉዳዩን የያዙት ዛሬ የወያኔ ወሮበሎች ሳይሆኑ የአገርና ሕዝብ ልጆች ናቸው፡፡ ወያኔዎቹና አጋሮቻቸው እረፍት ያሳጣቸው የባድሜ ወደ ኤርትራ መሄድ እንደመለስ ጊዜ ቀላል አለመሆኑ ነው፡፡ ለመሆኑ ግን ሻቢያ ምን አለች?  ዛሬ ድራማ መስራት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለወያኔና ሻቢያ ድራማ በመቶ ሺዎች ከሁለቱም ወገን ያለቀው ወገናችን ይቆጫል፡፡ በተለይ የእኛ ልጆች፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያን እየገነባን ነው፡፡ እነ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መመስረት ለእነ ግንቦት 7 ቦታቸውን ስለነጠቃቸው እንጂ የአንድነት ጉዳይ አደለም፡፡ ንቅናቄውም አይቆይም፡፡ አብይ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የወያኔን የዘር ክልልሎች ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ አገራትንም ድንበር ንዶት አፍሪካውያን ልዩ ሕብርት እንዲፈጥሩ ለማድረግ ነው አያያዙ፡፡ ሁሉም አብይን ተስፋ አድርገዋል፡፡ አዎ እኛ ኢትዮጵያውያን መሪዎች ነን፡፡

ኢትዮጵያውያን ከዘር ቀለበት እራሳችሁን አላቁ፡፡ የዘር ማንነታችንን አስመልክቶ በአንድ ወቅት እቅጩን የሚናገረውን የሳይንስ ጥናት ውጤት አሳይቻችኋሁ፡፡ አብይ በአንድ ወቅት ስለሰው ጄኔቲክስ የተናገረውን ብዙዎች ሲሳሳቱበት ተመልክቻለሁ፡፡ ጉዳዩ እንደዚያ አደለም፡፡ የሰው ዘረመል 99 በመቶ ቢመሳሰልም በወሳኝ ዘረመል ቀመር ብዙ ይለያያል፡፡ አንኳን  ጥቁርና ነጭ እናትና ልጅም ይለያያሉ፡፡ ለዛም ነው ዛሬ ዲኤን ኤ ምርመራ ወላጅን ወይም ቤተሰብን ዝምድና ለማረጋገጥ የሚውለው፡፡ ስለ99በመቶው ዛሬ አልነግራችሁም፡፡ ያም ሆኖ ግን በአለፈው የአጋራኋችሁ ጥናት ውጤት በአስገራሚ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ሕዝቦች ሲለዩ ውስጥ ግን አንዱ ከአንዱ በምንም አይለይም፡፡ ይህም ሆኖ ቁም ነገር አደለም፡፡ እኛ የተለየን ነንና ሌሎችን በዘረኘነት መመልከት የበታችነት ነው፡፡ የሚገርመው የዓለም የጄኔቲክ ክምችት ከሌላው አገር በተለየ እኛው ውስጥ መሆኑ ሳይንቲስቶቹንም አስደንቋቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክነያት ነው ያሉት አገሪቱ በዘመናት ብዙ ከሌላ የመጡ ሕዝቦችን ማስተናገዷና ዛሬ ተዋህደው መኖራቸውን ነው፡፡

ለማንኛውም በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምክነያታዊ (ሎጂካል) አስተሳሰብ ይኑረን፡፡ ብዙ ምሁር ዛሬ ዘረኝነት ስለበከለው አመክንዮ(ሎጂክ) መክናበታለች፡፡  የፈጠጠውን እውነት ክዶ በሐሴት ሴራ ተመርዟል፡፡

ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ታላቅነትን ይስጥ! አሜን