ሕወሓት የሚባለው የቅሚያና ግድያ ድርጅት ያወጣውን መግለጫ አነበብሁት። መግለጫው አንዳች ኢትዮጵያን የሚነካ ነገር የለውም። ሕወሓት እንደ ድርጅት ከምስረታው ጀምሮ ከበርካታ ግራ አጋቢ ነገሮች ጋር የተወሳሰበ ነውረኛ ድርጅት ነው። ነው ጌጡ የሆነው ይህ ድርጅት ያለ አንዳች ተቃውሞ አዲስ አበባ ላይ አብሮ የወሰነውን «የኢሕአዴግ» ውሳኔ መቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤው ተቃውሞታል። ከሽፍትነት ወደ «መንግሥትነት» የተለወጠው ይህ የማፍያ ቡድን በዛሬ እለት ባለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል አኳኋን ከቀናት በፊት ያወጣውን የራሱን ድርጅታዊ ውሳኔ ተቃውሞ መግለጫ ያወጣ ብቸኛው ድርጅት ለመሆን በቅቷል።
አንድ እውነት አለ። የትኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄድ ለውጥ [ጥገናዊም ሆነ መሰረታዊ] ከሚገባው በላይ ኢትዮጵያን የተቆጣጠረውና የመከላከያውን፣ ደህንነቱን፣ ኢኮኖሚውን፣ ውጭ ጉዳዩንና ባጠቃላይ የአገራችንን ሥልጣን ሁሉ የሰበሰበውን ወያኔን የሚጎዳ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ለማድረግ የሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ የወያኔን ቅጥ ያጣ ዘረፋና ቅሚያ፣ ግድያና ስቃይ ስለሚቀንስ የትግራይ ፋሽስቶች ለግል ጥቅማቸው የመሰረቱት የቅሚያና የስርቆት ድርጅት፤ ኢትዮጵያን ረግጠውና አደንቁረው ሊገዙበት፤ ሐብቷን ሊበዘብዙበት፤ እንቦቀቅላ ልጆቿን ሊረሽኑበት በወንጀል ያቋቋሙት የሌብነት፣የግድያና የሙስና ማሕበር የሆነው ሕወሓት ቢከፋ የሚያስደንቅ አይደለም።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ካቢኔ አመራረጥ አልተመቸኝም የሚለው የወያኔ መግለጫም ከማስተዛዘቡ በላይ ድርጅቱ ምን ያህል ግብዝና ነውር ጌጡ የሆነ የእሳ ቢሶች ማሕበር መሆኑን እስካሁን ላላወቁት ያሳወቀበት ይመስለኛል።
ሌላው ገራሚው እነ አባይ ፀሐዬና ስብሓት ነጋ በክብር እንዲሸኙላቸው የጠየቁት ነውረኛነታቸው ነው። አባይ ፀሐዬ የሩቁን እንኳ ብንተወው ከድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ 77 ቢሊዮን ብር የዘረፈ ገፋፊ ነው። ስብሓት ነጋም የሩቁን ብንተወው በቅርቡ በልጁ ስም ግዙፉን የጎተራ አደባባይ ለአምስት አመት ኮንትራት በ600 ሺህ ብር እንደወሰደው ፎርቹን ጋዜጣ ይፋ አድርጎታል። የ«አክሊል ክሬቲቭ ኤጄንሲ» ባለቤት የሆነው ተከስተ ስብሀት ነጋ፤ በአካባቢው ያለን 4000 ስኩዌር ኪሎ ሜትርና በቢሊዮኖች የሚገመት መሬት እንደ ስጦታ ነው የወሰደው።
ሕወሓት በክብር እንዲሰናበቱለት የሚጠይቃቸው እነዚህ በኢትዮጵያ ኪሳራ የአገር ካዝና አራቁተው የኢትዮጵያን ድሃ አጥንት የጋጡ ጨካኝ ወሮበሎችን ነው። ለነገሩ በቤተ ወያኔ አባይና ስብሃት ኢትዮጵያን ቢዘርፉ ገንዘቡ በመዋለ ንዋይ ስም ወደ ትግራይ እንደሚተላለፍ ስለሚቆጠር ኢትዮጵያን የሚጋጥጡ የሕወሓት ዘራፊዎች ለትግራይ እንደ ባለውለታ ቢቆጠሩ አይፈረድባቸውም፤ የታገሉትና እየታገሉ ያሉት ኢትዮጵያን ገፈው ትግራይን ለማልበስና የተስፋይቱን ምድር ለመመስረት ነውና።


