ቴምሳይድ ስታድየም

በእንግሊዟ ማንችስተር በተካሄደ የኤርትራውያን ብስክሌት ፌስቲቫል ተቃውሞ ዘጠኝ ሰዎች ሲጎዱ ስምንት ግለሰቦች ለእስር ተዳርገዋል።

ኩርዞን አሽተን ቴምሳይድ በተባለው ስታዲየም ቅዳሜ እለት በነበረው ዝግጅት ሰላሳ የሚሆኑ ኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ጠርሙሶችን፣ ምግብ እንዲሁም የቢራ ቆርቆሮዎችን ወርውረዋል።

ግለሰቦቹ የኤርትራን መንግሥት ሲቃወሙም እንደነበር ተገልጿል።

አዘጋጆቹ እንደገለፁት ህፃናቱ በነበረው ግጭት አደጋ ውስጥ ወድቀው ነበር ብለዋል።

የኤርትራውያን የብስክሌት ፌስቲቫል ከመቶዎች በላይ ብስክሌት አፍቃሪዎች የተገኙበት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1964 ቶክዮና በ1960 ሮም በተደረጉት ኦሎምፒክ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ብስክሌተኞችም ከመገኘትም በተጨማሪ በዘፈንና በእስክስታ የደመቀ እንደነበር ተገልጿል።

የዝግጅቱ አስተናባሪ አቶ ጎይቶም ስዩም ” ከፖለቲካ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ የለም። የኤርትራን ብስክሌት ለመዘከር የተዘጋጀ ዝግጅት ነው” ብለዋል።

ከፍተኛ ኃዘን

በአፍሪካ ሻምፒዮንና በኦሎምፒክ ውድድሮች የተሳተፉ ግለሰቦች ነበሩ።

በመጀመሪያ ሰላማዊ ሆነ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን በኋላ ግን ጠርሙሶችን፣ ምግብና የቢራ ቆርቆሮዎችን መወርወር ጀመሩ።

“በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው። ጨቅላ ህፃናት የነበሩበት ነው። ግለሰቦች ቆስለዋል፤ ደምም ፈሷል” በማለት አቶ ጎይቶም ይናገራሉ።

ይህ የሚያስደስት ፌስቲቫል የነበረ ቢሆንም ብዙዎች ግን ያዘኑበት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጎይቶም በእነዚህ ተቃዋሚዎች ምክንያት ህፃናት አደጋ ውስጥ የወደቁበት ነው።

ሰላማዊ ሰልፍ በታኞች ስታዲየም ገብተው ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሲሆን፤ የህዝቡን ሰላም በመረበሽ በሚል ነው የታሰሩት።

የአካባቢው ኢንስፔክተር አንዲ ኃርቲ ድርጊቱን አውግዘው ለቴምሳይድ ነዋሪዎችም ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች ወደ ፍትህ እንደሚቀርቡ ቃል ገብተዋል።

የኩርዞን አሽተን ቃልአቀባይ በበኩላቸው ፖሊስ ጉዳዩን እየተከተታለውና ምርምራዎች የቀጠሉ መሆናቸውን ገልፀው በዚህ ወቅት ምንም አስተያየት እንደማይሰጡ ተናግረዋል።

 

Source    –   BBC/AMHARIC

 

Police condemn ‘appalling’ violence at cycle festival

  • 17 June 2018
Tameside Stadium

Police have condemned the “appalling” violence at a cycling festival in Greater Manchester that saw nine people hurt and eight men arrested.

Thirty protesters stormed the Eritrean event at Curzon Ashton’s Tameside Stadium on Saturday, throwing bottles, food and beer kegs.

Organisers said frightened young children were put in danger by the violence.

It is thought the men were protesting against the Eritrean government.

Tameside Stadium
ASHLEY STOCKS
Police escort away two young men after the trouble at Curzon Ashton’s ground

The Eritrean Cycle Festival was attended by hundreds of people, with singing, dancing and appearances from cyclists who appeared at the 1964 Olympic Games in Tokyo and 1960 Games in Rome.

Organiser Goitom Seyoum, 48, said: “This had nothing to do with politics – this was purely a celebration of Eritrean cycling.

‘Sad feeling’

“We had African champions here and people who appeared at the Olympics.

“It was a peaceful protest at first and then they barged in throwing bottles, food and beer kegs.

“It was outrageous – there were children in buggies and people cut and bleeding.

“This was supposed to be a festival but now we leave with a sad feeling.

“Young children were put in danger by these cowards.”

Tameside Stadium
ASHLEY STOCKS
Ambulances and police attended the scene at Tameside Stadium

Riot officers were deployed by Greater Manchester Police at the stadium in Ashton-under-Lyne.

Those arrested were held on suspicion of public order offences.

Ch Insp Andy Harty said: “The vast majority of people attending the event today were innocent people, including children, who sadly got caught in the middle of this appalling act of violence.

“This type of behaviour is completely unacceptable and I want to assure the residents of Tameside that we are doing everything we can to bring any offenders to justice.”

A spokesperson for Curzon Ashton, who play in the National League North, said: “Police inquiries are currently ongoing and no further comment will be made at this time.”

Tameside Stadium

GOOGLE
Curzon Ashton’s Tameside Stadium where the violence erupted during a family cycling event
SOURCE    –   BBC