ሕዝብ፥ ዴሞክራሲያዊ ተቀባይነት፥ ምክክር፥ መርሕ፥ሕጋዊነት፥ ተቋም ይቅደም!!! አልክ? ይን ለመናገር አንተ አይከብድህም?

በመለስ ራዕይ የጠበበ ጭንቅላት አሁን ላይ የተነሱ ምጡቅ ኢትዮጵያውያን ራዕይ ሊገባው አይችልም፡፡ በደህና ቀን ኢትዮጵያዊ የሚባል ነገር የለም ብለህ ስትናገር እኮ ነው ከእውነትና እውቀት ሙልጭ ብለህ እንደወጣህ ያወቅንው፡፡ በኋላም ከአንድ ምሁር ነኝ ከሚል አይጠበቅም እያልን በምንሞግትበት ወቅት ጭራሽ ለጤነኝነትም የሚያጠራጥር ቃላቶችህን ከራስህ አንደበት መስማት ቀጠልን፡፡ ሰሚ ያገኘህ መስሎህ ነበር፡፡ አሁን እየሆነ ያለውን ነገር እንደሚሆን ግን እኔ ራሴው ነግሬህ ነበር፡፡ ችግሩ ምሁር ነኝ ስላልክ እውቀት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ ስላልክ እንዳይሆን፡፡ ለማንኛውም እጅግ አደገኛ የሆነው የዘረኝነት መንፈስህ ነው ሁሉንም ነገር ማየት እንዳትችል የጋረደህ፡፡ ስለ አብይ ያነሳሀቸውን ነጥቦች አየሁልህ፡፡ ፊደል ለሚቆጥሩ ምን አልባት የምሁር አስተያየት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ነገሩ ፊደል መቁጠርም አያስፈለግም እንደውም በተሻለ ፊደል አልቆጠሩም ያልናቸው በስለው ተገኝተዋል፡፡
በአጭሩ ችግርህ የአብይ አንተ ከገመትከው በላይ ፈጥኖና ገኖ መውጣት ምትሀታዊ ስለሆነብህ ነው፡፡ አብይ እኮ እየሰራ ያለው አንተ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት ብለህ ስለአመንክበት ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ነች እንጂ የጠላቶቿ አለችም፡፡ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ጉዳይ የትኛው የሞራል ልዕልናህ ነው መካሪ ለመሆን የሚያስችልህ?
በገዘፉ ቃላቶች ምሁር ለመምሰል አማርኛው ገላጭ ሆኖ እያለ አምጠህ በወለድካቸው ኢንግሊዘኛ ቃላቶች በማጀብ ትልቅ ሀሳብ ያለህ አስመሰልከው፡፡ አዝናለሁ፡፡ አብይ የአንተን እቅድ ሳይሆን የአገርንና ሕዝብ እቅድ ነው እየሰራ ያለው፡፡ ትልልቅ ዛሬ መነሳት የሌለባቸው ስትል የተቸሀቸውን ልክ አሳቢ ለመምሰል፡፡ ለመሆኑ ስለራዕይ ምን ታውቃለህ፡፡ የሶማሌና ኢትዮጵያን አንድነት በሀሳብ መነጋገር አይችልም የምትለው ሰው እኮ አንደሚችልና በተግባርም ሊያሳካው የሚችልበትን ሂደት አድሉን ማየት ስለሚችል ነው፡፡ በጨለምተኛ የእኔ ሰፈር ምናምን በሚል አእምሮ አደለም፡፡ ጽሁፍህ በእርግጥ የሆነ ወቅት ስለ ሰላም አወራለሁ ብሎ ከተበተበው የወያኔው ጀነራል አበባና ጻድቃን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የሆነ እንደተቀደማችሁ ስታውቁ ማደናገሪያ ጥሩ ሀሳብ የዞ የመጣ ለመምሰል ነው፡፡ እውነቱ ይሄ ነው፡፡ የጎበኛቸው አገሮች አብይ ማን እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡ ከአንተ በተሻለ አገርን የሚመሩ ትልልቅ ሰዎች አብይ እየሄደበት ያለውን ሂደት ስለተረዱ ነው እኮ በትኩረትና በጥሞና እየተከታተሉትም እያመኑትም ያሉት፡፡ ከሶማሌ አደለም ከግብጽም ጋር የነበረው ሀሳብ የአንድነት ነው፡፡ እንደሚቻል ስለአመኑም ነው ሀሳቡን የተቀበሉት፡፡ ቤቱ ድረስ መጥተው ምን መስራት እንችላለን የሚሉት እኮ በብዙ እጥፍ መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው ናቸው፡፡ አዎ ግዛትን ማስፋፋት ነው አላማችን እንጂ በቀበሌ ደረጃ ማሰብ አደለም፡፡ አሁን እየሆነ ያለውንና የሚሆነውን ለአንተ መንገር አያስፈልግም፡፡ ከምትፈልገውና ከምትችለው ውጭ ስለሚሆንብህ፡፡ አንተ ብቻም ሳትሆን የኦሮሞ አክራሪዎች ሁሉ ችግር አሁንም እዳለ ያለባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ የአብይ ጉዳይ አንትንና መሰሎችህን አይመለከታችሁም፡፡ አያገባችሁም፡፡ ጉዳዩ የእኛ ጉዳይ ነው፡፡ በፍጥነትም እየሄድን ነው፡፡ ድርድር ምናምን መጥተህ መደራደር ትችላለህ፡፡ ኢትዮጵያዊ የሚባል ነገር የለም ብለህ በኢትዮጵያ ምድር ፓርቲ መመስረት ትችላለህ፡፡ ወደ 50 ዓመት የተጠጋ ሴራ ነው አንተ የጀመርከው አደለም፡፡ አሁን ተቀድማችኋል፡፡ ሁለተኛ አይለምደንም! ዲሞክራሲ ምናምን ሕጎች ምናምን ብለሀል፡፡ አዎ አብይ አደለም እኮ ያን ሁሉ የተበተበው፡፡ አንተና መሰሎችህ ያሴራችሁት እንጂ፡፡ ሕገ መንግስት አልከው? ሕግን በተግባር ማዋል እንዴት እንደሚቻል ለማሳየት እንጂ የመለስ የጥንቆላ ሰነድ በኢትዮጵያ ሕግ ሆኖ እንደማይቀጥል ልነግርህ አወዳለሁ፡፡ መጀመሪያ እሰኪ የተጻፈውን ራሱን እናሳያቸው በሚል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊ ነን ለአንተ አይገባሕም፡፡ አንተ የኖርከውና እስካሁንም ያለህው በመሰሎችህ መካከል ስለሆነ ምን አይነት ሰዎች አገሪቱ አንዳሏት አይገባህም፡፡ አያገባህምም!
የፖለተካ ቡድን ነን ባዮች እድሉ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ፍቃደኛ የሆኑት ጥሪውን ተቀብለው ገብተዋል፡፡ ሌሎቹ አሁንም እየፎከሩ ነው፡፡ በተለይ ኦነግ በአዲስ መልክ ፉከራ የያዘ ይመስላል፡፡ እንደ እስከዛሬው የሚታረድ ኦሮሞ ያግኝ መስሎታል፡፡ ስለምርጫውም ሆነ ስለሌሎች የሕግ ማስተካከያዎች እየተሰራ ነው፡፡ ችግሩ እንዲህ በአንድ ጀምበር የሚሆን አለመሆኑ እንጂ፡፡ የአስቸኳ ጊዜ የተባለው የሽብር አዋጅም ለምን አውቀናል፡፡ ገና አይደለም የመለስ የጥንቆላ ሰነድ ሁሉም በወያኔ ሕግ ሆነው የወጡ ሰነዶች ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አንጻር ብቻ ተፈትሸው እርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡ ሥራ አልቆመም፡፡ ዲሞክራሲ ምናምን እያሉ የሚያቅራሩ እስኪ የት አሉ፡፡ ችግሩ እኮ ከመጀመሪያውም የአገርና ሕዝብ ጉዳይ ስላልሆነ ነው ጉዳያቸው፡፡ አሁን ጉድ ሆኑ፡፡ ኢትዮጵያ ሳያስቡት በልጆቿ እጅ ገባች!!
በዚህ አጋጣሚ ብዙ በበፊት በኦሮሞ ፈርስትነት የምናውቃቸው ሰዎች ወደሕሊናቸው እንደተመለሱ ብናውቅም አሁንም ገና የሚቀሩ አሉ፡፡ ምን አልባትም አንዳንዶቹ መመለስ ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰው ሁለተኛ ላይመለሱ ይችላሉ፡፡ ጸጋዬ አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት ደግሞ ቃላትን በመቀባባትና የሕዝብን ትኩረት በሚስብ መልኩ በመናገር በውስጥ ግን መርዛቸውን በመትፋት ነው፡፡ አሁን ግን ቢቀርባችሁ ይሻላል ነው የምለው፡፡ ዋነኞቹ አሁንም እዛው ናችሁ! አብይ ላይ ጥርጥር እንዲኖረን ብዙ ሞክራችሁ ነበር! አሁን እሱን አልፈን ብዙ ርቀን ሄደናል!
ለዑል አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!
