የስዩም መስፍን/መለስ ዜናዊ እና የህወሓታውያኑ ክህደት (መንግስቱ ሙሴ)
ማሕሉን ዳር የማድረግ የወያኔ እስትራቴጅክ ሴራ (ጎንደርን ለሱዳን/ትግራይን ለኢሳያስ)
የትግራይ ትግሪኝ አዲስ ሀገር የመመስረቱ የመጨረሻ
====================================
የህወሓትን ዘመነ ስልጣን አየን። ገና ከጅምሩ በሸፍጠት እና ጥላቻ የተወለደችው ህወሓት በለስ ቀንቷት እና አለማቀፍ እና የጎረቤት ሀገራትን ትብብር ተችራ ስልጣን ለመቆናጠጥ እና በሀገሪቱ አራጊ እና ፈጣሪ ለመሆን በቃች።፡ከ 1991 ጀምሮ አንድ በጎ ነገር ሰራች ብሎ ለመናገር በሚቸግር ህዝብን እና ሀገርን በመግደል ግዛተ ዘመኗን ጨርሳለች። የኢትዮጵያን ባህር ኃይል አፍርሳ የባሕር በራችንን ያለአንድም ቅድመሁኔታ ሰጥታለች። አሰብ ዛሬ ዳዋ ለብሷል። ግራቀኙ ገንጣይ እና አስገንጣዮች ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚጠቀም ዳዋ ይልበስ፣ ወና ሆኖ የአይጥ እና ፈልፈላ ሀገር ይሁን በሚል እሳቤ ነው መቶ ሚሊዮን ሕዝብን የጥቃቅን ጎረቤት ሀገራት የትርፍ ሲሳይ ያደረጉት። የወልደአብ ልጆች፣ የሞሶሎኒ ድቃዮች፣ የሹምባሹ እድሪስ አወቴ የመንፈስ ተከታዮች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻ ገደብ የለሽነቱን በ27 አመታት የግዛት ዘመናቸው አየነው። የመጨረሻው መጨረሻ ግን ያው የፈረደበት በድንበር የሚኖረው የሳሆ አዲ ኢሮብ ጾረና፣ ዛል አንበሳ፣ ባድሜ ነዋሪ ነው። በአዲ ኢሮብ ሕዝብ ላይ ህወሓት ሁልግዜም ቂም እንደቋጠረች ነው። የነ ተስፋየ ደበሳይ ሀገር። የነገብረ እግዚያብሔር (ጋይም) ትውልድ ህወሓት ስትመሰረትም ኢሕአፓን እንጅ አናውቅሽም ብሎ የወጋት እና ለአረንዷዴው ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ከፍተኛ ክብር ያለው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ዜጋ ሰልፍ ወጧል። ኤርትራ እንኳን በቅኝ ግዛት በነበረችበት ዘመን ከቀሪው ወገኑ ያልተለየውን ሕዝብ ነው ወያኔ የእኛ አይደላችሁም ይሂዱ ብላ አልጀርስ ላይ የፈረመች።
የአልጀርስ ስምምነት የሚባለው የክህደት ስራ እና ተግባር የህወሓት ማህከላዊ ኮሚቴ ሆን ብሎ የፈጸመው ወንጀል መሆኑ ግልጽ ነው። በእርግጥ የባድሜ ጦርነት በሚል ከበሮ ሲደለቅ፣ ዜጎችን የአይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራለን በሚል ፋሽሽስታዊ ፈሊጥ ሲያፈናቅሉ በግራና ቀኙ ማለት ነው። ህወሓት የሰራውን ሻእብያም እንደተገበረው ስለምናውቅ የካርታ ብወዛው በሕዝብ እና ሀገር ላይ ያደረጉት ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ክተት ብለው ጦርነት ሲገቡ (እኛ ብንቃወመውም፤ እንደክህደት የቆጠሩ ከሀዲወች እንደነበሩ ሳልረሳ) እነዚህን ሁለት አጥፊ ድርጅቶች ማመን አይገባም ብንልም ባለመስማት ያነን ሕዝብ አጫራሽ እና ሁለት ወንድማማች/እህታም ሕዝቦችን ማግደው አጨራርሰዋል።
አገር መስጠት ክህደት ነው! ይሰመርበት። ገዥ ሄዶ ሌላ ገዥ ይመጣል። ሀገር እና ሕዝብ ግን እንደተጓዥ ወንዝ ቀጣይ ነው። ይህን መሰረታዊ እና ዳይሌክቲካዊ ጅረት ለመቁረጥ ህወሐት በዘመነ ግዛቷ ብዙ ውሳኔወችን አሳልፋለች። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቻይ፣ ታጋሽ እና ጨዋ በይበልጥም ማንነቱን አዋቂ በመሆኑ እንጅ እንደሰሜን ገንጣይ እና አስገንጣዮች ስራ እና ተግባር ቢሆን ኢትዮጵያን ዮጎዝላቪያ የሚያደርግ በእጥፍ ድርብ ተሰርቶ ከሽፏል። ለዚህ የህወሓት አንፋሽ እና አጎንባሽ ደግሞ ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የመጡ ባንዶች እና በይበልጥም የትግራይ ምሁራን ሆነው ስናይ በታላቅ ሀዘን ነበር።
የፋሽስቷ ቡድን የደህንነት መስሪያቤት ማህል ከተሞች የማፈኛ እና የማሰቃያ ድብቅ ህንጻወች መስርቶ አፍ አውጥተው የተነፈሱትን፣ ለሀገር የጮሁትን፣ የጻፉትን ሁሉ እየሰበሰቡ ዘግናኝ በሆነ ወንጀል ተግባር ተሰማርተው መኖራቸውን ከየማፈኛ እስርቤቶች የተፈቱት እየነገሩን ነው። ከእስር የሚወጣው ዜጋ ቁጥር አሁንም እንደቀጠለ ነው። በዚህ ዘመን እና ግዜ የውጭ ጠላት የማይሰራውን የሰውልጅን ጥፍር መንቀል፣ ብልትን መስለብ፣ ሴት ዜጎችን በጠላት የማይሰራ ክብረነክ እና በጣም ዘግናኝ የሆኑ ወንጀሎችን በመንግስትነት የተሰየመችው ህወሓት ስትፈጽም በለው ባይ ምሁራን እንደነበሩም አሳፋሪ ታሪክ ነበር።
ዛሬ ህወሓት በቀሪው ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሰራችው ታሪካዊ ወንጀል በትግል ተፈንግሎ በመውደቅ ላይ ባለበት የ12ኛዋ ሰአት ልጆቻችን፣ የአይናችን ብሌን፣ ብሎ የተከተላትን የትግራይ ምሁራን ብቻ አይደለም ታላቁን ክህደት በአደባባይ ዘርግፋዋለች። ወንጀል እና ሚስጥር ተደብቆ የሚቀር አይደለም እና የህወሓት ገመና ዛሬ በሀገር ክህደቱ ታሪካዊ እና አሳፋሪ ጉዞን እንድናይ ሆነናል። በሰሜን ወሎ፣ በወልቃይት፣ በጸገዴ፤ በጸለምት፤ በምእራብ ሸዋ፣ በሀረር፣ በወለጋ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ፍጅት አይቶ እንዳላየ ከልማታዊ መንግስታችን ጋር ወደፊት ያሉት ዛሬ የእነርሱ ጉድ አደባባይ ሲሰጣ እንደትናንቱ በዝምታ የሚያልፉት እየሆነ አይደለም። የትግራይን ሕዝብ በመያዦ ሰጥተው ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገለል ያደረጉት የህወሓት አፋሽ አጎንባሽ ምሁራን የት ሊገቡ ይሆን?
ሀውዜንን የፈጠረች ህወሓት ትግራይን አትሰጥም የሚል እምነት ኖሮን አያውቅም። የህወሓት አመራር አባላት ከኢሳያስ እና ስብሀት ኤፍሬም በላይ ስለኤርትራ የሚጨነቁ እና የሚቸገሩ ናቸው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
