እኔን አልገባኝ ይሆን ወይስ? ጥላሁንን ማንገስ ቴዲን ማንገስ? ሀብታሙ አያሌው ሆይ ስለምንድነው የምታወራው ለመሆኑ? እሳቸው ዶ/ር ዛሬ የሚናገሩት ትላንት ቴዲ አፍሮ የዘፈነው ነው፡፡ አብይ ከቴዲ ኮርጆ ነው ማለት ነው? ለመሆኑ ግን አንተ የቴዲ ጉዳይ ይሄን ያህል አንገብግቦህ ነው? ነው የቴዲ ደጋፊዎች፣ የጥላሁን ደጋፊዎችን ድምጽ ለማግኘት፡፡ ሀብታሙ አያሌው አትሳሳት ብዙዎች መዝፈን ሳይሆን ነብሳቸውን ሰውተዋል፡፡ በማይቀለድበት እውነት አሳመርኩ ብለህና የራስህን ምኞች እዚህ ላይ በውዥነብር ትልቅ ሀሳብ አታድርግ፡፡ በማሰብም ከሆነ ከቴዲም ሆነ ከጠራሀቸው ሁሉ ኢትዮጵያ የሚያስቡላት ልጆች አሉ፡፡ ቴዲ መልካም አደረገ፡፡ አገሩን ሕዝቡን መውደዱ አንተ እንድትናገርለትና እንድታደንቀው ሳይሆን ግዴታው ነው፡፡ አንተ ግድፈት (ፋላሲ) በመስራት ትልቅ ጆሮ ለማግኘት ይመስላል፡፡ ጥሩ አደለም፡፡ እሺ የአብይ ንግግር ከቴዲ ዘፈን የተኮረጀ ነው እንበል፡፡ በኮፒ ራይት ለመጠየቅ እንዲመች ማለት ነው፡፡ በስቃይ ላይ ያሉትን ወደተስፋ የመለሰበት ተግባራዊው እርምጃስ፡፡ ላንተ ቴዲ ብቻ ነው አደል ኢትዮጵያዊ ነው ኢትዮጵያዊ ከሆኑ እንደቴዲ መዝፈን ነበረባቸው ነው፡፡ ጥሩ አደለም፡፡ ኢትዮጵያ ስትነግስ ቴዲ መንገስ አለበት…..? ይሄ አሁን ምን የሚሉት አመክንዮ ይሆን?ስታሚኝ ሰሙሽ ስህተትሽን ያለው ከያኒ ትዝ አለኝ! ለማንኛውም ጥሩ እንዳልሆነ ብቻ አስረግጬ እነግርሀለሁ፡፡ አስቴር በdhaኔ ያልተገኘችበት፣ ማን ደሳለኝ ነው ደግሞ ያልከን ያልተገኘበት…? የምታወራው ሁሉ ለራስህ ገበያ ለማግኘት እንጂ ከሆነው ነገር ጋር የሚሄድ አደለም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ሰው ተበሳጭቷል ግን ከንጹ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ለንግድ ትርፍ ስላለው አደለም፡፡ የሆነው ነገር እንድናስብበት ጥሩ ነው፡፡ ብዙ ነገሮች ለመጥፎ በሴረኞች እየተደረጉ ለእኛ ብዙ ትምህርት እየሆኑንና እንደግብዓት እየተጠቀምንባቸው ነው፡፡ የቅዳሜው ሙከራ በራሱ ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠን፡፡ የትላንቱም የአስቴርም ሆነች ሌላ ሰው ከአለ መታገድ ይህን ያደረጉት ይጋለጡ ዘንድ ነው፡፡ ዝም ቢሉ እኮ ሳናውቃቸው አብረውን ሊኖሩ ነው፡፡ አንትን ግን ያንገበገበህ የአስቴር መታገድ አይመስለም፡፡ ትልቅ ሆኖ ለመታየት ትልልቅ ናቸው ብዙ ደጋፊ አላቸውና ጆሮ አገኛለሁ የሚል እሳቤ ይመስላል፡፡ በፍልስፍና አርጉመንተም አድ ፖፑለም ይባላል፡፡ ብቻ ብዙ ማለት አልፈልግም ግን በጣም የማይረባ ነገር ነው፡፡
ሌላው ብዙ ጊዜ ያለኩት ራሱ ኢሳት የተባለው ሚዲያ ነው፡፡ ኢሳት ውስጥ ጥሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን በዋናነት ኢሳት ጉዳያቸው የንግድ አልፎም የሴራ ማስፈጸሚያ ሆኖ የምናየው ነው፡፡ የለንደኑ ወንድማገኝ ጥሩ ጥሩ ሥራዎችን ለሕዝብ አቅርቧል፡፡ ሰሜን አሜሪካ ያሉት ግን አሁን አጋጣሚ እየፈለጉ የሚነቁሩን ናቸው፡፡ ኤርሚያስ አሁንም እኔ ብያለሁ ከፈለጋችሁ መጻፌን ግዙና አንብቡ ይለናል፡፡ ሥራ አላጣንም፡፡ ላንተ እውቀት ማለት የወያኔን ጉዳይ ማራገብ ነው፡፡ ስለወያኔ አንተ አውቃለሁ ከምትለው በላይ ብዙዎች ያውቃሉ፡፡ ለንግድ ሳይሆን ለአገርና ሕዝብ ለማዳን እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ማናችሁም የአብይም ሆነ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምታስቡት ውጭ ሆኖባችኋል፡፡ በአንድ ሌሌት የመጣም ግን አይምሰላችሁ፡፡ ላለፉት 3-4 ዓመታት ብዙ ኢትዮጵያውያን መስዋዕት እስከመሆን ድረስ የተከፈለ ብዙ ዋጋ አለ፡፡ ብዙ ያልተደረሰባቸው ቦታዎች ነበሩ አሁን ሁሉም ተደረመሰ፡፡ ፍጥነቱም ግሩም ነው፡፡ ግን ማንም ዋጋ ሊወስድበት አንፈልግም፡፡ ይህን ሁሉ በአይናችን አንድናይ ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን!! ዛሬ እንደተራ ስለተለመደ የምንለው አይገባችሁም፡፡ ግን እግዚአብሔር ለዚህ ዓላማ የተጠቀመባቸው ምስጉን ናቸው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያን ከገደል አፋፍ የመለሷት ልጆቿ እነሀብታሙ የሚያደንቋቸውን ዘፋኞች ዘፈን ሰምተው አደለም፡፡ ሰቆቃን ምሬትን ተጋፈጧት እንጂ፡፡ ይህን ስንወስን የልዑል እግዚአብሐየር ክንድ ተዘረጋችልን!
የዲሲ ግብረኃይል ለለውጡ ምክነያት እኔ ዋናው ነኝ አለ አሉ፡፡ አትሳሳቱ ልፋታችሁንም አታርክሱ፡፡ የበኩላችሁን ጥረት ማድረጋችሁን አደንቃለሁ፡፡ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣው ለውጥ እናንተ ዋጋ የምትሻሙበት አደለም!! ስላደረጋችሁት ለራሳችሁና ለሂሊናችሁ መልካም ነው ግን እኔ ነኝ ብሎ ዋጋ ለመሻማት መሞከር ጥሩ አደለም፡፡ ለውጡ ከጠየቀው ዋጋ ጋር የእናንተ ጥረት ምንም አደለም፡፡ ከነጭርሱም ማንም አያውቀውም፡፡ ለራሳችሁ ግን ጥሩ አደረጋችሁ፡፡ ጥቂቶች በኤች አር 128 የተሳተፉ የተሻለ ሚዛን ያለው ሥራ ሰርተዋል፡፡ አገርና ሕዝብ እንዲህ ባሉ ሰዎች ሲታገዝ አቅሙ ይጎለብታል፡፡ የሚቀጥለውን ምዕራፍም አብይ ተመረጠ ነገሮች እየሰመሩ ናቸው ብለው ዝም ማለት የለባቸውም፡፡ የአሜሪካ መንግስት ከ27ዓመት በፊት አሸባሪ ወንበዴዎች ኢትዮጵያን እንዲይዙ ዋናውን ሚና ተጫውቷል፡፡ ከዛም በብዙ ገንዘብ እየደገፍ ብዙ ኢትዮጵያውያን ለስቃይና ሞት ተዳርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሆነውን ግፍ ሁሉ የአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ገንዘብ ያለበት ነው፡፡ ይሄ ለአሜሪካም ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ እንግዲህ ኤች አር 128 ሲያስተባብሩ የነበሩ ከኤስ አር 168 ጎን ለጎን ለትራምፕ መንግስት እስከዛሬ የሆነብንን ሁሉ አጉልተው ማሳየት ቢችሉ መልካም ነው፡፡ እኔ ከመጀመሪያውም የትራምፕ ደጋፊ ሆኜ ነበር ለዚህም ጥሩ ምክነያት ነበረኝ፡፡ በእርግጠኝነት ትራምፕ እንደነ ኦባማ የሽብር ኃይላትን እድል አይሰጥም፡፡ ያ አገር አለም ያስጨነቀው አይሲስ ዛሬ የት ገባ? በማን ገንዘብ ነበር ሲረዳ የነበረው? አስተውሉ! የሶማሌው አልሸባብስ እውን የሶማሌ ሙስሊም አክራሪ ወይስ የወያኔ የሽብር ቡድን? ዛሬ እስኪ የት ነው ያሉት? አሜሪካ አልሸባብን በወያኔ በኩል ድጋፍ ስታደርግ ነበር፡፡ ዛሬ ሁሉም ነገር በትራምፕ ሲቆም የት እንዳሉ ራሱ ወሬ የለም፡፡ አሸባሪ የምትሉት እንግዲህ ዋና ማስተባበሪያው አድስ አበባ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ነበር፡፡ ስለዚህ ለትራመፕ መንግስት በእርግጥ ያውቀዋል ግን እኛም እንደተረዳንውና አሁንም ከአራት ኪሎ ወጥተው በሕዝብ መካከል የሽብር ተግባራቸውን ለቀጠሉ እየታደኑ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ድጋፍ ልታደርግ አሜሪካ ይገባታል የሚለውን ሀሳብ ጨምሩበትና ሥራችሁን ቀጥሉ፡፡ እስካሁን ለአሸባሪዎች የተሰጠው ገንዘብ የግብር ከፋዩም ማህበረሰብ የመጠየቅ መብት አለው፡፡ ትራምፕ ለብዙዎች ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡ በምላስ መሸንገል የለመደ እንደ ትራምፕ ያለ በተግባር ሲመጣ ባይዋጥለት አይገርምም፡፡ ለእኛ ግን ጥሩ አጋጣሚ ነው!
አሁን ያየሁት ሀጫሉ ከቤተ መንግስት አኩርፎ ወጣ የሚል በአቶ ግርማ ካሳ የተጻፋው አስተያየት አልተመቸኝም፡፡ ሀጫሉ ያደረገው ትክክል ነው! ይሄ ጠባብነትም አደለም፡፡ ችግሩ ብዙ ነው! እውንስ ለምን አልተጋበዙም? ሀጫሉ ብቻውን ከኦሮሞ አርቲስት (ማለቴ በኦሮምኛ ከሚከውኑ) መጠራቱስ ለምንድነው? በማኩረፍ ደረጃ ሳይሆን ጉዳዩን ቦታ እንዲሰጠው ተጽኖ የሚያሳርፍ እርምጃ ነው! በዚህ ምክነያት ሰዎችን ጠባብ ብለን የምናስብ ከሆነ ብዙ ችግር አለብን፡፡ ለዚህ ነገር ፍትሀዊ መሆን ሳንችል ለትልልቅ አገራዊ ፍትሀዊነት እንዴት ማሰብ እንችላለን፡፡ እውነታው ሀጫሉ እንደተናገረው ነው፡፡ ብዙ የኦሮሞ አርቲስቶች ብዙ ግፍ ተቀብለዋል፡፡ እኔ ኦነግን ከወያኔ ለይቼ የማላይ ነኝ ግን ኦነግ ነህ እየተባለ መከራ ሲቀበል የኖረ ስንት ወጣት ጉዳይ እጅግ ያበሳጨኛል፡፡ የዚህ ግብዣ ጉዳይ ችግር አስተባባሪ ነን ያሉት ሰዎች ይመስላል፡፡ ብዙ ሴራ አለው፡፡ ሀጫሉም ያነሳው ከሴራዎቹ የሚደመር ነው ስለዚህ ልጁን ያለቦታው አትክሰሱት! አመሰግናለሁ
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ
