እኔ ግን በእውነት ሞኝ ነኝ ለካ! ምን መሰላቹህ አቶ ኢሳይያስ በዚህ በጉብኝታቸው ወቅት ለንግግር ሲጋበዙ የኢትዮጵያን ሕዝብ “በማወቅም ባለማወቅም ላጠፋነው ጥፋት ይቅርታ! ከስሕተታችን ተምረናል….!” ይላሉ ብየ ጠብቄ ነበረ፡፡ አልገርምም???
እሳቸው ግን ለካ እንዲህ ያለውን ቁምነገር ጨርሶ አላሰቡት ኖረው ከምሳ ግብዣ በፊት ለንግግር ሲጋበዙ ጭራሽ “ላደረጋቹህልኝ አቀባበል አመሰግናለሁ!” በሚባልበት በመሪዎች ጉብኝት በሚጠበቅ ሥነሥርዓት ላይ ለማመስገን እንኳ አልፈለጉ ኖረው በግድ በጉትጎታ ተነሥተው አረፉት፡፡
ርእሴ ላይ “ወዳልሠለጠነው ሕዝብ!” ማለቴ ከሁለት ዐሥርት ዓመታት በፊት አቶ ኢሳይያስ “ካልሠለጠነ የአማራ ሕዝብ ጋር መኖር አንፈልግም!” ብለው ስለነበረ ነው፡፡
ቆይ ግን በአቶ ኢሳይያስ መመዘኛ አለመሠልጠን ማለት እምቢ ለነጻነቴ፣ እምቢ ለክብሬ፣ እምቢ ለሉዓላዊነቴ፣ እምቢ….. ብሎ አጥንትን ከስክሶ ደምን አፍሶ ነጻነትን ማስከበር፤ ክብርን ማስጠበቅ ነው ማለት ነው???
መሠልጠን ማለት ደግሞ ሀገርን ለባዕዳን አሳልፎ ሰጥቶ ለባዕዳኑ በባርነት እያደሩ እንደ አህያ መገጠብ፣ መጠግረር፣ የባርነትን ግፍ መጋት፣ ሰብአዊና ሞራላዊ ክብርን ማጣት፣ በዚህ ውርደትም መኩራትና የባርነትን ውርስ እንደቅርስ መጠበቅ ….. ማለት ነው???
አቶ ኢሳይያስ ከዚህ ውጭ ሌላ ምክንያት ይኖረው ይሆን??? ምን ሊኖረው ይችላል??? በሹካ ፓስታ መብላትንና ተዛይዘው ያሉ በጥሊያኖች ጓዳ በቤት ውስጥ አገልጋይነት የተማሯቸውን ነገሮች ይሆን???
ይሄማ ከሆነ ጥሊያን ለመንግሥታቱ ማኅበር (league of nations) ቀርባ “እኔ ላሠለጥናቸው ነው እንጅ ቅኝ ልገዛቸው አይደለም!” ያለችውን እነ አቶ ኢሳይያስ ይቀበላሉ ማለት ነዋ??? አ…ይይይይ! ለዛ ነዋ እነ አቶ ኢሳይያስ ከጣሊያንና ከእንግሊዝ ነጥቀን ባሕረምድርን (ኤርትራን) ወደ እናት ሀገሯ መቀላቀላችን አስቆጥቷቸው በረሃ የወረዱት???
ግን እንዴት እንዲህ ሊያስቡ ቻሉ??? የቅኝ ግዛቱ ዘመን ጥሊያን እንዳለችው ሆኖ ነበር ወይ??? በፍጹም!!! ትምህርት እንኳ በገዛ ሀገራቸው ከአራተኛ ክፍል በላይ እንዲማሩ አይፈቀድላቸውም ነበረ፡፡ እስከ አራተኛ የተፈቀደላቸውም ምንም ከማያውቅ ባሪያ ጥቂት የሚያውቅ ባሪያ ለማግኘት አስበው ነው፡፡
ጥሊያኖች አስመራ ውስጥ ከሚሠሩት አገልጋዮቻቸው ወይም ባሮቻቸው በስተቀር የተቀረውን በገዛ ሀገራቸው አስመራን እንዲረግጡ እንኳ አይፈቅዱላቸውም ነበረ፡፡ ሌላው ሌላው የባርነት ግፉ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ይሄ ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው የሚናፈቀውና “ለምን ከዚህ ገላገሉን፣ ለምን ይሄንን አስቀሩብን!” አሰኝቶ ቂም ያሚያስቋጥርብን???
አየ እነ አቶ ኢሳይያስ! ለዛ ነው እንዴ ሌሎቹ ቅኝ ተገዢ የአፍሪካ ሀገራት ቅኝ ገዥዎቻቸው ለሀገሮቻቸው የሰጧቸውን ስሞች ወዲያ ጥለው ሌላ ስም ሲያወጡ እነ አቶ ኢሳይያስ ባርነት ስለሚያኮራቸው ኖሯል ለካ ጥሊያን ከኤርትራ (ቀይ) ባሕር ሥያሜ ወስዶ ያወጣላቸውን ኤርትራ የሚለውን ስም መቀየር ያልፈለጉት፡፡ መቸስ ጉድ እኮነው ባርነት ሲኮራበት!!!
አየ አቶ ኢሳይያስ! በዚህ በኛ በቤተ አማራ እኮ ባሪያ የሚለው ቃል አጥንት የሚሰብር የመጨረሻው የውርደት ስድብ እኮ ነው!!!
አየ ወዲ አፎምiii ታዲያ አሁን ይሄ ሰው እንኳን ለመሪነት ለሎሌነት እንኳ ብቁ ነው??? እኔን ብትጠይቁኝ እንኳን ለመሪነት ልመርጠው ይቅርና ለሎሌነት ወይም ለባሪያነት እንኳን አልመርጠውም!!!
ወዲ አፎም! ማለት ግን ምን ማለት ነው??? ትርጉሙ ምንም ይሁን የማወደስ የማቆላመጥ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የኤርትራ ሕዝብ አቶ ኢሳይያስን በዚህ የቁልምጫ ስም የሚጠራው ተገዶ፣ ፈርቶ፣ ለመኖር ብሎ ካልሆነና ወዶና ፈቅዶ ከሆነ ጠቅላላ ሕዝቡ ሁሉ ማሰብ የተሳነው ነው በሉኛ!!! እኔ ግን ወዶና ፈቅዶ አይመስለኝም፡፡ እኛስ ፈርተን ለመኖር ብለን መንግሥቱ ኃይለማርያምን “አባባ መንግሥቱ!” እንል አልነበር???
አቶ ኢሳይያስ ከአማራ ጋር ለመኖር ያልፈለገበትን ትክክለኛ ምክንያት ልንገራቹህ? ሌላ ምንም ሳይሆን የበታችነት ስሜት ችግር ነው (inferiority complex) አዎ ይሄ ነው ሌላ ምክንያት የለም፡፡
በምንና ከየት ባመጣው በራስ የመተማመን ስሜት (confidence) ከኩሩው፣ ለማንነቱ ለነጻነቱ ለክብሩ…. ሲበዛ ቀናኢ ከሆነው አማራ ጋር ይኑር??? የትኛው በራስ የመተማመን ስሜቱ ከአማራ ጋር ጎን ለጎን ያቁመው??? ከየት ያገኘው በራስ የመተማመን ስሜቱ ከአማራ ጋር እኩል ያናግረው??? ከወዴት ያመጣው በራስ የመተማመን ስሜቱ ከአማራ ጋር ዕኩል ያስቀምጠው???
እና ምክንያቱ ይሄው ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ምንም ምክንያት እንደሌለ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እሽ እሱ የለው ምክንያት ነው ትክክሉ ካላቹህ እሱ ሠልጥኖ የት ደረሰ??? የትም!!!
እናም ይሄ አኔ ያልኳቹህ ነው ምክንያቱ፡፡ ኢሳይያስ አማራ ማለት ማን እንደሆነ ደሴ በኖረበት ጊዜ ወ/ሮ ስሕን ት/ቤት በተማረበት ጊዜ አይቶታል ጠንቅቆም ያውቀዋል፡፡
አየ አቶ ኢሳይያስ አያሳዝንም ግን???
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
