ህወሓት በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለውን “የአልጀርሱ ስምምነትንና የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብለናል” የሚለውን የኢህአዴጉ ውሳኔ ተቀብሏል።
የህወሓት ባለስልጣናት ከፌደራል ስልጣን መባረራቸው ግን ተቃውሟል።
በዚሁ መሠረት ህወሓት የህዝብን ጉዳይ ችላ ብሎ የስልጣን ጉዳይ ግን አንገብግቦታል።

ከህወሓት የሚጠበቅ ነው፤ ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ስልጣን የሚኖር ድርጅት ነውና።

ዓረና ፓርቲ “… ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ …” የሚለውን የኢህአዴግ ውሳኔ አይቀበልም ብቻ ሳይሆን አጥብቆ ይቃወማል። ለዚህም ነው ዓረና የትግራይ ህዝብ ተቃውሞውን በሰልፍ እንዲገልፅ ጥሪ ያቀረበው።

የትግራይ ህዳሴ በተጋሩ አንድነትና ትግል ይረጋገጣል።

It is so!!!