ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛው ነው።  ጣና የአካባቢው ነዋሪ የህልውና መሰረት የሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ታሪካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ  ባህላዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ቅርስ ከመሆኑም በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ UNESCO የብዙ አእዋፍ፣ ኣሳዎች እንዲሁም እፅዋት ምንጭ ( biodiversity) እውቅና ያገኘ ሐይቅ ነው።

ሃይቁን የአካባቢው ሕዝብ ለማጓጓዣ፤ ለአሣ ምርት፤ለመጠጥ፤ለመዝናኛ፤ለእርሻ(ግብርና)፤ለቱሪዝም እንዲሁም ለግንባታ(አሽዋ) የሚያገለግል ነዉ። በሃይማኖት በኩል በብዙዎች ደሴቶች የሚገኙት ገዳማት እና ቤ/ክርስቲያናት ለክርስትና እምነት ታላቅ ድርሻ ሲያባረክቱ ቆይተዋል::

ክ2012 (እኤአ) ጀምሮ ጣና Water hyacinth (እምቦጭ) በተባለ ባዕድ አረም በመወረሩ የአካባቢው ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ውጭ በመጡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውንና ጎልበታቸውን መስዋዕት ባደረጉ ወግኖች አረሙ ሲወገድ ቆይቷል። በቅርቡ ደግሞ በዉጭ አገር በሚኖሩ  ኢትዮጵያዉያን  በብዙ ጥናት አፈላልገዉ ይህን አረም የሚይስወግድ መሳሪይ ተግዝቶ ተልኮ በቦታው ደርሷል። ለዚህ ግንባር ቀደም አራያነት ስራቸዉ ከፍ ያለ ምስጋናችን እናቀርባለን።

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ደግሞ ጣናን ለመታደግ ይረዳ ዘንድ ክዚህ በታች የሚታየውን መሳሪያ (Aquamarine H5-200 Harvester) በስጦታ ለክልሉ የደን ፤የዱር እንስሳትና፤የአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ለማበርከት ግዢውን አጠናቖ ጨርሷል። በተጨማሪም  የእምቦጭ የአረም  ማስወገጃ የዚህ አይነት  መሳሪያ እሰከ ሰባት እንደሚያስፈልግ ከሃላፊወ ማወቅ ችለናል። 

በመጨረሻም፤ ይህ ጥረታችን እምቦጮ እስኪወገድ ድረስ የሚቻለዉን ሁሉ ለማድረፍ የጎሕ አመራር እና አባላት በሙሉ ከህዝባችን ጎን ምንጊዜም እንደማንለይ እናሳዉቃለን ።  እንዲሁም ጣና ሃይቅ አደጋ ላይ መሁኑ ያሳሰባችሁ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንድትተባበሩ ጥሪያችን በአክብሮት እናስተላልፋለን።