
የመቀለ ህዝብ አገር ሲሸጥ እንዴት ትተኛለህ የህወሓት አማራር አገር ሽጦ ሲያበቃ እንደገና የህዝብ ቁጣ ፈርቶ መገላበጡ የተለመደው ባህሪውና ተፈጥረው መሆኑ አውቀህ ሮማናት አደባባይ ከተት !!
የተከበርከው አገር ወዳድ የመቀለና አከባቢ ህዝብ አንተ በማታውቀው ባላመንክበት የሀገርህን ልኡላዊ መሬትህ የህወሓት ከዳተኛ መሪዎችህ ነን ተብየዎች አንደ ስጋ ቅርጫ ቆርሰው ሊሸጡ እየተስማሙብህ (ፈርደወበህ ) ስላሉ በሰላም ሰልፍ ወጥተህ ተቃውምህ እንዳታሰማ እንቅፋት ሊፈጥሩብህ ስለሚችሉ የሚፈጥሩብህ እንቅፋት በትእግስት ፣በጭዋነት ተሻግረህ በሮማናት አደባባይ ተሰልፈህ ብሶትህ ግለጽ !!!!
በመቀለ የምትገኙ የፓሊስ ፣የክልል ትግራይ ልዩ ሀይል ፣ፈደራል ፓሊስ ፣ሁሉም የፍትህ አካላት ፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆናቹ ሰራቶኞች ፣እንዲሁም የህወሓት አባላት ካድሬዎች ፣ድህንነቶች ወ ዘ ተ በሙሉ ነገ ቅዳሜ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የሀገራችን ሉአሏውነት አሳልፈን አንሰጥም የሚል ሞፎከር የያዘ በመሆኑ ፣ ይህ አጀንዳ የሁላችን ዜጎች እና ሀላፍነት በመሆኑ ፣እዚሁ ሀገራዊ መድረክ አንዱ እንቢ አገሬ አልሰጥም ሲል ፣አንዱ የለም አገር የለህም ዝም ብለህ ተገዛ የሚል መሆን የለበትም ። በመሆኑ ፖለቲካዊ ልዩነታች አቆይተን ሰለሀገራችን ሉኣኧሏውነት ከመሸጥ መከላከል አብረን ዘብ እንቁም !!
ለዚህ ከ20 አመት በኃላ አገርሽቶበት የኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ የክሀደት ወንጀንጀለኛ ውሳኔ ተጠያቂው የኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ሲሆን የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ጨምሮ ማለት ነው ፣ በተለይ ደግሞ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የህዝብ ፍላጎት ያልሆነ ህዝብ መሬታችን ሰጥተንም ቢሆን ሰላም እንፈልጋለን እፈልጋለን እያለ ነው ብሎ ለኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ የውሼት ሪፖርት አቅርቦ አሰወስኖ ሲያበቃ ተቃውሞ ካለው በኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ልዩነት ወይ አቋሙ ይዞ ወጥቶ ደረጃ በደረጃ ሊፈታው እየተገባው ፣ከዛ አድፍጦ ትግራይ ከመጣ በኃላ የትግራይ ህዝብ የተቃውሞ እሳት ጎርሶ ቆይቶ ሊበላው መሆኑ ስለገባው ፣ተገልብጦ የህዝብ ጥያቄ የሚደግፍ መስሎ እቺ አገር ወደ ቀውስ ጎደና ሲመራት ይታል ። ይህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ የሚሆነው በዋናነት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ሲሆን ፣በተጨማሪ ካሁን በፊት በተለያዩ ምክንያት ከህወሓት ስራ አሰፈጻሚ እና ማእከላይ ኮሚቴ የወጡ ያረጁ ያፈጁ በማይመለከታቸው የስልጣን እርከን እየገቡ ሴራ እየጠነጠኑ የኖሩት ናቸው ።
በመሆኑ የህወሓት ማእከላይ ከሚቴ ይዛችሁት ያለ መንገድ እጅግ መጥፎ አቅጣጫና ለአገራችን አንድነት ለአደጋ የሚዳርግ (የሚያጋልጥ ) ስለሚመስል ፣ይህ እኔ ከመትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች እገሌ ከማለት ይልቅ ቆም ብላቹ በማሰብ በአካልም በአስተሳሰብም ተዳክማችሁ ስላላችሁ ፣በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን በሳይንሳዊ መንገድ ሊመራ የሚችል (ሊተካችሁ ) የሚችል በሽ የሚቆጠር በቁ ወጣት ሙሁር ስላለ ፣የክብር እና የእውቅና ሽልማት ወይ ምስክር ወረቀት ከፈለጋችሁ ስልጣናችሁ አስረክባችሁ የቀረች እድሚያችሁ ትንሽ እውቀት ካለች ለተኪ ወጣት አሟኩሩባት ።
በተረፈ ድል ለነገ የተቃውሞ ሰልፋችን !!
ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
መቀለ
08 / 10 /20 10
