ከኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ከሚቴ ስለ የአልጀርስ ሰምምነት እና የወሰን ኮሚሽን ውሳኔ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢህአደጉ ስብሰባ ውሳኔው ተቀብሎ ሲያበቃ እንደገና ውሳኔው ሳይውል ሳያድር በመገልበጥ የህዝብ ተቃውሞ ለስልጠኑ አስጊ ሆኖበት ስላአገኜው ውሳኔው በመሰረተ ሀሳቡ የኢህአደግ መርህ የተከተለ ሆኖ ነገር ግን ወደህዝብ ወርደን አሳማኝ ስራ ባለመስራታችን ትክክል ያልሆነ ውሳኔ ወስነናል ብለውናል ።

ዋዋ እነዚህ ሰዎች አስተሳሰባቸው ምን ያህል ወርዷል ? እነዚህ አካላት የኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ሰብሰባና ውሳኔ ያለአንዳች ማቅማማት እንደውሰኑ ትግራይ መጥተው በሚዲያ ማብራርያ ሰጥተዋል ታድያ ለምን ተገላበጡ?

1ኛ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ሰፊ ቃለመጠየቅ ተጠይቆ ህዝባችን 18 አመት ሙሉ ህዝባችን ምለሻዎች በጦርነት ተጠምዷል የልማት ተቋዳሽም ስላልሆነ የህዝብ ችግር ወደ ኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ አቅርበን ማስወሰናችን ትክክል ነው በመሆኑም ተጠያቂዎቸ እኛ ብሎ መግለጫ ከሰጠ በኃል የህዝብ የተቃውሞ ቁጣ ተሰማ ። አደባባይም ወጥቷል ።

2 አቶ ጌታቸው ከዶክቶር ደበረጽዮን ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብለት መልስ ሲሰጥ ፣ እኛ ይህ ውሳኔ የኛ አይደለም ከ15 አመት በፊት ተወስኖ ያደረ ስለሆነ የኛ ስህተት አይደለም ብሎ ለማምለጥ ለመገላበጥ ሞክሮዋል ። የዛሬ እንዳላመኑበት አዲስ ነገር አድርገው መቅረብ ማጭበርበር እና ክህደት አይሆንም ? እናንተ ህዝብና ፓርቲያችሁ ከማጭበርበር ላዳናገራቹህት ህዝብ እንደገና ማጭበርበር አይሆንም ?
አሁንነም የሀወሓት ስራ አስፈጻሚ ከሚቴ ተወላዋላይ(ተገላባጭ ) የህወሓት እና የህዝብ አቋም
ልዩነት እንዳለው ያመለክታል ?

3ኛ በእኔ እምነት አሁንም እኮ የህወሓት መሪዎች ውሳኔ መፍትሄ አላመጣም የህዝብ መሰረታዊ ፍላጎትና አላማ አያሉት ያሉ ወሰናችን እኛ ኢትየጱያውያን ነን እኛ ስንኖር ኢትዮጱያውያን ነን ። ስንሞትም እዚሁ ኢትየጱያ ሆነን ነው በመሆኑ መቃብራችን እዚሁ ኢትዮጱያ ነን እሉ ስለዚህ የህወሓት በውሳኔው ሲገላበጥ ሲገላበጥ ፣ ህዝብ ደግሞ እጠየቀው ያለው ከትግራይ መረብ ተከትሎ ተሰነይ ወደ ውስጥ ያደረገ እስከ ከሰላ ነው በአፋር ደግሞ ከጅቡቲ እስከ ማርሳ ፋጥሟ የባህር ጠረፍ ሀብታችን ነው ይላል ።

እንዳው ሰራዊታችን በጦርኖቱ ጊዜ አብዛኛው የኤርትራ ስትራተጅክ ቦታዎች ይዘው አስመራና ቀይባህር ሊቆጣጠሩ ሲገሰግሱ መለስ ዘይናዊ ተመለሱ ብሎ በመመለሱ ለችግሩ አዋሳስቦታል እንጅ ነገሩ በዛን ጊዜ አልቆለት ነበር ።
የሚቀጥለው 8 ወሳኔ መልሱ ይቀጥላል ፣

ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
መቀለ