የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም መግለጫ ሰቷል። በጣም ደግ! መቃወም መብት ስለሆነ ይችላሉ። እኛም ዕድሉን እንጠቀምበታለን። ደግሞም ታሪክ ሰርቷል። ለ 27 ዓመታት ያልተሞከረዉን ለመጀመሪያ ጊዜ አደረጉት። አንድ አባል ድርጅት የኢህአዴግን የEC ዉሳኔ ሲቃወም ይህ የመጀመሪያዉ ነዉ።ግን ዉሳኔዉ ሲሰጥ በቦታዉ የነበሩ መሰለኝ። ህወሀት ወደ አጋር ፓርቲነት መቀየሩን ከመግለጫዉ አላነበብኩም። ተሳስቼ ከሆነ እታረማለሁ።
ተቃዉሞዉ ብዙ ጉዳዮችን ያነሳል። በጣም ደስ ያለኝ ለቀድሞ ታገዮች እዉቅና መጠየቁ ነዉ። እነ አባይ ፀሐዬን “ባለራዕዮች!” በሏቸዉ እያለን ነዉ። እንደለመደብን ትዕዛዙን በመቀበል “በሙስና ለሙስና የኖሩ ምርጥ የሙስና አመራሮች” ብለናቸዋል።

በሌላ በኩል ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊ መስመሩን እንደሳተ መግለጫዉ ይናገራል። እዝህ ላይ ቢያስቡበት ጥሩ ነዉ። እነሱ ራሳቸዉ ኢህአዴግን የመቃወም መብት ያገኙት አሁን አይደለም እንዴ? ከዝህ በላይ ዴሞክራሲ ከየት ይምጣ? ኢህአዴግ ሆኖ ኢህአዴግን መቃወም ተአምር አለነበረም? የፓርላማ አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሲቃወሙ ጉድ አልተባለም? መስመር ተበላሸ ያለዉ ማን ነበር? ክብር ለዶር አብይ እያለችሁ ተቃወሙ!