~በዛሬው የትህነግ/ህወሓት መግለጫ እንደተመለከተው ትህነግ ብስጭት ላይ ነው። የኢህአዴግ ዋነኛው አካል ሆኖ የወሰነውን ውሳኔ ሽሮ መግለጫ ሰጥቷል!

~ይህ ብስጭት በዋነኝነት የሚወልደው ሌላ ነገር ይኖራል! በአሁኑ ወቅት ሀገር ላይ በርካታ ቀውስ ሊፈጥሩ የሚችሉ የትህነግ ሰዎች ስራ ፈትተዋል!

#የደህንነት ሚኒስትር የነበረው ጌታቸው አሰፋ
#የደሕንት መስርያ ቤቱ ምክትል የነበረው ወልደስላሴ
#insa ዳይሬክተር የነበረው ጀኔራል ተክለ ብርሃን
#የሜቴኩ ክንፈ ዳኘው
#ኢታማጁር ሹም የነበረው ሳሞራ የኑስና በርካቶች ስልጣን የማስጠበቁ ስራቸውን ፈትተዋል። እነዚህ ሰዎች ከስራ ውጭ ሲሆኑ ለማበጣበጡ ደግሞ ሙሉ ጊዜ አግኝተዋል።

~ዶክተር አብይ እነዚህን ሰዎች ደፍሮ ሲያነሳ በራሱ ኃይል ብቻ ነው ለማለት አያስደፍርም። “ህወሐት ያረጀ ፈረስ ነው፣የፈለከውን እርምጃ ውሰድ ዓለም ከአንተ ጎን ነው” እያሉ ሲፅፉ የሰነበቱት የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ማስታወስ በቂ ነው

~ትህነግ/ህወሓት ስልጣን እንደወጣ ሰሞን ኢኮኖሚውን ነፃ እንዲያደርግ ያስገደዱት ሰዎች፣ ዛሬም ነፃ ካልሆነ ብድርም እርዳታም አናቀምስም ሳይሉ አልቀሩም። የአልጀርሱ ስምምነት ላይ ዋናዋ ሀገር አሜሪካ ነበረች። እንዲፈፀም የምትገልገው የመጀመርያ ሀገርም እንደዚሁ።

~ትህነግ በምስራቅ አፍሪካ ሰላም ጠባቂ ነኝ የሚለውን ተረት ተረት ለአሜሪካ ሲያወራ ኖሯል። አሁንም የሚያምኑት ይመስለዋል! ለሕዝብም ለአሜሪካም “እኔ ከሌለሁ አለቀላችሁ” ማለት ይፈልጋል! ትህነግ ያመናት አሜሪካ የምትባል ፈረስ ግን ክዳዋለች!

~ከምንም በላይ ትህነግ ከአህያይቱ የባሰ አመለካከት እንዳለው የተወቀ ነው። እሱ እያለም ቢሆን ሰርዶው ለእሱ ብቻ እንዲበቅል የሚፈልግ ከአህያይቱ የባሰ አመለካከት ያጠቃዋል። በቁሜ ሞትኩ እያለ ያለው ትህነግ/ህወሓት በየ ቦታው ትርምስ መፍጠር ብስጭቱን የሚያበርድለት ይመስለዋል! እነ አብይ የምር ለውጥ ቢፈልጉ በቁሙ ሳይሆን ግብአተ መሬቱን መፈፀም ነበረባቸው። ትህነግ እባብ ነው! ለመደ ተብሎ በኪስ የማይያዝ!

~አብይን የአልጀርሱን ስምምነት ላይም ሆነ ተቋማቱ እንዲሸጡ ሲያባጅኑት ትህነግንም ለማባከን ቃል ሳይገቡ አልቀሩም። ደግሞም እነ ጌታቸውንና ሳሞራን ማንሳት ቀላል አይደለም። መቀሌ ላይ አለን የሚሉትን ግን በደንብ ያባከኑለት አይመስልም። እንግዲህ የአብይ እዳው እዚህ ላይ ነው! እባቡን ከኪሱ አውጥተው ይወረውሩለታል? አይወረውሩለትም? አብይ ማንም ተጠቅሞ ከኪሱ አውጥቶ ካልጣለ የመጀመርያው ተነዳፊ እሱ ራሱ ነው! አንደኛ ተከሳሽ ዶክተር አብይ አህመድ!