ወያኔና ኦነግ መቼም ተለያይተው አያውቁም ስንል ከምንም ተነስተን አልነበረም፡፡ ዛሬ ላይ የምታዩትን እውነት ለ27 አብረው እንደነበሩ ማሳያ ነው፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ ኦነግ የተባለው ቡድን እንዴትና ሜቼ ከወያኔ ጋር መሥራት እንደጀመሩ አላውቅም ግን በአለፉት 27 ዓመት አብረው የሰሯቸውን ሴራዎች በደንብ አናስተውል፡፡ ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ የኦነግ አመራሮች ኦሮሞን ሁሉ ኦነግ ከአደረጉ በኋላ የኦሮሞ ልጅ ሁሉ ኦነግ ነህ እየተባለ ሲታረድ እነሱ ወደሚፈልጉት አገር በቦለይ በአውሮፕላን ነበር የተሸኙት፡፡ ይህ ብቻም አደለም የኦነግ መስራችና ጸሀፊ በመባል የሚታወቁት(በእድሜ ትልቅ ስለሆኑ አንቱ ማለት ግድ ይለኛል) አቶ ሌንጮ (ዮሐንስ) ለታ ኦነግ አሸባሪ ተብሎ ኦሮሞ ሁሉ በኦነግነት እየታደነ በሚታፈንበትና በሚታረድበት ወቅት አንድ የኦነግ አባል ከውጭ አገር ቤት ይገባና ታሰረ፡፡ ልብ በሉ ሌንጮ ይህ ሰው አስፈታለሁ ብለው ቀጥታ ከሚኖሩበት የውጭ አገር አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ሶስት ቀን ጉድ ተባለ፡፡ እውነትም እኛ ጅሎቹ ነን እንጂ ጉድ የሆነብን ለካ ሌንጮ የመጡት በጠላትነት የሚፈልጋቸው ቡድናቸውን አሸባሪ በማለት በሥሙ (ኦነግ) ሥም ኦሮሞን የሚያፍነውና የሚያረደው ወያኔ የሚተማመኑበት ሚስጢራዊ ቡድናቸው ነው፡፡ እውነትም ሶስት ቀን ሻራተን ተዝናንተው ታሰረ የተባለውን ይዘው ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡  አሁን ግን እንደምጠረጥረው ጭራሽ ተጠርተውም ይሄዱ ነው የሚመስለው፡፡

ከዛ ለበርካታ ዓመታት ወያኔ ሕዝብን ያለ በአረመኔነት እየገደለች የአገርን ሀብት ሁሉ እየዘረፈች ኖረች ኦነግና መሰሎቹ ሌሎች የወያኔ አጋሮች ሁሉ ኤርትራ ጽ/ቤት ከፍተው መነገድ ጀመሩ፡፡ ንግዱም ኤርትራ ውስጥ በእርግጥም እስከ አስመጪና ላኪነት ሲሆን ከወያኔ ጋር በአላቸው ዋና ሥራ ደግሞ ወያኔ ከኢትዮጵያ የምትዘርፈውን ለአገልግሎታቸው መቀበል ነው፡፡ ይህ ድራማ ኤርትራ ውስጥ በመሸጉት ቡድኖች ሁሉ የተከወነ ነው፡፡ ልብ በሉ ይህ ማለት የኦነግ አመራር ሁሉ ወይም በሌሎችም ያሉ የቡድን አባላት ሁሉ ላይሆን ይችላል፡፡ ይህን ድራማ የሚሰሩት ቡድኑን በዋነኝነት የሚመሩ ወሳኝ የሆነ ቦታ ለወያኔ ደጀን ሊሆኑ በሚችሉበት መልኩ በአላማ የሚሰሩ ናቸው፡፡ በዚህ ቀመር ነበር ግንቦት 7ንም ከኦነግ ጋር ተመሳሳይ ንግድ ውስጥ አለ ብዬ የምወተውተው፡፡ ምን አልባት አንዳርጋቸውና ጥቂት ሌሎች በግንቦት 7 አሉ ብላችሁ አትሸወዱ፡፡ አመጣበታለሁ፡፡ በአጠቃላይ ኤርትራ ውስጥ የመሸጉት ቡድኖች እውነታ ይሄ ነው፡፡ ልብ በሉ ወያኔን ለመጣል ሕዝቡ የሞት ሽረት በሚያደርግበት ሰዓት ድምጻቸው እንኳን አይሰማም፡፡ ግን የሕዝቡ ትግል አይሎ አንድ ምዕራፍ ሊዘልክ እንደሆነ ሲያዩ ወያኔም ከአገር ቤት ምልክት ስታደርግላቸው በጣም ወሳኝ ሥራ ይሰሩላታል፡፡ ልብ በሉ የኦሮሞና አማራ ሕዝብ ከ25 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ወንድሜ ወንድሜ የሚለውን ጥሪ እርስ በእርስ ሲጠራራ የሰማች ዕለት ወያኔ ወደመቃበር እወረደች እንደሆነ ስትረዳ ከዚህ አደጋ የሚያወጣትን ሴራ እንዲከውንላት ኦነግን አሰማራች፡፡ በለንድን ያያችሁት የኢትጵያን እንበታትናታለን ድንፋታና ያ ሁሉ ጭብጨባ ሲደረግለት ያያችሁት ኩነት ልዩ ሴራው ነበር፡፡ አላማው ኦሮሞ በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጥላቻ ሲያይ አማራው እንዲበረግግና ዳግም ከኦሮሞ እንደ ጠላት እንዲተያይ ነው፡፡ አማራ የአገር አንድነት ሥነልቦናው ጠንካራ ነው የሚል እምነት ስለነበራት፡፡ በእርግጥም ብዙ የሚባል ኦሮሞን አንዴት ከኢትዮጵያዊነት አንዳመከኑትና እንደልባቸው የሚዘውሩት እንዳደረጉት በተደጋጋሚ ጽፌአለሁ፡፡

አሁን ላይ ኦነግን በአሸባሪነት ሥም ለመጠቀም ነገሮች ሁሉ በለማ ቡድን ተበላሹባቸው፡፡ በእርግጥም ዛሬ ኢትዮጵያ እየተመራች ያለቸው በምርጥ ልጆቿ ስለሆነ የወሮበሎቹ መዋቅር እየፈራረሰ ስለሆነ ያለው አማራጭ በቀጥታ ሕዝቡ ውስጥ በመሰግሰግ ሰላም ማደፍረስ ነው፡፡ ዛሬ ኦነግና ወያኔ እድላቸው ሁሉ ስለጨለመ የመጨረሻ ሙከራቸውን እየተንደፋደፉ ነው፡፡ ኦነግ በኦሮሚያ በሙሉ አማራን እየመረጠ ማጥቃቱን ተያይዞታል፡፡ ለዚህ ተግባሩ ሙሉው ወጪው በወያኔ ነው የሚሸፈነው፡፡ አማራ ብቻም ሳይሆን ኦሮሞንም ማስጠቃት የሴራው አካል ነው፡፡ ኦሮሞን ለማጥቃት ግን የኦነግ አባላት በቀጥታ ሳይሆን በወያኔ በኩል ነው፡፡ ኦሮሞን ለማጥቃት ግን ኦነግ በሆነ ቦታ አለሁ ብሎ እንዲናገር ከዛ በአሸባሪ ሥም ምክነያት ፈጥሮ ሕዝብን መግደል ነበር፡፡ ለምሳሌ የሞያሌውን ሴራ ያስታውሱ፡፡  እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ሌላው ነጥብ ትግሬ ኦነጎችም አሉ፡፡ ወያኔና ኦነግ ዛሬ የእነለማን ቡድን በኦሮሞና በአማራ ማስጠላትና በሁለቱም ሕዝቦች መካከል የተገነባውን አንድነት መልሶ ለማፍረስ እንቅልፍ አጥተዋል፡፡ ነገሮች ከእጃቸው እንዳመለጡ ቢረዱም ግን 27 ዓመት የገነቡትን የዘረኝነት ሴራ ለመጠቀም ዛሬም እየተንደፋደፉ ነው፡፡

ወደ ደቡብ አዋሳ ልውሰዳችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመት ትልቁ ቸህግር የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ በወያኔና ኦነግ ከኢትዮጵያዊነት መምከንና ይበልጠውንም አማራን እንደጠላት እንዲያስብ መሆኑ ነው፡፡ በትልቋ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነገር ፋታ ስለነሳን ላለፉት 27 ዓመት በሌሎች ብሔረሰቦችና ክልሎች ውስጥ ያለውን ብዙም አልሰማን ይሆናል፡፡ ከሰማንም አንዱ ክልል ከሌላው ሲጋጭ ነው፡፡ ብዙ ግፍ ከአስተናገደውና ከጥቂቶቹ በቀር ከአልተሰማው ክልል አንዱ የደቡብ ክልል ነው፡፡ በደበቡ ክልል በተለይ አዋሳና አካባቢው የሲዳማ አክራሪዎች በሌሎች ሕዝቦች ላይ የሚያደርሱት በደል ሳይረሳ በወላይታ ሕዝብ ላይ ግን በልዩ ሁኔታ በጠላትነት ሲጎዱ ኖረዋል፡፡ ከአንድ 10 ዓመት ገደማ ተነስቶ በነበረ ሁከት ወደ 6000 ሕዝብ አብዛኛው ወላይታ እንዳለቀ ይነገራል፡፡ ከዛም በተደጋጋሚ ግጭቶች ነበሩ፡፡ የኦነግና ወያኔ ሥሪቶች የኦሮሞ አክራሪዎች ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ እንደሚሉት የሲዳማ አክራሪዎችም እንዲሁ አዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን በአሉ ቦታዎች ከሲዳማ ውጭ  ያሉ ይውጥልን ዛቻና ማስፈራራት እጅግ የተለመደ ምን አልባትም ከኦሮሚያው የከፋ ነው፡፡  ወያኔ በኦሮሚያ ኦነግንና ደጋፊዎቹን ስትጠቀም በደቡብ የሲዳማ አክራሪዎቹን ነው የምትጠቀመው፡፡ ለዚህ ደግሞ በዋናነት ክልሉን የሚመሩት መሪዎች ዋና አጋር ናቸው፡፡ ኃ/ማሪያም ወላይታ እንደሆነ ይነገርለታል ግን የወያኔ ቅጥረኛ ስለነበር የወያኔን ሴራ አከናዋኝ ነበር፡፡ በደቡብ ከአባተ ኪሾ ጀምሮ ሲዳማ የሚነገረው ከሲዳማ ሌላ በክልሉ እንዳይኖር ነው፡፡ወያኔ የጠ/ሚኒስቴርነቱን ቦታ እንዲይዝ የሞት ሽረት ስታደርግለት የነበረው ሽፈራው ዋና የዘረኝነት መሪው ነው፡፡ ምን አለፋችሁ አብዲ ኢሌ ብትሉት ይቀላል፡፡ ከጉራ ፈርዳ አማሮችን በግፍ በማስወጣቱ ወያኔ እንደ ልዩ ባለውለታ ነው የምታየው ይህን ግለሰብ፡፡ አሁንም በአዋሳ ለምናየው ግጭት ሰውዬው አለበት ቢባል ለምን ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ እውነታው ሰውዬው በአብይ አስተዳደር ሊቆይ እንደማይችል ገብቶታል፡፡ አብይ አዋሳ ሄዶ የነበረም ጊዜ ከእኛ ሽማግሌ የተነገረው እውነት ሽፈራውን እጅግ አበሳጭቶታል፡፡ አብይም ቢሆን በወቅቱ ስላልቻለ እንጂ ሽፈራውንም ሆነ ሌሎች ብዙ በሕዝብ ዘንድ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ሁሉ በቅርብ ከኢትዮጵያ የመንግስት ሥልጣን እንደሚወገዱ አላጣውም፡፡ አሁንም በአንዳንዶች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ ግን እስኪ አንደው በሂሊናችሁ ሳሉት በአብይ ቦታ ሽፈራው ተመርጦ ቢሆን! እግዚአብሔር ያያል! ኢትዮጵያንና ልጆቿን መከራቻን   አስቧል፡፡ እስካሁንም የራሳችን ክፋት እንጂ ከዚህ ቀድሞ በደረሰልን ነበር፡፡ አሁንም እርግጥ ከክፋታችን አልተመልለስንም፡፡ ሀይማኖት፣ ስብዕና ሁሉም ከእኛ መክነው በጥላቻ ታውረናል፡፡ ልብ በሉ እኔ ዘረኛ አደለሁም ከማለታችን በፊት እሰኪ ዘረኝነት ምንድነው የሚለውን አጥኑ፡፡ ዛሬ ብሔረተኛ ተብሎ የተሸሞነሞነው ቃል ፍፁም  አሳፋሪ የሆነው ዘረኛ መሆኑን ለአፍታም አትዘንጉት፡፡ ሌብነት ሙስና ሲባል እንደኖረው ነው!

የሰሞኑ ሌላው የዘረኝነት ሴራ የወልቂጤው ጉድ ነው፡፡ ቀቤና ጉራጌ ሌላውን ጉራጌ ጉራጌ ወደ አገሩ ይግባ ያለበት የዘረኝነት ጽንፍ፡፡ ኦሮሞ ከሱማሌ አማራ ከኦሮሚያና ከደቡብ መሳደዱ አይግረመን፡፡ውስጡን ስለማናውቅ ነው፡፡ ትንሽ ቆይተን የሐረር ኦሮሞ ከወለጋ ወለጋም ከሀረር ሲባረር እናይ ነበር፡፡ አሁንም በይፋ ስላልተነገረ እንጂ ጥላቸውን እናውቀዋለን፡፡ ሌላ ቀርቶ እንደወንድም አማች የሚተያዩት ጉጂና ቦረናም ተጣልተው ብዙ ደም ተፋሰዋል በወያኔ ዘመን፡፡  የወልቂጤው ክስተት የዚህ መገለጫው ነው፡፡ ልብ በሉ ወልቂጤ የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ እንደሆነ አስተውሉ፡፡  ጉራጌ ወደ ሀገሩ ይግባ ብለውት እርፍ አሉ ቀቤናዎች፡፡ የሚገርመው ሀይማኖትም ሰብዕናችንም በጣም ስለወረደና ስለተዋረደ እንደ ድሮው በፈጣሪ ሥም ሊባል የሚችል ሕዝብ እያጣን መምጣቱን ነው በወልቂጤው ሁከት የታዘብኩት፡፡ ቀቤናዎች በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ እንግዲህ ይህን ሁሉ ሁከት የፈጠሩት በረመዳን ወር መሆኑን አስተውሉ፡፡ ለወያኔ የተገዛ በቃ እንዲህ ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ትግሬ ሀይማኖቱን ክዶ በወያኔ ወንበዴ ሙታኖች የሚምለው ወዶ አይምሰላችሁ፡፡

በመጨረሻ  አንድ ጥያቄዎች ለአቶ አንዳርጋቸውና ለአቶ ሌንጮ ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ ጥያቄው ተመሳሳይ ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ስለ ግንቦት 7 ሚስጢር የምታውቀውን ሳትዋሽ ትነግረናለህ? እውን ግ7 ከእስር ስትፈታ ተጠናክሮ ነው ያገኘህው? ኤርትራ ውስጥ ምን እየተሰራ ነው? አንተ ከእስር ስትፈታ ሕዝብ የተቀበለህ በግንቦት 7ነትህ ነው ወይስ አንዳርጋቸውን እንደ አንድ ልዩ ታጋይ? እውን ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ስለግንቦት 7 ሕዝብ የሚያወራው እነ ብርሀኑ እደሚያወሩት ነው? ስትታሰርስ የቡድንህ እጅ እንደሌለበት እርግጠኛ ነህ? ታስረህ በነበርክበት ወቀት ቡድንህ ስለአንተ ምን ያደረገው ነገር አለ? ቢያንስ አለመ አቀፍ ማሕበረሰቡን በማሳሰብ፡፡ አትዋሸን፡፡ ዛሬ ምንም የምንደባብቀው ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ብዙዎች ብዙ መከራን የተቀበሉት እንዲህ  በተምታታ አካሄድ ወሮበሎች እድል እንዲኖራቸው ስለተደረገ ነው፡፡  ለአቶ ሌንጮም ተመሳሳ ነው ግን ከእርሶ ጋር የሚሄድ፡፡ እውን እርሶ ተጸጽተው ነው ዛሬ የሕዝብ ወገን የመሰሉት ወይስ ወያኔ አሁን እየተንቀሳቀሰችበት በአለችው ሴራ የውስጥ አርበኛ በመሆን ለማሴር? ኦነግን ለቀቅሁ ሲሉ የለቀቁበት ሚስጢር ምንድነው? ኦነግ ኤርትራ ውስጥ ምን እየሰራ ነው? ዛሬስ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየሰራ ነው? መቼም ስንት አመት የኑሩበት ቡድን እየሰራ ያለውን አላውቅም ሊሉ አይችሉም፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ እርሶ በሚመሩበት ወቅትስ ዋና አላማው ምንድን ነበር? ከወያኔ ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ? ዛሬስ ወያኔና ኦነግ መካክል ያለው ግንኙነት? እኔ ከቅርብ ጊዜ በኋላ የሚናገሯቸውን ነገሮች ከበጎነት እውስዳቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን ሌንጮ ዛሬ ፍጹም ተቀይረዋል በዬ ማመኔ አደለም፡፡ በአጋጣሚ በኦሮምኛም በአማርኛም የሚያወሩት ተመሳሳይ ነው፡፡ ብዙ የዘር ችግር ያለባቸው በተለይ ኦሮምኛ ሲናገሩ ነገራቸውን በውል ለተከታተለ ማን እንደሆኑ ይረዳል፡፡ የግድ እንደ አቶ በቀለ ገርባ በይፋ መናገር ሳያስፈልግ ማለቴ ነው፡፡ እርሶ ጋር ይህን ለማየት ስለአደገተኝ ነው፡፡ ምን አልባት ብዙ አመት በሴራው ሥለሰሩ ለመደበቁ ተሳክቶሎት ይሆን? አሁን አንደባበቅ የኦነግን ከወያኔ ጋር ያለውን ዝምድና የጋራ ሴራዎችን ግልጥ አድርገው ሲነግሩን ያኔ እናምንዎት ይሆናል፡፡

አመሰግናለሁ

ልዑል አምላክ እግዚአብሐየር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ