Tigrayoline የሚባለው የህወሓቶች ድህረገፅ የካቲት 07/2010 ዓ.ም ላይ ኢትዮጱያ መንግስት የዜጎቹን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር ለቀጣይ ሦስት አመታት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅ እንዳለበት የሚል ፅሁፍ አውጥቶ ስመለከት በዕለቱ የለየለት እብደት መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም ከየካቲት 05 – 7/2010 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ እነ በቀለ ግርባ እና እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት የፖለቲካ እስረኞች በመፈታታቸው ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እየገለፀ ነበር። ይህ ድህረ-ገፅ ግን በተጠቀሰው ዕለት በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ መከሰቱን በመጥቀስ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ እንዳለበት ሲወተውት ነበር። ከሦስት ቀን በኋላ የካቲት 09/2010 ዓ.ም የአስቸኳይ ግዜ ሲታወጅ ከድረገፁ ፀኃፊዎች ይልቅ የራሴን አዕምሮ ጤንነት ተጠራጠርኩ። ፍፁም እብደት የመሰለኝ ነገር እውነት ሆኖ ሳገኘው ለምን ራሴን አልጠራጠር?
ከሦስት ወር በኋላ ሰሞኑን Tigrayoline ተመሳሳይ መረጃ ይዞ መጥቷል። ከአስር ቀናት በፊት ይህ ድረገፅ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ አመፅና አለመረጋጋት ከተቀሰቀሰ እንደ ከዚህ ቀደሙ ኦሮሚያና አማራ ውስጥ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀርና መላ ሀገሪቱ በሁከትና ብጥብጥ ልትታመስ እንደምትችል ይገልፃል። በዚህ ምክንያት የምናውቃት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ልትቀየር እንደምትችል ይጠቁማል። ለዚህ ዋናው ምክንያት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሥራና ተግባር አፍራሽና ሀገሪቱ ውስጥ ቅሬታ ስለፈጠረ እንደሆነ ድህረገፁ ይጠቅሳል።
በእርግጥ የካቲት ላይ የተሳሳትነው እኛ እንጂ Tigrayoline ትክክል ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ እኛ እስረኞች ስለተፈቱ ደስታና ፈንጠዚያ ላይ ሳለን የድረገፁ ፀኃፊዎች በኢሉአባቦራ ዞን፥ በኖ በደሌ አከባቢ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ምን እየተሰራ እንደሆነ ያውቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል፥ ጋምቤላና የተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በግፍ ተፈናቅለዋል፥ ተገድለዋል። አብዛኞቻችን የካቲት 07/2010 ዓ.ም ስለተፈፀመው ግጭትና ማፈናቀል በትክክል ያወቅነው ከሦስት ወር በኋላ በባህር ዳር እና ወልዲያ አከባቢ አሉ ሲባል ነው። እነዚህን ተፈናቃዮችን በአካልና በስልክ በማነጋገር ያረጋገጥነው ነገር በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ግድያና መፈናቀል ሆን ተብሎ በህወሓት የደህንነት ሰዎችና ተላላኪዎቻቸው አማካኝነት የተፈፀመ መሆኑን ነው።
ባለፈው የሰራነው ስህተት Tigrayoline ከማንም ቀድሞ ሁከትና ብጥብጥ እንደተከሰተና የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲታወጅ ሲወተውት እንደ እብደት ወስደን ንቀን መተዋችን ነው። ምክንያቱም ይህ ድህረ ገፅ መረጃውን የሚያገኘው ከተጎጂዎች ሳይሆን ከገዳዮቹ አንደበት ነው። ስለዚህ በድህረ-ገፁ የወጣው መረጃ ከሞላ ጎደል የህወሓት ዕቅድና ዝርዝር መርሃ-ግብር ነው። በተመሳሳይ ከአስር ቀናት በፊት Tigrayoline ከአማራና ኦሮሚያ ውጪ ባሉት ክልሎች ሁከትና ብጥብጥ እንደሚነሳ በግልፅ ነግሮናል። ይኸው ሰሞኑን በዕቅዱ መሰረት ደቡብ ክልል በሁከትና ብጥብጥ እየታመሰ ይገኛል። ይህን መሰረት በማድረግ ተግባራዊ ሊደረግ የታቀደው መርሃ-ግብር ደግሞ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ነው። እንደተለመደው ሁከትና ብጥብጡ ሆነ የአዋጁ ባለቤት ደግሞ ህወሓት ነው። በአጠቃላይ የTigrayoline ዘገባ የሚያስረዳው ህወሓት ከአስር ቀን በፊት በደቡብ ክልል ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት አቅዶ የተግባር እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው።
************
የ Tigrayoline ሙሉ ዘገባ ከዚህ በታች ያንብቡ
Lift the state of emergency in Ethiopia, and lose the country
Tigrai Online, June 2, 2018

Lifting the state of emergency in Ethiopia will lead to disintegrating the country
The Ethiopian government is about to lift the emergency which was declared four months ago two months earlier than it was planned to be lifted. Prime Minister Abiy Ahmed was handed a calm country mainly because of the state of Emergency not because of some miracle that came with the swapping of two men from the same party.
The new Ethiopian prime minister is doing too much and too fast probably he is eager to please everyone in all sides. Prime Minister Abiy’s actions for the first weeks after he took office must have been exiting for many Ethiopians, however as time goes on the euphoria that swept across Ethiopia is fading faster than morning fog.
Unless the Ethiopian prime minister has guarantees from Minnesota and Asmara lifting the state of emergency will be his own undoing. If the unrest restarts again it would not be confined to Amhara and Oromos regions, it will engulf the entire country because this time every region and every ethnic is boiling with anger. Unleashing public unrest will lead to the demise of Ethiopia as we know it.
The forces behind the three year public unrest in Amhara and Oromia regional states were not and are not interested on democracy or freedom of people their primary goal is to dismantle the Ethiopian federal system. From what we have seen so far the new Ethiopian Prime Minister’s actions are counterproductive and creating more discontent in the country.
There are signs signaling involvement of external forces twisting the young prime ministers’ hand for their own national interest. A covert, but highly concerted international effort has been going on for a while to undermine the EPRDF government and its aim is to dislodge China from the Horn of Africa especially from Ethiopia. The Chinese are fully aware of the current changes taking place in Ethiopia and they might be taking actions to protect themselves. The Financial Times said the following in its article today, “For much of the last decade Ethiopia has been a leading investment destination in sub-Saharan Africa, particularly for China. But Beijing’s waning enthusiasm for the region’s fastest-growing economy reflects the challenges facing Abiy Ahmed, the prime minister, as he juggles demands from a public hungry for both democracy and development and myriad vested interests”, emphasis from TOL
Source: http://www.tigraionline.com/articles/keep-state-emergency.html


