በሚሊየነም አዳራሽ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የበለጠ መቀራረቡን ለማምጣት ትልቅ አሰደማሚ ዝግጅት ተደርጓል። የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ መንግስት መሪ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም በፊትም የቀድሞ የሕዝባዊ ሃርነት ግንባር ኤርትራ (ሸቢይ) መሪ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በአማርኛ ሲናገሩ ተሰምተው አያውቁም። ሆኖም ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ልብን የሚነካ ንግግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርበዋል።

አንድ ነገር መታወቅ ያለበት፣ ሕዝብ ለአቶ ኢሳያስ ድግፍ ሲሰጥ አቶ ኢሳያ ከዚህ በፎት የሰሩትን ግፍ ማጽደቁ አይደለም። ግን በፍቅርና በይቅርታ መንፈስ አዲስ ሆነው፣ ከዶ/ር አብይ ተምረው፣ ሕሊናቸው ወቅሷቸው፣ እስረኞችን እንዲፈቱ፣ የግፍና የመከራ ቀንበርን ከሕዝቡ ላይ እንዲያነሱ፣ የወታደራዊ ማሰልጠኞቻቸውን እንዲዘጉ…ለማበረታታት ነው። የኋላዉን ሳይሆን የወደፊቱን በማሰብ ነው።

የዝግጅቱ መንፈስ በአጠቃላይ በጣም ደስ የሚል፣ ፍቅር የሰፈነነት ሲሆን የተለያዩ አርቲስቶች ደስ የሚሉ ጣእመ ዜማዎችን አሰምተዉናል። አንጋፎቹ መሐመዱ አህመድና አሊ ቢራ በሕመም ላይ ሆነውም በዚህ ቀን ፍቅርን፣ አንድነት ታመንም ቢሆን እናወራለን ብለው መድረክ ላይ ወጥተዋል። መሐመዱ “ሰላም ፣ ስላም፡ እያለ ሰላምን ሲያወጅ፣ አሊ ቢራ ደግሞ ““መልቱ አዳኑባሴ፤ ኤኙ አዳኑባሴ” እያለ እንደ ሙዚቃ ለመስማት በሚጥመው የሃረር ኦሮምኛ “ማንነው የሚለያየን ፣ ምንድን ነው የሚለያየን” እያለ አንድነትን አቀንቅኗል። እነ አረጋኸን ወራሽ “ሁሉም ቢተባበር” ሲሉ እነ ጋሽ አበራ የአገርን ፍቅር ዘክረዋል። ቴዲ አፍሮ ከዉጭ አገር ወደ አገር የገባው ከአንድ ቀን በፊት ስለነበረ ለልምምድ ጊዜ ስላልነበረው በስፋራው እንደ አንድ ታዳሚ ተግኝቶ ነበር።ሆኖ በአዳራሹ መገነኘቱን የሰማው ሕዝብ ቴዲ እንዲወጣ በመጠየቁ የፕሮግራሙ አዘጋጅ በማይክሮፎን ለቴዲ ጥሪ አቀረበለት። ሆኖም ለደህንነት ሲባል በዉጭ አምስት በሮች ከውስጥ ተዘግተው ስለነበረ፣ ቴዲ ወደ መድረኩ ለመመድረስ ወድ ፳ ደቂቃ ወሰደበት። በመድረኩ ከትልቅ ይቅርታ ጋር ዝግጅት እንዳላደረገ ለሕዝቡ ገልጹ፣ ለሕዝብ ክብር ሲል፣ ሳይዘጋጅም፣ ስለ ጓል አስመራ ፣ ስለኤርትራ ህዝብ ፍቅር፣ ፊዮሪና የሚለውን ዝነኛ ዘፈኑን በመዝፈን አቀነቀነ።ፍቅር ያሸንፋል ብሎም ከመድረኩ ወረደ።

ሌላው አርቲስት አጫኩ ሁንዴሳ ነበር። አጫሉ በወቅቱ ምን እንደዘፈነ አብዛኛው የአዳራሹ ታዳሚ አላወቀም ነበር። እንደ አሊ ቢራ የዘፈኑን መንፈስ ለሕዝቡ አልገለጸም። አንድ የአማርኛ ቃል አልወጣውም።ሆኖም በዚህ ትልቅ ቀን ያገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም እርሱ የሚያምንበትን ከዝግጅቱ መንፈስ ጋር የማይሄድ ምልክት ነበር አስተላልፎ የወረደው።
በሶማሌና በኦሮሞ ክልል መካከል አለመረጋጋቶች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። ለዞህም አለመረጋጋት ተጠያቂ በሶማሌም በአማራ ክልል ያሉ አክራሪዎች እንደሆኑና እነዚህ አክራሪዎች የሶማሌ መሬት፣ የኦሮሞ መሬት እያሉ ከነርሱ ዘር ዉጭ ያለዉን እንደ መጤ እንዲመለከቱ ያደረገውን አሁን ያለው እነ አጫሉ የሚደገፉት የዘር ፌደራል አወቃቀር መሆኑ ይታወቃል። የተፈናቀሉ፣ የተገደሉ ኦሮምዎች እንዳሉ፣ የተፈናቀሉ የተገደሉ ሶማሌዎች አሉ። ይሄንን በተመለለተ በሁሉም ቦታዎች በሕዝብ ላይ ሁለት ለሚፈጥሩ አክራሪዎች ዶ/ር አብይ በአዋሳ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወቃል። ከዚያም በፊት ኦቦ ለማ መገርሳም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ሰጧል። ሆኖም አጫሉ፣ ይሄንን እያወቀ፣ እነ ዶ/ር አብይ እነ አቶ ለማ በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው ሃላፊነት ባለበት መልኩ እየሰሩ ባለበት ወቅት፣ “አብይ አዳምጥ፣ ለማ አዳምጥ፣ አለበለዚያ ቄሮን ነው የምልክባችሁ” ብሎ ፎክሮ መሄዱ በርግጥም ትንሽነቱን የሚያሳይ ነው።

“ሁሉም ነገር የራሱ ስርዓት አለው!! መድረክም እንዲሁ!!” በሚል ጦማሪ ደረጄ ገረፉ ጉዳዩን በግልጽ አስቀምጦታል።

“አሁን ጥያቄው” ይላል ደረጄ ሲጀምር። “መድረኩ የኢትዮ-ኤርትራን ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነ የገለጸው ደረጄ ለእርቲስቶች የሚፈልጉትን ዘፈን እንዲዘፍኑ እድል ለመስጠት፣ አርቲስቶችም የሚፈልጉትን ዘፈን የመዝፈን መብት ለመጠበቅም አይደለም። ያንን ለማድረግ የሚፈልግ አርቲስት የሀገሪቷን ህግ ጠብቆ በራሱ መንገድ ያንን ማድረግ መብቱ ነው። በራሱ ገንዘብ ማስታወቂያ አሰርቶ ያንን የማድረግ መብት አለ” የሚለው ደረጄ፣ “ከዚህ አንፃር ለመድረኩ የሚመጥን (የኢትዮ-ኤርትራን ወዳጅነት ከፍ በሚያደርግ መልኩ) ዘፈን የዘፈነው አርትስት ማነው ? “ ብሎ ይጠይቃል። “አንድ ሰው ሰርጉ ላይ አንድ አርትስት ጋብዞ አርትስቱ መዝፈን ያለበት ሙሹራው የሚፈልገውን ነው ወይስ አርትስቱ የሚፈልገውን ነው? አንድ አርቲስት በሰርጋችሁ ላይ ሙሾ ቢያወርድ ወይም ቀረርቶ ቢያቀርብ ትክክል ነው ወይ?” ሲል ደረጄ በተዘዋዋሪ መንገድ የአጫሉን ድርጊት ተችቷል።

ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነ የኦሮሞ ብሄረተኛ አክቲቪስት ግርማ ጉተማ ከደረጄ ጋር አይስማም። “ሃጫሉ ሁንዴሳ ለምን ጌራርሳ ዘፈነ ለማለት ነው ይሄ ሁላ ዙሪያ ጥምጥም? ለምን የህዝቡን ብሶት አሁንም ያሰማል ነው? ይገርማል ብቻ!! ሼም የለም?” ሲል ቅሬታዉን ያሰማል።

ከዞን ዘጠኝ ⶏማሪዎች መካከል አንዱ ማህሌት ፋንታሁን ደግሞ “ጠ/ሚ አብይ ከዛሁሉ የድጋፍ ጭብጨባ እና ወከባ፤ የሃጫሉ ቀረርቶ ናት ልቡ ውስጥ የቀረችው። እናም ዛሬ በመግለጫው ለኦሮሚያ እና ሶማሊያ ክልል ትእዛዝ አስተላለፈ። ሃጫሉ ባያስታውሰው ኖሮ የዛሬውን አይነት መግለጫም አንሰማም ነበር። ዶ/ር አብይ በጭብጨባ እንዳይጠፋ የሃጫሉ አይነት አስታዋሾች በብዛት እና በጥራት ያስፈልጉናል” ስትል አጫሉ በቀረርቶ በነዶ/ር አብይ ላይ የሰነዘረዉን “ቄሮን እልክባቹሃለሁ” ማስፈራሪ የተመቻት ይመስላል።

አጫሉ የርሱ ባልሆነ ዝግጅት ከዝግጅቱ መንፈስን አላማ ውጭ በሶማሌና በኦሮሞ ክልል ስለተፈጠረው አሳዛኝ ሁኔታ ከመናገሩ ከአንድ ቀን በፊት ዶ/ር አባይ በአዋሳ ጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው ፣ ለጥፋት ሃይሎች ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ከላይ ገልዣለሁ። በዚያ ማስጠንቀቂያ መሰረት ዛሬ ተግባራዎ እንቅስቃሴዎች በዶ/ር አብይ ትእዛዝ እየተረጉ ናቸው። ማ’ህሌት ፋንታሁን ዶ/ር አብይ ለሕዝቡ የማይሳብና የማይጠነቀቅ ይመስል፣ አጫሉን ሰምቶ ነው እርምጃ የወስደውን የሚል እድምታ ያለው ምልእክት ማስተላለፏ፣ ከትልቅ አክብሮት ጋር እርሷን የሚመጥን አይመስለኝም።

ከዚህ በኋላ በሚደረጉ ተመሳሳይ ዝግጅቶች ለታዳሚዎች ክብር ሲበል እንደ አጫሉ ያሉ አርቲስቶች መጋበዝ ብቻ ሳይሆን አካባቢዎች እንዲደርሱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። ከፈለጉ በራሳቸው ዝግጅት እንደ ጥንጨል ይዝለሉ።

ከዚህ በታች የአንጋፋው አሊቢራን የሃረር ኦሮምኛ “ማን ነው የሚለያየን ” የሚለው ጣ’እመ ዜማ ጋብዣቹሃለሁ።

  • Easy healthy recipes
  • Breaking New
  • Home
  • Peer Reviews
  • Platforms
  • Processes
  • Scholarly
  • Sectors
  • Share
  • Site
  • Easy healthy recipes